የሀገር ውስጥ

ማህበሩ በሊቢያና በደቡ...

በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን የግፍ ግድያ በጥብቅ እንደሚያወግዘው በኢትዮጵያ የአህለልሱና ወልጀማአ አሶፍይ ማህበር የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ ኢብራሂም መሐመድ እንደገለጹት፤ ማህበሩ...

You are here: Homeአዲስ ዘመንየሀገር ውስጥ«የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሳይጠናቀቅ ሞት አይቅደመኝ» - የ119 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ

«የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሳይጠናቀቅ ሞት አይቅደመኝ» - የ119 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ

የዕድሜ ባለጸጋው የአሁኑ ትውልድ ታላቁን የህዳሴ ግድብ እንደጀመረው

እንዲፈጽምና የጀግና ልጅነቱን ዳግም እንዲያስመሰክር አደራ ብለዋል፤

 

«አባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሳይጠናቀቅ፣ አገሬ በብርሃን ላይ ብርሃን ሳታይ ሞት እንዳይቀድመኝ ጸሎቴና ተማጽኖዬ ነው» ሲሉ አንድ 119 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ገለጹ፡፡

ትውልዱ ለአገር ነፃነት ከወራሪ ኢጣሊያ ጋር በዱር በገደሉ እንደተዋደቁት አባቶቹ አባይን ገድቦ ለልማት ለማዋል ተጋድሎ ማደረግ ይኖርበታል ሲሉ የዕድሜ ባለጸጋው ሻምበል ባሻ ዘውዴ ፍሰሐ አሳስበዋል፡፡

በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለመስፈር እስካሁን ዕድል አላገኘሁም የሚሉት እኚሁ የ 119 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ የአድዋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በውስጣቸው የተዳፈነውን አገራዊ ልማት በወኔ ገልጸዋል፡፡

«አድዋ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ሞትን ሳይፈሩ ቤት ንብረት ሳይሉ ለአገርና ለወገን ፍቅር ሲሉ በጀግንነት የተዋደቁባት የጦር አውድማ ናት»ብለዋል፡፡

ቀደምት አባቶች አገር ከማስከበር አልፎ በዓለም አደባባይ ኢትዮጵያን የጀግና እናት አስብለዋታል ያሉት የዕድሜ ባለጸጋው የአሁኑ ትውልድ ታላቁን የህዳሴ ግድብ እንደተጀመረው በመፈጸም የጀግና ልጅነቱን ዳግም ማስመስክር ይጠበቅበታል በማለት አስገንዝበዋል፡፡

አባቶቻችን ባቆዩልን አገር ታፍረንና ተክብረን ከመኖር ባሻገር ያሻንን እየበላንና እየጠጣን በነፃነት ያረጀነው በጀግኖች አኩሪ ገድል፣ ደምና አጥንት ክስካሽ ውጤት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የአድዋ ድል ታሪክ ለአሁኑ ትውልድ የሚተረከው የልማት አርበኛ በመሆን አገሩንና ወገኑን ከበለጸጉት አገራት ተርታ ለማሰለፍ እንዲጀግን ነው ብለዋል፡፡

ይህ ትውልድ አሁን የተፋጠጠው ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ነው ያሉት ባሻ ዘውዴ፤ አገሩ ድሃ ተብላ ዝንተ ዓለም በሌሎች እንዳትጠራ ልማቱን ማጠዳፍ ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በመሆኑም ለረሃብና ለችግር የሚያጋልጠንን የድህነት ጦርነት ለመዋጋት የተጀመረውን የአባይ ግድብ በጋራ ልናስፈጽመው ይገባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አባይን የመገደብ ሙከራ በንጉሡ ዘመን ታስቦ እንደነበረ ጠቁመው፤ የግብፅ ስጋት ያኔም ተመሳሳይ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ በጀግንነትና በፍርድ በዓለም ላይ ተወዳዳሪ የሌላት አገር በመሆኗ ማንም በሀብታችን እንዳንጠቀም ሊያግደን አይችልም። ከዚያም የከፋ ቢመጣ ክብራችንን እናስጠብቃለን ሲሉ በግድቡ ላይ ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም ገልጸዋል፡፡

«58 ዓመታት በክብር ዘብ እና በፖሊስ ሠራዊት ውስጥ በወታደርነት ኢትዮጵያ ሀገሬን አገልግያሉሁ» ያሉት ሻምበል ባሻ ዘውዴ፤ በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ መዝመታቸውንና አሁንም ክፉ ጠላት አገራቸውን ቢተነኩስ ከልጆቻቸው ጋር ተሰልፈው እንደሚፋለሙት ምለውና ተገዝተው ተናግረዋል፡፡

 

 

 

Add comment


Security code
Refresh

የፎቶ ክምችት

ድረገጹን በመጎብኘት ላይ ያሉ

We have 56 guests and no members online
2094509
ዛሬ
ትላንት
በዚህ ሳምንት
ባለፈው ሳምንት
በዚህ ወር
ባለፈው ወር
አጠቃላይ ድምር
84
8193
13417
2041305
149969
112856
2094509

የእርሶ IP: 174.129.64.33
የአገልጋዩ ሰዓት: 2015-04-28 00:30:13