ማህበራዊ

ይህንን ያድርጉ...

በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ማለትም ዓይን፣ ጆሮ፣ አፍንጫ፣ ጉሮሮ ወይም የአየር ቧንቧ ውስጥ ባዕድ ነገር ሊገባ ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ እንደ ጉድፍ፣ ጥራጥሬ ፣ ሳንቲም፣ ዶቃ፣ የብ ረት ወይም የዕንጨት ስባሪዎች...

You are here: Homeአዲስ ዘመንማህበራዊየዩኒቨርሲቲዎች ሰባ ሰላሳ ቀመር በጥናት ሲደገፍ

የዩኒቨርሲቲዎች ሰባ ሰላሳ ቀመር በጥናት ሲደገፍ

23ኛው አገር አቀፍ ትምህርትና ሥልጠና ጉባዔ ላይ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፤

 

ሀገሪቱ የአምስት ዓመቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ጉዞ ከጀመረች ሦስት ዓመታትን አስቆጥራለች። እነዚህ ዓመታት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሽግግርን ለመፍጠር ከፍተኛ ትኩረት የተደረገባቸው ናቸው ማለት ይቻላል። በአሁኑ ወቅት መንግሥት የትምህርት ልማትን በማፋጠን ከድህነትና ኋላቀርነት ለመውጣት ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው። ትምህርቱን ተግባር ተኮር ለማድረግና በጥናትና ምርምር የተደገፈ ለማድረግ እጅግ በርካታ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ለእቅዱ ስኬታማነት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

መሃይምነትን ለማጥፋትም ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የመማር ማስተማሩ ሂደት በተጠናከረ መንገድ እንዲመራ እያደረገ ነው። ከመንግሥትና አጋር ድርጅቶች በተጨማሪ በአገሪቱም ያሉ የግል የትምህርት ተቋማትም በትምህርት ልማት ዘርፍ በመሳተፍ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።

መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሳይንስና ቴክኖሎጂው ትምህርቶች ልዩ ትኩረት በመስጠቱ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት70ከመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ቀሪ ሰላሳ ከመቶ የሚሆኑትን ደግሞ በማህበራዊ ሳይንስ እንዲመ ደቡ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱ እያደር እየተጠናከረ ይገኛል። በተለይም ለኢንጂነሪንግ ትምህርት ትልቅ አፅንኦት በመሰጠቱ በመላው አገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተግባራዊነቱ በትጋት በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።

23ኛው አገር አቀፍ የትምህርትና ሥልጠና ጉባኤ ከጥቅምት 14ቀን 2006 .ም እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2006.ም በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል። በጉባኤው ላይ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ከአጋር ድርጅቶች፣ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በአብዛኞቹ የመንግሥት ትምህርት ተቋማትም እቅዱ ከታሰበው በላይ እየተተገበረ መሆኑን የዩኒቨርሲቲዎቹ ተወካዮች አስረድተዋል። ለጥናትና ምርምርም በር ከፋች እንደሆነም በመግለፅ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መብራቱ ገብረማርያም እንደገለጹት፤ ተቋማቸው ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ነው። ዩኒቨርሲቲው በ1999 .ም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ የጥናት ሥራዎችን እያከናወነ ትርጉም ያለው ውጤት ማስመዝገበ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የሰባ ሠላሳ የትምህርት ትግበራን ከታቀደው በላይ በመሥራት በሳይንስ ትምህርት የሚቀበላቸውን ተማሪዎች ሰባ አምስት በመቶ አድርሷል። ቀሪው ሃያ አምስት በመቶዎቹ በማህበራዊ የትምህርት ዘርፍ የተቀበላቸው ነው። የሚሰጠው ትምህርትም ተግባር ተኮር ለማድረግ እየሠሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የቤተ መጽሐፍትና የቤተ ሙከራዎችን ግንባታ በማከናወን አገራዊ አደራን እየተወጡ መሆኑንም ጠቁመዋል። በጥናቱም ዘርፍ የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የተለያዩ ማህበረሰብ ተኮር ጉዳዮችን ነቅሶ በማውጣት የተሻለ የሕይወት መስመር ለመከተልና ከድህነት የመውጣትን መርሀ ግብር በማፋጠን ላይ እንደሆኑም ዶክተር መብራቱ ተናግረዋል፡፡

በሚዛን ቴፒ አካባቢ የሚመረቱ ገበያ ተኮር የሆኑ እንደ ኮረሪማና ቡና ያሉ ምርቶችንም ትኩረት ሰጥተው በመሥራት ትረፋማነትንና እንዲሁም አርሶ አደሩ ተጠቃሚ የሚሆንበትን አቅጣጫ በመንደፍ እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ዶክተር መብራቱ አስረድተዋል፡፡ ይህም በተለያዩ ጊዜያት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ከመሙላቱ ባሻገር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የበለጠ እንደሚያረጋግጥ አስገንዝበዋል፡፡

የእንስሳት አያያዝን በተመለከተም አርሶ አደሩን በማሰልጠንና ዘመናዊነት እንዲላበስ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል። በአካባቢው የሚገኘው ጎደሬ የተባለ የእፅዋት ዝርያ ከብቶች ቅጠሉን እንዳይመገቡ በማድረጉ ረገድና በሌላም በኩል ሥሩን ጥቅም ላይ በማዋል ለከብቶች መኖነት በስፋት ሊያገለግል በሚችል መልኩ እየሠሩ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ይህም በአካባቢው ትኩረት ላላገኙ አንዳንድ አብይ ጉዳዮች አቅጣጫ ጠቋሚ መሆኑን አመልክቷል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚና የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍቃዱ ለሜሳ በበኩላቸው ለጥናትና ምርምር ቅድሚያ በመስጠት በተለይም በጥናትና ምርምር ሂደቱ ላይ ትኩረት በመስጠት ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የማህበረሰቡን ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ አስር የጥናት ሥራዎች እንደተሠሩ ተናግረዋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ የግብረሠናይ ድርጅቶች እርዳታ መስጠት ምን አሉታዊና አዎንታዊ ገጾች እንዳሉት፤ በኮብል ስቶን ማንጠፍ ላይ የተሠማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ችግሮችና መፍትሔ፤ በከተማ ዙሪያ የሚገኙ ኢንዱስት ሪዎችና ፋብሪካዎች ምርታማነትን መጨመር በሚቻልበት መንገድ፣ የጨርቃ ጨርቅና ብረታ ብረት እንዲሁም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርታማነትም በሚያሳድጉበት ሁኔታ ላይ ጥናት በማካሄድ ለውጥ እየመጣ እንደሆነም ነው፡፡ በትምህርት ቅበላው 72 ከመቶ በተፈጥሮ ሳይንስና 28 ከመቶ በማህበራዊ ሳይንስ ምደባ በመተግበር ለምርምሩ እምርታ ሊያመጡ የሚችሉ በእውቀት የታነጹና ችግር ፈቺ ምሁራንን ለማፍራት እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

«ማህበረሰቡ በችግሮች ውስጥ ተዘፍቆ መኖር የለበትም፣ የሌሎችን ልገሳ መጠበቅ የአገር ልማት ዘላቂነት ትርጉም ያሳጣዋል» የሚሉት ዶክተር ፈቃዱ፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የህብረተሰቡን ችግር በመለየት መፍትሔ መስጠት እንዳለባቸው በአጽንኦት ይናገራሉ ።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍቅሬ ለሜሳ በበኩላቸው፤« በዚህ ዘመን በጥናትና ምርምር ያልታገዘ ትምህርት ልጓም የሌለው ፈረስ ነው» ሲሉ የምርምር አስፈላጊነትን አንክሮ ሰጥተውበታል ፡፡

የሰባ ሰላሳን የትምህርት ቅበላና የመማር ማስተማርን ሂደት አስመልክቶም የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ስኬት እያስመዘገበ እንደሆነ ተናግረዋል። በተለይም ለኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፍ ትኩረት በመስጠት በሀገሪቱ የሚስተዋሉ የባለሙያዎችን እጥራት ለማስወገድ ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ነው የገለጹት። በጥናትና ምርምር መስኩም አያሌ ውጤቶችን እያስመዘገበና ቀጣይነት ያለው የትምህርት ልማት በማፋጠን ሀገራዊ አደራን እየተወጣ እንደሆነም በመግለጽ ጭምር።

ዘመናዊ የእንስሳት አያያዝና እንክብካቤን በተመለከተም በተለይም የዶሮ ጫጩት ማሳደጊያ ሳጥን በመፈብረክ በአካባቢው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሆነም ገልጸዋል። ከአገር አለፍ ሲልም በጎረቤት አገሮች የምርምሩን ውጤት ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰባዊ አለኝታነትን የሚገልጽ የጥናትና ምርምር ሥራን እንዳከናወኑ ዶክተር ፍቅሬ ተናግረዋል።ከአገር ውጭም ኬንያ፣ታንዛኒያ፣ ዑጋንዳ፣ ምርቱን በመጠቀም በምርምር ውጤቱ ተጠቃሚነታቸውን ማትረፋቸውን በግብረ መልሳቸው አረጋግጠዋል።

የወባ ትንኝ በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ በማጥናት እንዲሁም የወባ በሽታን ለመከላከል ጥቅም ላይ እየዋሉ በሚገኙ መድኃኒቶች ላይ ውጤታማነታቸውን በመፈተሽ እየሠራ መሆኑን፤ በግልገል ጊቤ ዙርያ የአካባቢ ጥበቃ በማከናወን የመሬት መንሸራተትና የአፈር መሸርሸር በሚቀንስበት መልኩና የገጠሩ ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆን በተለያዩ አነስተኛ የውሃ አካላት ላይ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ተግባርም እንዳከናወኑና እጅግ በርካታ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንዳደረጉም ገልጸዋል።

ጥናትና ምርምሩ ተደራሽ እንዲሆንና በእዚህም ህብረተሰቡ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ከአገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የጠነከረ የጋራ ስምምነት በመፍጠር እየሠሩ እንደሆነም አመልክተዋል። ይህም የእውቀት ሽግግርን ከመፍጠሩ ባሻገር በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ቀላል በሆነ መንገድ መፍትሔ ለማበጀት እንደሚጠቅም ተናግረዋል።

ለአብነትም ከቤልጅየም ሉቨን፣ የሆላንድ ቫግኒገን፣ የካናዳ የተለያዩ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ የአሜሪካ፣የኖርዌይ፣ ዴንማርክና ጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በቅርበት ከሚሠሩ የውጭ አገር የትምህርት ተቋማት መካከል ጥቂቶቹ መሆናቸውን ዶክተር ፍቅሬ ተናግረዋል።

ከአገር ወስጥ ደግሞ ከአምቦ፣ መቀሌ፣ ባህርዳር፣ መቱ፣ ወላይታ ሶዶ፣ እንዲሁም በጅማ አካባቢ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከላት ጋር በቅርበት በምርምርና ጥናት እንዲሁም በመተባበር የሚሠሩዋቸው በርካታ ሥራዎች እንዳሉዋቸውም አስታውቀዋል።

በተለይም በቅርቡ ወደ ሥራ እየገቡ የሚገኙ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ የበለፀጉ የሰው ኃይል እንዲያፈሩ በቅንጅት እንደሚሠሩም አስገንዝበዋል። በአገሪቱ የሚስተዋሉ በርካታ ችግሮችም በአነስተኛ ወጪና በጥቂት የሰው ኃይል ማቃለል እንደሚቻል ዶክተር ፍቅሬ አብራርተዋል። በተለይም ደግሞ በአሁኑ ወቅት አገሪቱ የምትፈልጋቸውን የሳይንስ ባለሙያዎች ለማፍራት ሌት ተቀን መሥራት ግድ ይላል ይላሉ።

Add comment


Security code
Refresh

የፎቶ ክምችት

ድረገጹን በመጎብኘት ላይ ያሉ

We have 37 guests and no members online
2101457
ዛሬ
ትላንት
በዚህ ሳምንት
ባለፈው ሳምንት
በዚህ ወር
ባለፈው ወር
አጠቃላይ ድምር
7032
8193
20365
2041305
156917
112856
2101457

የእርሶ IP: 54.204.243.45
የአገልጋዩ ሰዓት: 2015-04-28 23:36:31