የሀገር ውስጥ

ኮሚሽኑ በዜጎች ላይ የ...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሰሞኑን በሊቢያ እና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የጣሰ በመሆኑ አጥብቆ እንደሚያወግዝ አስታወቀ። ኮሚሽኑ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ራሱን አይ...

You are here: Homeአዲስ ዘመንየሀገር ውስጥ የሃይማኖት ነክ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይበልጥ ትኩረት ይሻሉ

የሃይማኖት ነክ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይበልጥ ትኩረት ይሻሉ

ለሚኒስቴሩ በየጊዜው የሚቀርቡ በርካታ ቅሬታዎችን በየደረጃው ለመፍታት

ጥረቱ መጠናከሩ ተገልጿል፤

 

ዜና ሐተታ

የአምልኮና የመቃብር ቦታ እንዲሰጣቸው ለሚመለከተው አካል ለረጅም ጊዜያት ጥያቄ ቢያቀርቡም ምንም ዓይነት ምላሽ እንዳልተሠጣቸው ነው የተለያዩ የዕምነት ተቋማትን ወክለው የተገኙ አካላት የሚገልጹት።

የእምነት ተቋማቱ ተወካዮቹ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ለሁለት ቀናት ባዘጋጀው መደበኛ የውይይት መድረክ ላይ እንዳሉት፣ ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩል መንገድ ለማስተናገድና ፍታሃዊነት ያለው አሠራር ለመዘርጋት እያደረገ ያለው ሀገር አቀፍ ጥረት የሚበረታታ ነው።

ይሁንና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩና ውስብስብ የሆኑ የአሠራር ሥርዓቶችን በመፍታት የእምነት ተቋማትን ጥያቄዎች ለመመለስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ዛሬም መለስ ብሎ ሊፈትሽ ይገባል።

የአምልኮና የቀብር ቦታዎች ጥያቄ አንገብጋቢና ቶሎ ምላሽ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ መሆኑን የሚያመለክቱት ተወካዮቹ፤ በተለይም የቀብር ቦታ በአቅራቢያቸው ባለማግኘታቸው ምዕመናን ሬሳ ይዘው ረጅም ርቀት የሚጓዙበትና የሚጉላሉበት ሁኔታ መኖሩን ያስረዳሉ።

አንዳንዶቹ ደግሞ «በገዛ ገንዘባችን ከግለሰቦች ላይ ለአምልኮ ቦታ ገዝተን ወደ እምነት ተቋማችን ስም ለማዞር ረጅም ጊዜ ይወስድብናል። አንዳንዴም ሕገመንግሥቱ ለሃይማኖት ተቋማት የሰጠውን መብት በማያውቁ አንዳንድ ፈፃሚዎች ዘንድ በፍቃድ እድሳት ምክንያት ከነጭራሱ ቤተ እምነታችን እንዲዘጋ የሚደረግበት አጋጣሚ አለ» ይላሉ። አክለውም «እድሳት ለማድረግና ህንፃ ለመገንባት ፍቃድ እንዲሰጠን በተደጋጋሚ ብናመለክትም ምላሽ የሚሰጠን አካል አላገኘንም» ሲሉ ይጠቅሳሉ።

ሌሎቹ ደግሞ «በደርግ ጊዜ ይዞታችን ተወርሶ በፍርድ ቤት እንዲመለስልን ቢወሰንልንም፣ በአንዳንድ የመንግሥት ተቋማት ዘንድ በሚስተዋለው ውስብስብ አሰራር ምክንያት ንብረቶቻችንን መረከብ አልቻልንም፤ በህግ የተሰጠንን ቦታ እንዳንጠቀምበት ተደርገናል፤ ከመንገድ ሥራ ጋር ተያይዞ የአምልኮ ቦታችን በመፍረሱ የሚሰጠው ካሳ በቂ አይደለም» በማለት ተናግረው በተለይም በክፍለ ከተሞችና በወረዳዎች አካባቢ ያለው የተንዛዛና ብልሹ አሠራር ሊፈተሽ እንደሚገባ ነው የሚያስገነዝቡት ፡፡

የውይይት መድረኩን የመሩት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው፣ ሁሉም ቤተ እምነቶች ህገመንግሥቱ በሠጣቸው ህጋዊ መብቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑና እኩልነታቸው እንዲረጋገጥ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ያመለክታሉ።

በተለይም በተደጋጋሚ የሚነሱትን የአምልኮና የቀብር ቦታ ጥያቄዎችን እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ የቀረቡትን ቅሬታዎች ለመፍታት ትኩረት ሠጥቶ እየሰራ መሆኑን ይናገራሉ። ለዚህም ከየትኛውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ከክልሎችና ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶና የግንኙነት አግባብ ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ይጠቅሳሉ።

በየጊዜው የሚቀርቡት የቦታ፣ የይዞታ፣ የካርታና የፍቃድ ጥያቄዎች ከብዛታቸው አኳያ በአፋጣኝ ምላሽ ለመሥጠት አስቸጋሪ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በየደረጃው ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ከችግሩ ስፋት አኳያ የሚፈለገውን ያህል ርቀት መጓዝ ተችሏል ተብሎ እንደማይታመን አስረድተዋል። በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላትና የእምነት ተቋማቱ የጋራ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ነው የሚያስገነዝቡት።

በሚኒስቴሩ በሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሰላም እሴት ዳይሬክተር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ገዛሃኝ ጥላሁን በበኩላቸው ፤ ሚኒስቴሩ 19 ከሚሆኑ የሃይማኖትና የእምነት ተቋማት 220ቅሬታዎች የቀረቡለት መሆኑን አመልክተዋል።

ቅሬታዎቹን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ችግሮቹን ለመፍታት ባደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት 126 የሚሆኑት ቅሬታዎች የተፈቱ መሆናቸውን ይጠቁማሉ። 75 የሚሆኑት ደግሞ በሂደት ላይ ያሉና ያልተፈቱ መሆናቸውን እንዲሁም 19 ቅሬታዎች መረጃና ማስረጃ ያልቀረበባቸውና ገና በምርመራ ሂደት ላይ ያሉ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ።

እንደ እርሳቸው ገለፃ፣ በአጠቃላይ ያልተፈቱት የመልካም አስተዳደር ችግሮች በየክልሉ ለመፍታት ጥረት እየተደረጉ ናቸው።

በአብዛኛው በማጣራት ሂደት ላይ ያሉና በፍርድ ቤት የተያዙትም በክልሎች ቀድሞ መታወቅ ሲገባቸው አልፈው የመጡ መሆኑ ታውቆ በኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት የሚቀርቡ የቅሬታ አቤቱታዎች በተዋረድ የመንግሥት አስተዳደር ቀርበው ምላሽ የሚሰጣቸው ይሆናል።

በመሆኑም ቅሬታ ያላቸው የእምነት ተቋማት ቅሬታቸውን በመረጃ በማስደገፍ ሊያቀርቡ ይገባል። በክልሎች ለረጅም ጊዜ የተንጓተቱ አንዳንድ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ክልሎች ክትትልና ድጋፍ እንዲሰጥበት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

Add comment


Security code
Refresh

የፎቶ ክምችት

ድረገጹን በመጎብኘት ላይ ያሉ

We have 101 guests and no members online
2097799
ዛሬ
ትላንት
በዚህ ሳምንት
ባለፈው ሳምንት
በዚህ ወር
ባለፈው ወር
አጠቃላይ ድምር
3374
8193
16707
2041305
153259
112856
2097799

የእርሶ IP: 54.211.79.99
የአገልጋዩ ሰዓት: 2015-04-28 14:08:45