የእለቱ ዜና

አንሸበርም አንሸበርም አ...

ዜና ሐተታ «... ኀዘን ቢበዛ ብንሰበርም አንሸበርም፣ የፈሪ ቢላ ወገን ቢቀጥፍም፣ አንሸበርም፣ ሰው መሳይ አውሬ ቢላ ቢስልም አንሸበርም...» የሚለውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነብዩ ባዬ የተገጠመውን መዝሙር የዩኒቨርሲቲው የቴአትር ትምህርት...

You are here: Homeአዲስ ዘመንዜናየመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ተለይተዋል

የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ተለይተዋል

ዜና ሐተታ

«ሁሉንም ተግባሮቻችንን በልማት ሠራዊት አቅም በመፈፀም እምርታዊ ውጤትን እናረጋግ ጣለን»«በመልካም አስተዳደር ዘርፍ ሥር ነቅል ለውጥን ለማረጋገጥ የአመራሩ ሚና ወሳኝ ነው» የሚሉት በአዳራሹ በግልጽ ከሚታዩት መፈክሮች መካከል ይገኙበታል።

የከተማዋ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ፤ የንግድ ኢንዱስትሪ፣የከተማ ሥራ አስኪያጅና በሥሩ የሚገኙ ፅሕፈት ቤቶችና የፌዴራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቶች የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚመለከቱ እቅዶች የቀረቡበትና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን መልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመፍታት ያዘጋጀው የውይይት መድረክ ከትናንት በስቲያ በእዚህ በአስተዳደሩ አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት እንደተጠቆመው፤ በከተማዋ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በተከናወኑ በርካታ ተግባራት የተሻሉ ውጤቶች ቢመዘገቡም በሚፈልገው መልኩ ተጨባጭ ለውጥ አልመጣም።

«ከኅብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎች ይነሳሉ፤በተለይ ከሰነድ አልባ ይዞታዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ትልቅ እንቅፋት እየሆነ ነው» ይላሉ የመድረኩ ታሳታፊ የአዲስ አበባ ሴቶች ፎረም ምክትል ስብሳቢ ወይዘሮ ካሰች ገብረ ጊዮርጊስ። ከይዞታ ባለቤትነት ጋር በተያያዘ የከተማዋ ነዋሪ ለረጅም ዓመታት የኖረበት ቤት «ሰነድ አልባ»እየተባለ ለእንግልት እየተዳረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት ችግሮችን ለመፍታት ቢሮውና ከተማ አስተዳደሩ ቀደም ሲል ተግባራዊ ባደረጉት አሠራር መሻሻል እየታየ መሆኑን ጠቅሰው፤ባለጉዳይ በስፋት ይንገላታ የነበረበት ሁኔታም መቀነሱን ነው የሚናገሩት። ይሁንና አሁንም ባለጉዳዮችን የስብሰባ መብዛትና «ስብሰባ ላይ ናችው» የሚለው መልስ እንዳስመረራችው ይናገራሉ።

ወይዘሮ ካሰች እንደሚሉት፤በቀጣይ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት ችግሮችን ለመፍታት ሁሉም ሥራውን በማክበር በቁርጠኝነት ከአስተዳደሩ ጋር በመተባበር ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው እንደሚሉትም፤ አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት ከመልካም አስተዳደርና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ኅብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ችግሮች በፈጣን ምላሽ አምጪ ዕቅዶች ተገቢውን ከትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለመፍታት ተንቀሳቅሷል። ይህንን ተከትሎም የተሻሉ ውጤቶች ቢመዘገቡም፤ መንግሥትና ኅብረተሰቡ በሚፈልጉት መልኩ ተጨባጭ ለውጥ አልመጣም።

የከተማ አስተዳደሩ የኅብረተሰቡን ቅሬታዎች ለመፍታት በተያዘው ዓመት ባለፉት ወራትም ይህንኑ አሠራር በመጠቀም በየደረጃው ተጨበጭ ለውጦች አስመዝግቧል፤በርካታ ችግሮችም ተፈትተዋል። ይሁንና አሁንም ያልተፈቱ በርካታ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ይስተዋላሉ።

«ከተማ አሰተዳደሩ የመልካም አሰተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ጎልቶ ይታይባቸዋል ያላቸውን ለይቷል» ያሉት ምክትል ከንቲባው፤ ከመሬት፣ ከካሳ ክፍያ ፣ ከመዘጋጃ ቤት አገልግሎት፣ ከውሃና ፍሳሽ፣ ከከተማዋ ፅዳትና ንግድ ነክ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከኅብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት እቅድ መዘጋጀቱን ነው የተናገሩት። ችግሮቹን ለመፍታት የጎላ ጠቀሜታ ባለው በእዚህ እቅድ ላይም ከከተማ አስተዳደር እስከ ወረዳ ከሚገኙ የአመራር አካላትና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ይጠቀማሉ።

እንደ አቶ አባተ ገለጻ፤ውይይቱ ያልተፈቱ ችግሮቹን ለመፍታትና ተከታታይነት ያለው ለውጥ በማስመዝገብ በየደረጃው የሚነሱ የሕዝብ ቅሬታዎችን ለመፍታትና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ያስችላል ።

በአዲስ አበባ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታትና ከእዚህ አኳያ እየተመዘገበ ያለውን ውጤት ለማስቀጠል በየደረጃው የሚገኙ የአመራርና ፈፃሚ አካላት አሁንም ከኅብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት በጋራ መሠራት እንዳለባቸው ነው ያስገነዘቡት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሌ እንደሚሉት፣በአዲስ አበባ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ላይ ቅሬታዎች፣ ከመሬት ዝግጅት ጋር የተያያዙ በርካታ ችግሮች፣ሕገ ወጥ ግንባታዎች፣ከፋቃድ አሰጣጥ ጋር ያልተጣጣሙ ግንባታዎችም ይስተዋላሉ። ኅብረተሰቡን መጥቀምና መልማት እያለባቸው ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችም በብዛት ይገኛሉ። «ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት እነዚህን ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን የመለየት ሥራ በስፋት እያከነወነ ይገኛል ያሉት ኃላፊው፣ እነዚህን ይዞታዎች ለመለየትም ሠፊ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ነው ያመለከቱት።

አቶ ሰለሞን እንደሚሉት፤የሚወሰደውን ሕጋዊ እርምጃ ተከትሎ ለመንግሥት ተመላሽ የሚደረጉት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ወደ መሬት ባንክ ገቢ ይደረጋሉ። ይህም መሬት ከመንግሥት ወስደው ወደ ግንባታ ያልገቡትን ሁሉ ይመለከታል።

«ሕገ ወጥ ግንባታ በመገንባት ከጊዜ በኋላ መንግሥት ሕጋዊ ያደርገናል የሚል የተሳሳተ አመለካክት በኅብረተሰቡ ዘንድ ይስተዋላል» ያሉት አቶ ሰሎሞን፣በተገልጋዮች ዘንድም የግንዛቤ እጥረት እንዳለም ነው የጠቆሙት።

መሬትና መሬት ነክ በሆኑ ጉዳዮች ከመመሪያና ግልጽነት ጋር በተያያዘ የሚጣረሱ ሃሳቦች እንዳሉም ጠቅሰው፤መሰል የአሠራር ክፍተቶችን ለመሙላት በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት መመሪያዎቹን በመገምገም ክፍተቶችና በመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ኅብረተሰቡ እንዲያ ውቃቸው የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ይጠቁማሉ።

«በከተማዋ የመልካም አሰተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፤አሁንም ግን ከችግሮቹ አልተላቀቅንም» ነው ይላሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይሌ ፍሰሐ።

እንደ አቶ ኃይሌ ገለጻ፤የከተማ አስተዳደሩ ችግሮቹ ጎልቶ የሚታይባችውን የአምስት ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ የመለየት ሥራ አከናውኗል፤እነዚህም ችግሮች የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን አስመልክቶ ኅብረተሰቡ ከሰጣቸው አስተያየቶች ጋር ተመሳሳይ ሆነው ተገኝተዋል። የችግሮቹ ዋና መነስኤ በመሆን የተለዩትም በአመራር አካላት ዘንድ የሚታየው የቁርጥኝነት ማነስና ቀጣይነት ያለው ወጥ አሠራር አለመኖር መሆናቸው ታውቋል። የከተማ አስተዳደሩ በተቋማቱ ዘንድ እቅድ አውጥቶ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ አስፈላጊ ሆኖ እንዳገኘው ጠቅሰው፤ሌሎች በአስተዳደሩ በኩል የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትም በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝ ይናገራሉ።

Add comment


Security code
Refresh

የፎቶ ክምችት

ድረገጹን በመጎብኘት ላይ ያሉ

We have 32 guests and no members online
2081335
ዛሬ
ትላንት
በዚህ ሳምንት
ባለፈው ሳምንት
በዚህ ወር
ባለፈው ወር
አጠቃላይ ድምር
243
4578
40030
2006511
136795
112856
2081335

የእርሶ IP: 54.145.246.183
የአገልጋዩ ሰዓት: 2015-04-26 01:34:01