የእለቱ ዜና

 «አሜሪካ መንግሥትን በሃይል ለመናድ ለሚሞክሩ ቡድኖችና ፓርቲዎች ድጋፍ አታደርግም»   - የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፖለቲካ ጉዳዮች ተጠሪ ዊንዲ ሼርማን

«አሜሪካ መንግሥትን በ...

ዊንዲ ቬርማን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር በተወያዩበት ወቅት፤ ግንቦት ሰባትን ጨምሮ ሌሎች ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ የተቋቋመን መንግስት በሃይል ለመናድ ለሚሞክሩ ቡድኖችና ፓርቲዎች አሜሪካ ድጋፍ...

You are here: Homeአዲስ ዘመንዜናበኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ 20 በመቶ የመንግሥት ሠራተኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ

በኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ 20 በመቶ የመንግሥት ሠራተኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ

                             አቶ መስፍን መንግሥቱ፤

በመንግሥት በመገንባት ላይ ከሚገኙት አዳዲስም ሆነ ነባር የኮንዶሚኒየም ቤቶች መካከል የመንግሥት ሠራተኞች በዕጣ የ20 በመቶ የቅድሚያ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሠራር መዘርጋቱን የአዲስ አበባ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የ10/90፣ የ20/80 ነባርና የአዳዲስ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ልማት መርሐ ግብር እንዲሁም በማህበራት ፈላጊዎች ምዝገባ ለማከናወን የሚያስችል ዝግጅት ማጠናቀቁን አመለከተ፡፡

የከተማዋ የቤቶች ልማት አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መስፍን መንግሥቱ ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የመንግሥት ሠራተኞች በቤት ልማት መርሐ ግብሮቹ በተለየ መልኩ ቅድሚያ ተጠቃሚ ይሆናሉ። ይህን ማድረግ ያስፈለገው የመንግሥት ሠራተኛው የልማቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ በመሆኑ ይህን የህብረተሰብ ክፍል መደገፍ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡

እንደ እርሳቸው ገለፃ፤ ብዙኃኑ የመንግሥት ሠራተኛ ሀገሪቱ በምታካሂዳቸው የልማት ሥራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ ቢሆንም፤ በከፍተኛ የኑሮ ጫና ውስጥ የሚገኝ ከመሆኑም ባሻገር ሌሎች የገቢ አማራጮች የሉትም፡፡ በመሆኑም ልማቱን በዘላቂነት ለማስቀጠል እነዚህን ችግሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት በተለየ መልኩ ተጠቃሚ የሚሆንበትን አሠራር ዘርግቷል፡፡

አስተዳደሩ በከተማዋ ነዋሪ ዘንድ ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ፍትሐዊና አግባብነት ባለው መልኩ ለማስተናገድ ከአንድ ዓመት በላይ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም መሠረት ቤት ፈላጊ የህብረተሰብ ክፍሎችን በከተማዋ በ113 ወረዳዎችና 33የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና በሥራቸው ባሉ 177 ተቋማት በተዘጋጁት የምዝገባ ጣቢያዎች መመዝገብ የሚችልበት አሰራር መዘርጋቱን አመልክተው፤ የምዝገባ ሂደቱም በተደራጀ የሰው ኃይልና በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሣሪያዎች በመታገዝ የሚከናወን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሦስት የገጠር ወረዳዎች የኔት ወርክ ችግር በማጋጠሙ ነዋሪዎቹ በሌሎች ወረዳዎች የሚስተናገዱበት አግባብ መኖሩን አስገንዝበው፤ የምዝገባ ሂደቱን የሚያስፈጽሙ ከሃያ አራት ሺ በላይ ሙያተኞች፣ አስተባባሪዎችና ኃላፊዎች ሰልጥነው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በህብረተሰቡ በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ችግሮችንም ለመፍታት 11ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ከመረጃና ደህንነት ኤጀንሲና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተሰሩ ሥራዎች መኖራቸውን አስረ ድተዋል፡፡ አላስፈላጊ ድግግሞሽን ለማስቀረትም ከምዝገባ በኋላ የተመዝጋቢዎች የጣት አሻራ የሚወሰድበትንና ለየተመዝጋቢዎቹ ልዩ የምስጢር ቁጥር የሚሰጥበት አሰራር የሚዘረጋ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የምዝገባው መረጃም በድረ ገጽ እንደሚለቀቅ ተናግረዋል፡፡

ተመዝጋቢዎች መመዝገብ የሚችሉት ከሁሉም የቤት ልማት መርሐ ግብሮች ውስጥ በአንዱ ብቻ መሆኑን አስታውቀው፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ እድሉ ካመለጠው ዳግመኛ የሚመዘገብበት አግባብ እንደማይኖር አቶ መስፍን አስገንዝበዋል፡፡

በዚህም መሠረት መመዝገብ የሚፈልጉ ነዋሪዎች በቅድሚያ በራሳቸውም ሆነ በትዳር አጋራቸው ስም ቤት የሌላቸው፣ ቅድሚያ ክፍያውን መክፈል የሚችሉ፣ ወቅታዊ የነዋሪነት መታወቂያ ያላቸውና በተከታታይ ለሁለት ዓመት በአዲስ አበባ የኖሩ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ፣ በሀገር ከሌሉም የውክልና ማስረጃ ሊኖራቸው የሚገባ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም ነባር ተመዝጋቢዎች እስከተመዘገቡበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ዓመታት፣ አዳዲስ ተመዝጋቢዎች ደግሞ ለተከታታይ ሰባት ዓመታት መቆጠብ የሚገባቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በመካከሉ ስሙ ከምዝግባ ዝርዝር ውስጥ ተሰርዞ ገንዘቡ እንዲመለስለት የሚፈልግ የቤት ተመዝጋቢ የሚስተናገድበት ሁኔታም መኖሩን ጠቁመው፤ የቁጠባ መጠኑም እንደ ወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ሊጨምርም ሊቀንስም እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

ማህበራትም መመዝገብ የሚችሉት በቅድሚያ የቤቱን ወጪ 50 በመቶ በዝግ አካውንት ከፍለው ሲያጠናቅቁ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በዚህም መሰረት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ የሚያሟሉ የ10/90 እንዲሁም የነባርና የአዲስ 20/80 ተመዝጋቢዎች ምዝገባ ከሰኔ 3 እስከ21፣ ማህበራት ከሐምሌ15እስከ 30እንዲሁም የ40/60 ከነሐሴ5 እስከ 17 ቀን ድረስ የሚከናወን መሆኑን አስታውቀዋል።

ማንኛውም በዳግም ምዝገባው ያልተሳተፈ ነባር የ20/80 ቤት ተመዝጋቢዎች በራሳቸው ፈቃድ ምዝገባውን እንደተወውት እንደሚቆጠር አቶ መስፍን አስገንዝበዋል፡፡

Add comment


Security code
Refresh

የፎቶ ክምችት

ድረገጹን በመጎብኘት ላይ ያሉ

We have 27 guests and no members online
2044944
ዛሬ
ትላንት
በዚህ ሳምንት
ባለፈው ሳምንት
በዚህ ወር
ባለፈው ወር
አጠቃላይ ድምር
3639
5540
38433
1966776
100404
112856
2044944

የእርሶ IP: 54.204.147.224
የአገልጋዩ ሰዓት: 2015-04-19 16:24:23