Items filtered by date: Sunday, 11 March 2018

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 1768 ፍሊፕ አስትሌ የተባለ እንግሊዛዊ ለዘመናዊው ዓለም አንድ አዲስ በትርኢት የታጀበ እና ተመልካችን ያስደነቀ ትዕይንት አስተዋወቀ። በስፖርቱ እና በመዝናኛ መድረኮች ላይ ልዩ ተቀባይነት ያለው ይህ የመድረክ ትዕይንት በሰፋፊ ድንኳኖች ውስጥ ከከፍታ ላይ በተንጠለጠሉ ገመዶች የጅምናስቲክ (ትራፔዝ)፣ የአክሮባት፣የዳንስ፣ ፊትን በሚያዝናኑ አሻንጉሊቶች በመሸፈን በትናንሽ ኳሶች ትዕይንት ማሳየት፣ የአስማት ጥበብ እንዲሁም የተለያዩ ስፖርታዊ እና አዝናኝ ዝግጅቶች ይቀርቡበታል። በዘመናችን በስፋት ተቀባይነት ካገኙት የመድረክ ላይ ትዕይንቶች የሚመደበው ሰርከስ።

እንግዲህ ፍሊፕ አስትሌ ይህንን ስፖርታዊ ትዕይንት ነው በዘመናዊ መንገድ እና በአዲስ አቀራረብ ከላይ በጠቀስነው ዓመት ለታዳሚዎች ማቅረብ የጀመረው። አስትሌ የሰርከስ ስፖርትን በቀዳሚነት የጀመረ ባይሆንም አዳዲስ ትርኢቶችን ማስተዋወቅ ስለቻለ «የዘመናዊው ሰርከስ አባት» በመባል ይታወቃል። በወቅቱ አስደናቂ ከሆኑት ትዕይንቶቹ ውስጥ «ትሪክ ራይዲንግ» ወይም ፈረሶችን ግርምትን በሚያጭሩ ድርጊት ውስጥ እየሆኑ መጋለብን አስተዋውቋል። በተለይ ደግሞ ሌሎች ትርኢት የሚያሳዩ ተቀናቃኞቹ ማድረግ ከሚችሉት በተሻለ በክብ ቦታ ላይ ግልቢያን ያደርግ ነበር። በኋላም እርሱ የጀመረው አዲስ ትዕይንት «ሰርከስ» የሚል ስያሜ ማግኘት ቻለ። እአአ1770 የተለያየ አስደናቂ ክህሎት ያላቸውን የሰርከስ ስፖርተኞች በመቅጠር ሥራዎቹን በስፋት ማቅረብ ጀመረ።
ፈር ቀዳጁ ስትሌ ትዕይንቱን በዘመናዊ መልክ ካስተዋወቀ በኋላ በቀጣዮቹ 50 ዓመታት በጣም በርካታ ማሻሻያዎች እየተጨመሩበት መሻሻሎችን ማሳየት ጀመረ። ሙዚቃዎች በሰርከስ ትርኢት «በኪሮግራፈሮች» እየተቀመሙ መቅረብ ጀመሩ። በስፖርታዊ ትዕይንቱ ላይም ለማመን የሚያስቸግር ብቃት ያላቸው ሰዎች መታየት ጀመሩ። በጊዜው በተጣበበ እና ክፍት በሆኑ ቦታዎች ላይ ትርኢቶች ይቀርቡ ነበር። ሆኖም አስትሌ እና የስፖርታዊ ትርኢቱ አቅራቢ ጓደኞቹ ለዘመናዊ ሰርከስ መፈጠር ጥረት በማድረጋቸው በሰፋፊ ቦታዎች ላይ ትዕይንቶች መቅረብ ጀመሩ። በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከእንጨት እና ከተለያዩ ባህላዊ መሳሪያዎች በሚዘጋጁ ቁሶች የትዕይንት ቦታዎችን ማዘጋጀት ጀመሩ። ተወዳጅነቱ እጅግ እየሰፋ እና በመላው ዓለም ላይ ትኩረት እያገኘ መምጣቱ የመታደሚያ ስፍራዎች ዘመናዊ እንዲሆኑ እና የትርኢት ማሳያ መሳሪያዎች እንዲሻሻሉ በሮችን ከፍቷል። በዚህም በተለምዶ «ቴንት» እና «ቢግ ቶፕ» በመባል የሚታወቁ ትላልቅ ትርኢት ማሳያ ድንኳኖች በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተዋወቁ። ቴንት አሁንም ድረስ በሰርከስ ስፖርታዊ ትዕይንት በዋናነት ጥቅም ላይ የሚውል መሳሪያ ሆኗል።
በ1980ዎቹ እጅጉን የዘመነ ወይንም «ኮንቴምፖራሪ ሰርከስ» እየተፈጠረ መጣ። የዓለምን የጅምናስቲክ እና ብዛት ያላቸው ትዕይንቶችን በአንድ ላይ መታደም የሚፈልጉ ሰዎች ቀልብ መቆጣጠር ቻለ። በዚህም በዓለማችን ላይ በጣም በርካታ የሰርከስ ቡድን አባላት እየተፈጠሩ፤ አንዳቸው ከአንደኛቸው እየተማሩ አንዳንዴም እየተፎካከሩ በሰው ልጅ ክህሎት አይሞከሩም የተባሉ ድርጊቶችን ማቅረብ ጀመሩ። ከተለመደው ያፈነገጡ፣ አንዳንዴም ለአደጋ የሚያጋልጡ፣ ልዩ የሆነ ተሰጦን የሚጠይቁ እንዲሁም ተአምር የሚመስሉ ድርጊቶች በሰርከስ ትዕይንት ላይ እየቀረቡ የብዙ ሚሊዮን ሰዎችን ቀልብ ጨምድደው መያዝ ቻሉ።
ሮማውያን ግላዲያተሮቻቸውን ለማፋለም፣ የፈረስ ውድድሮችን ለማድረግ፣ በመድረክ ላይ ዝግጅቶችን ለማሰናዳት እንዲሁም ያሰለጠኗቸውን የዱር እንስሳት ትርኢት ለህዝብ ለማቅረብ በማሰብ የጀመሩት የሰርከስ ትርኢት አሁን ላይ ቅርፁን አስፍቶ በዘመናዊ መንገድ መቅረብ ጀምሯል። በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሞናርኪያል ዘመን የተገነባው «ሰርከስ ማክሲመስ» የተባለው ከእንጨት እና ከተለያዩ ቁሶች የተሰራው ትርኢት ማሳያ ነበር። ይህ ማሳያ እስከ 250 ሺ ታዳሚዎችን የመያዝ አቅም ነበረው። በሮም ስልጣኔ ከተገነቡ ትልቅ ስታዲየሞች መካከልም ተጠቃሽ ነው።
በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን ለቁጥር የሚከብዱ የሰርከስ ማሳያ ስፍራዎች ይገኛሉ። በዚያኑ ልክ የስፖርታዊ ትዕይንቱ በላቀ ሁኔታ አመርቂ ለውጦችን ማስመዝገብ ችሏል። በቴክኖሎጂ እየታገዘ ፈጣን የሆነ ለውጥም አምጥቷል። ስፖርት በተለይም የሰርከስ ትርኢት ታዳሚያንን በአንድ ላይ በማሰባሰብ፣ በጎ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ይታወቃል። የተለያዩ ባህሎችን በአንድነት በማሰባሰብ ፍቅርን፣ አንድነትን እና መልካምነትን የመስበክ አቅሙ ከፍተኛ መሆኑንም ይነገርለታል።
ሰርከስ በኢትዮጵያ
ሰርከስ ውስብስብ ሳይንስ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። አንድ ነገር ለመከወን ከጊዜ፣ ከእውቀት እና ከቅልጥፍና ጋር መቀናጀት ያስፈልጋል። ከባድ የአዕምሮ እና የአካል እንቅስቃሴ የሚጠይቅም ነው። አንዳንድ ከሰውነት ቅርፅ እና ቁመና ጋር የሚያያዙ ስራዎችም አሉት። ጅምናስቲኩ በከባድ ድርጊት ስለሚታጀብ ተመልካቾች ባለሙያው በእንቅስቃሴ ላይ ሲሆን ጉዳት እንዳይደርስበት ስጋት ያድርባቸዋል። ነገር ግን የተሰጦው ባለቤቶች «በልምምድ እና በሂደት ሁሉም ለውጥ ይመጣል» ይላሉ። ማናቸውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ፈተና ማጋጠሙ እንደማይቀርም ነው የሚገልፁት።
በዓለማችን ላይ የተለየ ትኩረት ተሰቶት ተሰጦ ያላቸውን ሰዎች በስፋት የሚያሳትፈው ስፖርታዊ ትዕይንት በኢትዮጵያም የቅርብ ጊዜ ትዝታ አለው። ስፖርታዊ ትርኢቱ በፕሮፌሽናል ደረጃ ተግባር ላይ መዋል ከጀመረ ሦስት አስርት ዓመታት እንኳን አላስቆጠረም። ነገር ግን ይህን ሙያ ጠንቅቀው የሚያውቁት ሰዎች ሲናገሩ «በተጠና እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ስፖርቱ በሰርከስ ትርኢት መልክ ለታዳሚያን ባለመቅረቡ እንጂ ከድሮም የነበረ ነው» ይላሉ። ባህላዊ በሆነ መንገድ እቃ በጭንቅላታቸው በመሸከም ብዙ ርቀት ሚዛናቸውን ጠብቀው የሚጓዙ የኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ እናቶች፣ የተለያዩ የዳንስ እና የጅምናስቲክ ትርኢት የሚያሳዩ ብሄር ብሄረሰቦች ለዚህ ትክክለኛ ምሳሌ እንደሚሆኑም ይገልፃሉ።
ሰርከስ በኢትዮጵያ ውስጥ በፕሮፌሽናል ደረጃ የተጀመረ ሰሞን ተስፋ የሚሰጡ እንቅስቃሴዎች ተስተውለውበት ነበር። ይህ የሆነው ደግሞ የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ከተለያዩ አካላት ይገኝ ስለነበረ መሆኑን ለስፖርቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ። ይህ አይነት ድጋፍ በስፖርቱ ላይ ለውጥ ማምጣት ችሎ ነበር። በርከት ያሉ ትዕይንቶችም ይዘጋጁ ነበር። ሆኖም ስፖርታዊ ትዕይንቱ አሁን ላይ ከምንጊዜውም በበለጠ በመቀዛቀዝ ላይ ይገኛል። የተወሰኑ የሰርከስ ቡድን አባላት በራሳቸው የግል ተነሳሽነት ስፖርቱ እንዳይዳከም ከሚያደርጉት ጥረት በዘለለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ትኩረት የነፈጉት ይመስላል።
በአሁን ሰዓት በርካታ ብቃት ያላቸው ልጆች እራሳቸውን በራሳቸው የሚያሰለጥኑ እና ብዙም ድጋፍ የማያገኙ ናቸው። በመስኩም ከመንግሥት እና ከስፖርት አካላት ያለው ግንዛቤ ደካማ ነው። በተለያየ ቦታ ክህሎት ኖሯቸው በተበታተነ ሁኔታ የሚሰሩ ልጆችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚደረገው ሙከራ ውስን ነው። በተለይም የልምምድ ስፍራ በቀላሉ አለማግኘት እና ያሉትም ቦታዎች ምቾት የጎደላቸው መሆናቸው ዋናው እንቅፋት እየሆነ መጥቷል።
ሰርከስ በኢትዮጵያ ጅምር እና ያልጠነከረ ታሪክ ያለው ከመሆኑም በላይ ትኩረት መነፈጉ ስፖርቱ ብዙ ሳይጓዝ ጭርሱኑ እንዳይመናመን ስጋት ይፈጥራል። ሆኖም ይህ ሁኔታ እንዳይከሰት በግላቸው ጥረት የሚያደርጉ አካላት አልጠፉም። ከተመሰረተ 3 ዓመታት ያስቆጠረው የጋሞ ሰርከስ ቡድን ከ80 በላይ ልጆችን በማፍራት ኢንተርናሽናል ትርኢቶችን በማሳየት እና የተስፋ ብልጭታ በመስጠት ከሚጠቀሱት መካከል ነው። በተገቢው መንገድ ድጋፍ የሚደረግላቸው ከሆነ ለወደፊት በሰርከስ እና ጅምናስቲክ ስፖርት አገሪቷ የተሻለ ተስፋ እንደሚኖራት የሚያመላክት አቅም ያላቸው አንዳንድ የሰርከስ ቡድኖችም መጥቀስ ይቻላል።
ሰርከስ ደብረብርሀን
በኢትዮጵያ ውስጥ የሰርከስ ቡድን መስርቶ ለበርካታ ዓመታት ስፖርቱን ለማሳደግ ጥረት ከሚያደርጉት መካከል «ሰርከስ ደብረብርሀን» አንዱ ነው። የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ ባለፈው ሳምንት በፍካት የሰርከስ ቡድን የተሰናዳውን እና ለሦስት ቀናት ያህል የቆየውን የአፍሪካ ሰርከስ ፌስቲቫል በታደመበት ወቅት ተጋባዥ ከነበረው የቡድኑ ኃላፊ ጋር ጥቂት ቆይታ አድርጎ ነበር።
አቶ ተክሉ አሻግሬ የሰርከስ ደብረ ብርሀን ኤክሲኩቲቭ እና አርቲስቲክ ዳይሬክተር ነው። ቡድኑ ከኢትዮጵያዊ ባህላዊ እሴት ጋር የሰርከስ ስፖርትን አመጋግቦ የመስራት እቅድ እንዳለው ይናገራል። ሙዚቃው እና ስፖርቱ እንዲሁም የተለያዩ ትዕይንቶችን ማቀናጀት አስፈላጊ ነው ይላል። ሰርከስ ደብረብርሀን ዘመናዊ እና ሁሉን አቀፍ የኪነ ጥበብ ማዕከል የመገንባት ዓላማንም አንግቦም ይሠራል። በአገሪቱም ሆነ በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የመሆን ህልም እንዳላቸው ይገልፃል። ሆኖም ግን የሰርከስ ስፖርታዊ ትዕይንት ብዙ ፈተናዎች እያጋጠሙት እንደሆነ ይገልፃል።
ለሰርከስ ስፖርት ጎልቶ ያለመውጣት ዋንኛ እንቅፋት በወረቀት ላይ የተቀመጡ አሰራሮች ወደ ተግባር መቀየር አለመቻላቸው በሆኑን በአብነት ይጠቅሳል። አስፈላጊውን ትኩረት እና ድጋፍ ማድረግ ቢቻል ብሎም ህጉን ወደ ተግባር መቀየር ቢቻል የዓለምን መድረክ መቆጣጠር የሚችል አቅም ያላቸው ልጆች መኖራቸውን ይናገራል።
ሰርከስ ደብረብርሀን ምንም እንኳን በዙ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ስኬቶች እንዳስመዘገበ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከ100 በላይ የምስጋና ሰርተፍኬቶች በስራዎቻቸው አግኝተዋል። ከአራት ዓመት በፊትም ከስዊድን የዓመቱ ምርጥ ፕሮዳክሽን በሚል ሽልማት ተቀብለዋል። ሰርከስ ደብረብርሃን በርካታ ሥራዎችን የሠራ ቡድን ነው። ስራዎቻቸው ኢትዮጰያዊነትን የሚያንፀባርቁ መሆናቸው ተወዳጅ አድርጓቸዋል። በተለያየ አጋጣሚ ሲሲቲቪ፣ ቢቢሲ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን ሰጥተውታል። ይሄ ቡድን ከላይ ለማስቀመጥ እንደሞከርነው ለሁለተኛ ጊዜ የፍካት ሰርከስ ቡድን ባዘጋጀው የአፍሪካን ሰርከስ ፌስቲቫል ላይ ተጋባዥ ነበር። አቶ ተክሉ ይህን መሰል ፌስቲቫል መዘጋጀቱ ለአገሪቷ ሰርከስ እድገት ጉልሀ ሚና እንደሚጫወት ይናገራል።
በርከት ያሉ የአፍሪካ አገራት ጋር የልምድ ልውውጥ በሚደረግበት የሰርከስ ፌስቲቫል ላይ ተጋባዥ መሆናቸው የማይገኝ እድል እንደሆነ ይገልፃል። ከዚያም ባለፈ መድረክ ላይ ስራዎችን በማቅረብ ሰርከስ ያለውን የማቀራረብ አቅም ማሳየት የሚቻልበት አንድነት፣ ሰላም የባህል ብዝሀነት እና ዓለም አቀፍ ትብብር በቀላሉ በገሀድ ማሳየት ያስችላል።
ፌስቲቫሉን ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የፍካት ሰርከስ ቡድን በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ይህን መሰል መሰናዶ ማዘጋጀቱ የሚደነቅ ነው የሚለው አቶ ተክሉ፤ በስፖንሰር ደረጃ ባለሀብቶች ገብተው ዘርፉን ሊደግፉት ይገባል ይላል። ብዙዎች በሰርከስ ላይ ያላቸው ግንዛቤ ማስተካከል እንዳለባቸውም መልዕክቱን ያስተላልፋል።
ቀልብን የሚስበው ትዕይንት
ጦር ሀይሎች በሚገኘው በመኮንኖች ክበብ ነን። በስፍራው ከተለያዩ አገራት የመጡ በርካታ የውጪ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን ታድመዋል። እጅግ ሰፊና ማራኪ እይታ ያለው ግቢ በየቀኑ እንክብካቤ እንደሚደረግለት በሚያሳብቀው ውብና አረንጓዴ ሳር ተሸፍኗል። በስፍራው አንድ ግዙፍ ድንኳን እና በርካታ ትናንሽ ጊዜያዊ ምግብ እና መጠጦች መሸጫ ድንኳኖች ተተክለዋል። ግቢው ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ሞቅ ደመቅ ብሎ የታየው በስፍራው የሰርከስ ትርኢት ስለሚቀርብ ነበር።
ሰሞኑን እየጣለ ያለው የበልግ ዝናብ መጣሁ ብሎ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ እየዘነበ ነበር። ዝግጅቱን የሚያሰናዱት የፍካት ሰርከስ ቡድን አባላት እና አስተባባሪዎች የሚጥለውን ካፊያ ተቋቁመው ትርኢቱ ወደሚታይበት ድንኳን ውስጥ እቃዎችን በማስገባት መሰናዷቸውን ቀጥለዋል። በግቢው ውስጥ ባሉ አነስተኛ ድንኳኖች ውስጥ ደግሞ በርካታ ታዳሚዎች ካፊያውን በመሸሽ ተጠልለዋል። ዝናቡ እስኪያቆም እና ዝግጅቱ እስኪጀምር ሁሉም በጉጉት ይጠብቃሉ። ብዙም ሳይቆይ የሚጥለው ዝናብ አቆመ። የበልግ ዝናብ በመሆኑም ወዲያው ብርሀን ፈነጠቀ። አስተናባሪዎቹም ሲጠበቅ የነበረውን የሰርከሰ ትርኢት መጀመሩን አበሰሩ። ሁሉም ሰው ወደ ትልቁ ድንኳን ገባ።
ለስለስ ብሎ ልምምድ በሚመስል መንገድ የጀመረው የሰርከስ ትርኢት እየሞቀ መጣ። በዝግጅቱ ላይ ተጋባዥ ከሆኑ ከስድስት የአፍሪካ አገራት መካከል በቅድሚያ ትርኢቱን ያቀረበው የኬኒያው «ሳራካሲ ትረስት የሰርከስ ቡድን» ነበር። በአፍሪካ ሙዚቃ የታጀበ ድንቅ የጅምናስቲክ እና የሰርከስ ትርኢቶችን አሳዩ። አዝናኝ እና ፈገግታን የሚያጭሩ እንቅስቃሴዎችን አቅርበው ከተመልካች ሞቅ ያለ አድናቆትን አግኝተው ከመድረክ ወረዱ። ቀጣዩ ተረኛች ደግሞ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ሁለት ታዳጊ ህፃናት እና ሁለት ወጣት የድሬዳዋ ሰርከስ ቡድን አባላት።
በድንኳኑ ውስጥ ምንም ክፍት መቀመጫ የለም። ፉጨት እና ጭብጨባ ከያቅጣጫው ይሰማል። እጅግ አስደናቂ እና በቃላት ለመግለፅ የሚከብዱ የጅምናስቲክ ትርኢቶችን ወጣት እና ታዳጊዎቹ ማቅረብ ጀመሩ። ተመልካችን ከመቀመጫው ቁጭ ብድግ የሚያሰኝ፤ አንዳንዴም የ«ይጎዱ» ይሆን ስጋት የሚያጭር፤ ጥቂቶች የታደሉት ነገር ግን ብዙዎች የሚደነቁበት ተሰጧቸውን ማሳየት ቻሉ።
የእውነትም የሰርከሰ ስፖርት ይህን ያህል የተመልካችን ቀልብ መያዝ እየቻለ፤ ድንቅ ብቃት ያላቸው ታዳጊና ወጣት ባለሙያዎች እያሉት፤ ለምን እንዲዳከም ሆነ? ለምን ትኩረት ተነፈገው የሚል የግርምት ጥያቄ ያጭራል። ሆኖም የሰርከስ ባለሙያዎቹ ዝግጅቶቻቸውን ከማቀረብ እና የተመልካችን ፍላጎት በስሜት ከማርካት አልተቆጠቡም። ከድንኳኑ ውጪ በክፍት ሜዳ ላይ ከሞዛምቢክ የመጡ «ማሪዮኔታስ ጊጋንቴስ የሰርከስ ቡድን» አባላት ገንዘብ እና ፍቅር ላይ ያተኮረ፣ በሙዚቃ የታጀበ ፣በግዙፍ አሻንጉሊቶች የደመቀ ሙዚቃዊ የዳንስ ትርኢት አሳዩ። ለታዳሚው በተለይ ለህፃናት አዝናኝ ትእይንት ቢሆንም ለሰርከስ ባለሙያዎቹ ፈታኝ እና ጥበብን የሚጠይቅ ነበር።
ዝግጅቱን ማን አሰናዳው?
የዚህ ዝግጅት ጠንሳሾች «የፍካት ሰርከስ» ቡድን አባላት ናቸው። በኢትዮጵያ ትኩረት የተነፈገውን ስፖርታዊ ትርኢት ለማሳደግ እና ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካን የሰርከስ ደረጃ ወደ ተሻለ ቦታ ለማድረስ ራዕይ ሰንቀው ተነስተዋል። የእውነትም መሰናዷቸው በዚህ ከቀጠለ አንድ ብስራት ለሰርከስ ትርዕይት አፍቃሪዎች ይዞ መምጣቱ የሚያጠራጥር አይደለም። ምክንያቱም ከጅምሩ ጥሩና ተስፋ ሰጪ ስራን ማሳየት ስለቻሉ።
የፍካት የሰርከስ ቡድን 30 አባላት እንዳሉት የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ወይዘሪት ፍፁም አበራ ትገልፃለች። በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትርኢቶችን ያቀርባል። አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ የአፍሪካን ሰርከሰ ፌስቲቫልን አሰናድቷል። ባሳለፍነው ሳምንት ለሦስት ቀናት የተካሄደው ፌስቲቫሉ ከሞሮኮ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኬኒያ፣ ከሞዛምቢክ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ጊኒ የተውጣጡ 11 የሰርከስ ቡድን አባላትን እንዲሳተፉ በማድረግ ዝግጅቱን በበላይነት መርቷል።
ፍካት የሰርከስ ቡድን አባላት መላው አፍሪካን የሚያካትት በዓይነቱ የተለየ የአፍሪካ ሰርከስ ትርኢት ፌስቲቫል በተከታታይ ለማዘጋጀት ሀሳቡ አላቸው፡፡ ባለፉት ሁለት ዝግጅቶች ላይም አላማቸው ሰምሮ የተሳካ መሰናዶ ለሰርከስ ቤተሰቡ አቅርበዋል። ፌስቲቫሉን ለመካፈል አፍሪካዊ ሰርከስ ክበቦች ወደ አዲስ አበባ መጥተው የአህጉሪቱን ህብረት፣ የከበሩ የባህል መገለጫዎቻቸውን እና የፈጠራ ችሎታቸውን ተለዋውጠዋል። ይህን መሰል ዝግጅት መቀጠሉ አፍሪካውያንን በስፖርቱ ጥላ ስር ለማቀራረብ ጥሩ አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
በ2008 ዓ.ም ሲካሄድ በሦስቱ ተከታታይ ቀናት የሰርከስ ትርዒት ለማየት ከ12ሺ በላይ ተመልካቾች በፌስቲቫሉ ላይ መገኘታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ዝግጅቱን የሚደግፉ አካላት በቀጣይ ሲፈጠሩ ከዚህ በላይ ድምቀት እንደሚኖረው አያጠራጥርም። ፌስቲቫሉ በአውሮፓ ህብረት፣ የኢትዮጵያን የባህልና ቅርስ ዕድገት በሲኒማ ፣ፎቶግራፊ እና ስነ ጥበብ የማስተዋወቅ ፈንድ ስር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ትብብር የሚደገፍ ቢሆንም ተጨማሪ አካላት መሳተፍ ይኖርባቸዋል።
በፌስቲቫሉ ላይ አስራ አንድ አፍሪካዊ የሰርከስ ክበቦች ተገኝተዋል። «ኮሎኮሎ ሰርክ አርቤን» ከሞሮኮ፤ «ዚፕ ዛፕ» ከደቡብ አፍሪካ ፤ «ሳራካሲ ትረስት» ከኬንያ፤ «ማርዮኔታስ ጅጋንቴስ» ከሞዛምቢክ እንዲሁም «ቲና ፋን» ከጊኒ ተገኝተዋል። ከኢትዮጵያ ደግሞ አዘጋጁን «ፍካት ሰርከስን» ጨምሮ ስድስት የሰርከስ ቡድኖች ተሳትፈዋል።
በዚህ ፌስቲቫል ላይ በአፍሪካ ቀንድ የመጀመሪያ የሆነው የሰርከስ ድንኳን ተመርቋል። ድንኳኑ ለሰርከስ ቡድን የእድገት፣ የጥንካሬ እና የብልፅግና ምልክት መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀዋል። ይህን ዝግጅት በተለየ መንገድ ደማቅ እና ልዩ ያደረገው ደግሞ መሰናዶው የቀረበው «የአድዋ በዓል» በኢትዮጵያውያን ተከብሮ በዋለበት እለት መሆኑ ነበር። በወቅቱ ከተለያየ አገራት ዝግጅቱን ለመታደም የመጡ የውጪ ዜጎች ከኢትዮጵያውያን ጋር የድል በአሉን እንኳን ደስ አላችሁ በመባባል አክብረውታል።
ፍካት በመኮንኖች ክበብ ካካሄደው ትርኢት ውጪ የሦስት ቀን የሰርከስ ጥበብ ልምድ ልውውጦች እና ኮንፍረንሶች በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ አድርጓል። በከተማይቱ የባህላዊና የንግድ ማዕከሎች ላይ የተለያዩ የሰርከስ ትርኢቶችም ቀርበዋል። ጅምሩ ያማረው መሰናዶ በፍካት እና በተጋባዥ የሰርከስ ቡድን አባላት ለወደፊት እድገቱ ብርሀን የፈነጠቀበት ይመስላል። ኢትዮጵያውያን አፍሪካውያንን ከባርነት ቀንበር ነፃ ለማውጣት መንገዱን እንደከፈቱት አሁንም የሰርከስን እድገት የሚያበስር ዝግጅት በተከታታይ እንደሚያቀርቡ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

አካላት ያለው ግንዛቤ ደካማ ነው። በተለያየ ቦታ ክህሎት ኖሯቸው በተበታተነ ሁኔታ የሚሰሩ ልጆችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚደረገው ሙከራ ውስን ነው። በተለይም የልምምድ ስፍራ በቀላሉ አለማግኘት እና ያሉትም ቦታዎች ምቾት የጎደላቸው መሆናቸው ዋናው እንቅፋት እየሆነ መጥቷል።
ሰርከስ በኢትዮጵያ ጅምር እና ያልጠነከረ ታሪክ ያለው ከመሆኑም በላይ ትኩረት መነፈጉ ስፖርቱ ብዙ ሳይጓዝ ጭርሱኑ እንዳይመናመን ስጋት ይፈጥራል። ሆኖም ይህ ሁኔታ እንዳይከሰት በግላቸው ጥረት የሚያደርጉ አካላት አልጠፉም። ከተመሰረተ 3 ዓመታት ያስቆጠረው የጋሞ ሰርከስ ቡድን ከ80 በላይ ልጆችን በማፍራት ኢንተርናሽናል ትርኢቶችን በማሳየት እና የተስፋ ብልጭታ በመስጠት ከሚጠቀሱት መካከል ነው። በተገቢው መንገድ ድጋፍ የሚደረግላቸው ከሆነ ለወደፊት በሰርከስ እና ጅምናስቲክ ስፖርት አገሪቷ የተሻለ ተስፋ እንደሚኖራት የሚያመላክት አቅም ያላቸው አንዳንድ የሰርከስ ቡድኖችን መጥቀስ ይቻላል።
ሰርከስ ደብረብርሃን
በኢትዮጵያ ውስጥ የሰርከስ ቡድን መስርቶ ለበርካታ ዓመታት ስፖርቱን ለማሳደግ ጥረት ከሚያደርጉት መካከል «ሰርከስ ደብረብርሀን» አንዱ ነው። የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ ባለፈው ሳምንት በፍካት የሰርከስ ቡድን የተሰናዳውን እና ለሦስት ቀናት ያህል የቆየውን የአፍሪካ ሰርከስ ፌስቲቫል በታደመበት ወቅት ተጋባዥ ከነበረው የቡድኑ ኃላፊ ጋር ጥቂት ቆይታ አድርጎ ነበር።
አቶ ተክሉ አሻገር የሰርከስ ደብረ ብርሃን ኤክሲኪዩቲቭ እና አርቲስቲክ ዳይሬክተር ነው። ቡድኑ ከኢትዮጵያዊ ባህላዊ እሴት ጋር የሰርከስ ስፖርትን አመጋግቦ የመስራት እቅድ እንዳለው ይናገራል። ሙዚቃው እና ስፖርቱ እንዲሁም የተለያዩ ትዕይንቶችን ማቀናጀት አስፈላጊ ነው ይላል። ሰርከስ ደብረብርሀን ዘመናዊ እና ሁሉን አቀፍ የኪነ ጥበብ ማዕከል የመገንባት ዓላማንም አንግቦም ይሠራል። በአገሪቱም ሆነ በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የመሆን ህልም እንዳላቸው ይገልፃል። ሆኖም ግን የሰርከስ ስፖርታዊ ትዕይንት ብዙ ፈተናዎች እያጋጠሙት እንደሆነ ይገልፃል።
ለሰርከስ ስፖርት ጎልቶ ያለመውጣት ዋንኛ እንቅፋት በወረቀት ላይ የተቀመጡ አሰራሮች ወደ ተግባር መቀየር አለመቻላቸው በሆኑን በአብነት ይጠቅሳል። አስፈላጊውን ትኩረት እና ድጋፍ ማድረግ ቢቻል ብሎም ህጉን ወደ ተግባር መቀየር ቢቻል የዓለምን መድረክ መቆጣጠር የሚችል አቅም ያላቸው ልጆች መኖራቸውን ይናገራል።
ሰርከስ ደብረብርሃን ምንም እንኳን ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ስኬቶች እንዳስመዘገበ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከ100 በላይ የምስጋና ሰርተፍኬቶች በስራዎቻቸው አግኝተዋል። ከአራት ዓመት በፊትም ከስዊድን የዓመቱ ምርጥ ፕሮዳክሽን በሚል ሽልማት ተቀብለዋል። ሰርከስ ደብረብርሃን በርካታ ሥራዎችን የሠራ ቡድን ነው። ሥራዎቻቸው ኢትዮጰያዊነትን የሚያንፀባርቁ መሆናቸው ተወዳጅ አድርጓቸዋል። በተለያየ አጋጣሚ ሲሲቲቪ፣ ቢቢሲ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን ሰጥተውታል። ይሄ ቡድን ከላይ ለማስቀመጥ እንደሞከርነው ለሁለተኛ ጊዜ የፍካት ሰርከስ ቡድን ባዘጋጀው የአፍሪካን ሰርከስ ፌስቲቫል ላይ ተጋባዥ ነበር። አቶ ተክሉ ይህን መሰል ፌስቲቫል መዘጋጀቱ ለአገሪቷ ሰርከስ እድገት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ይናገራል።
በርከት ያሉ የአፍሪካ አገራት ጋር የልምድ ልውውጥ በሚደረግበት የሰርከስ ፌስቲቫል ላይ ተጋባዥ መሆናቸው የማይገኝ እድል እንደሆነ ይገልፃል። ከዚያም ባለፈ መድረክ ላይ ሥራዎችን በማቅረብ ሰርከስ ያለውን የማቀራረብ አቅም ማሳየት የሚቻልበት አንድነት፣ ሰላም የባህል ብዝሀነት እና ዓለም አቀፍ ትብብር በቀላሉ በገሀድ ማሳየት ያስችላል።
ፌስቲቫሉን ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የፍካት ሰርከስ ቡድን በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ይህን መሰል መሰናዶ ማዘጋጀቱ የሚደነቅ ነው የሚለው አቶ ተክሉ፤ በስፖንሰር ደረጃ ባለሀብቶች ገብተው ዘርፉን ሊደግፉት ይገባል ይላል። ብዙዎች በሰርከስ ላይ ያላቸው ግንዛቤ ማስተካከል እንዳለባቸውም መልዕክቱን ያስተላልፋል።
ቀልብን የሚስበው ትዕይንት
ጦር ኃይሎች በሚገኘው በመኮንኖች ክበብ ነን። በስፍራው ከተለያዩ አገራት የመጡ በርካታ የውጪ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን ታድመዋል። እጅግ ሰፊና ማራኪ እይታ ያለው ግቢ በየቀኑ እንክብካቤ እንደሚደረግለት በሚያሳብቀው ውብና አረንጓዴ ሳር ተሸፍኗል። በስፍራው አንድ ግዙፍ ድንኳን እና በርካታ ትናንሽ ጊዜያዊ ምግብ እና መጠጦች መሸጫ ድንኳኖች ተተክለዋል። ግቢው ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ሞቅ ደመቅ ብሎ የታየው በስፍራው የሰርከስ ትርኢት ስለሚቀርብ ነበር።
ሰሞኑን እየጣለ ያለው የበልግ ዝናብ መጣሁ ብሎ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ እየዘነበ ነበር። ዝግጅቱን የሚያሰናዱት የፍካት ሰርከስ ቡድን አባላት እና አስተባባሪዎች የሚጥለውን ካፊያ ተቋቁመው ትርኢቱ ወደሚታይበት ድንኳን ውስጥ እቃዎችን በማስገባት መሰናዷቸውን ቀጥለዋል። በግቢው ውስጥ ባሉ አነስተኛ ድንኳኖች ውስጥ ደግሞ በርካታ ታዳሚዎች ካፊያውን በመሸሽ ተጠልለዋል። ዝናቡ እስኪያቆም እና ዝግጅቱ እስኪጀምር ሁሉም በጉጉት ይጠብቃሉ። ብዙም ሳይቆይ የሚጥለው ዝናብ አቆመ። የበልግ ዝናብ በመሆኑም ወዲያው ብርሀን ፈነጠቀ። አስተናባሪዎቹም ሲጠበቅ የነበረውን የሰርከስ ትርኢት መጀመሩን አበሰሩ። ሁሉም ሰው ወደ ትልቁ ድንኳን ገባ።
ለስለስ ብሎ ልምምድ በሚመስል መንገድ የጀመረው የሰርከስ ትርኢት እየሞቀ መጣ። በዝግጅቱ ላይ ተጋባዥ ከሆኑ ከስድስት የአፍሪካ አገራት መካከል በቅድሚያ ትርኢቱን ያቀረበው የኬኒያው «ሳራካሲ ትረስት የሰርከስ ቡድን» ነበር። በአፍሪካ ሙዚቃ የታጀበ ድንቅ የጅምናስቲክ እና የሰርከስ ትርኢቶችን አሳዩ። አዝናኝ እና ፈገግታን የሚያጭሩ እንቅስቃ ሴዎችን አቅርበው ከተመልካች ሞቅ ያለ አድናቆትን አግኝተው ከመድረክ ወረዱ። ቀጣዩ ተረኞች ደግሞ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ሁለት ታዳጊ ህፃናት እና ሁለት ወጣት የድሬዳዋ ሰርከስ ቡድን አባላት።
በድንኳኑ ውስጥ ምንም ክፍት መቀመጫ የለም። ፉጨት እና ጭብጨባ ከያቅጣጫው ይሰማል። እጅግ አስደናቂ እና በቃላት ለመግለፅ የሚከብዱ የጅምናስቲክ ትርኢቶችን ወጣት እና ታዳጊዎቹ ማቅረብ ጀመሩ። ተመልካችን ከመቀመጫው ቁጭ ብድግ የሚያሰኝ፤ አንዳንዴም የ«ይጎዱ» ይሆን ስጋት የሚያጭር፤ ጥቂቶች የታደሉት ነገር ግን ብዙዎች የሚደነቁበት ተሰጧቸውን ማሳየት ቻሉ።
የእውነትም የሰርከስ ስፖርት ይህን ያህል የተመልካችን ቀልብ መያዝ እየቻለ፤ ድንቅ ብቃት ያላቸው ታዳጊና ወጣት ባለሙያዎች እያሉት፤ ለምን እንዲዳከም ሆነ? ለምን ትኩረት ተነፈገው የሚል የግርምት ጥያቄ ያጭራል። ሆኖም የሰርከስ ባለሙያዎቹ ዝግጅቶቻቸውን ከማቀረብ እና የተመልካችን ፍላጎት በስሜት ከማርካት አልተቆጠቡም። ከድንኳኑ ውጪ በክፍት ሜዳ ላይ ከሞዛምቢክ የመጡ «ማሪዮኔታስ ጊጋንቴስ የሰርከስ ቡድን» አባላት ገንዘብ እና ፍቅር ላይ ያተኮረ፣ በሙዚቃ የታጀበ ፣በግዙፍ አሻንጉሊቶች የደመቀ ሙዚቃዊ የዳንስ ትርኢት አሳዩ። ለታዳሚው በተለይ ለህፃናት አዝናኝ ትዕይንት ቢሆንም ለሰርከስ ባለሙያዎቹ ፈታኝ እና ጥበብን የሚጠይቅ ነበር።
ዝግጅቱን ማን አሰናዳው?
የዚህ ዝግጅት ጠንሳሾች «የፍካት ሰርከስ» ቡድን አባላት ናቸው። በኢትዮጵያ ትኩረት የተነፈገውን ስፖርታዊ ትርኢት ለማሳደግ እና ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካን የሰርከስ ደረጃ ወደ ተሻለ ቦታ ለማድረስ ራዕይ ሰንቀው ተነስተዋል። የእውነትም መሰናዷቸው በዚህ ከቀጠለ አንድ ብስራት ለሰርከስ ትርዕይት አፍቃሪዎች ይዞ መምጣቱ የሚያጠራጥር አይደለም። ምክንያቱም ከጅምሩ ጥሩና ተስፋ ሰጪ ስራን ማሳየት ስለቻሉ።
የፍካት የሰርከስ ቡድን 30 አባላት እንዳሉት የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ወይዘሪት ፍፁም አበራ ትገልፃለች። በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትርኢቶችን ያቀርባል። አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ የአፍሪካን ሰርከስ ፌስቲቫልን አሰናድቷል። ባሳለፍነው ሳምንት ለሦስት ቀናት የተካሄደው ፌስቲቫሉ ከሞሮኮ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ፣ ከሞዛምቢክ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ጊኒ የተውጣጡ 11 የሰርከስ ቡድን አባላትን እንዲሳተፉ በማድረግ ዝግጅቱን በበላይነት መርቷል።
ፍካት የሰርከስ ቡድን አባላት መላው አፍሪካን የሚያካትት በዓይነቱ የተለየ የአፍሪካ ሰርከስ ትርኢት ፌስቲቫል በተከታታይ ለማዘጋጀት ሀሳቡ አላቸው፡፡ ባለፉት ሁለት ዝግጅቶች ላይም አላማቸው ሰምሮ የተሳካ መሰናዶ ለሰርከስ ቤተሰቡ አቅርበዋል። ፌስቲቫሉን ለመካፈል አፍሪካዊ ሰርከስ ክበቦች ወደ አዲስ አበባ መጥተው የአህጉሪቱን ህብረት፣ የከበሩ የባህል መገለጫዎቻቸውን እና የፈጠራ ችሎታቸውን ተለዋውጠዋል። ይህን መሰል ዝግጅት መቀጠሉ አፍሪካውያንን በስፖርቱ ጥላ ስር ለማቀራረብ ጥሩ አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
በ2008 ዓ.ም ሲካሄድ በሦስቱ ተከታታይ ቀናት የሰርከስ ትርዒት ለማየት ከ12ሺ በላይ ተመልካቾች በፌስቲቫሉ ላይ መገኘታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ዝግጅቱን የሚደግፉ አካላት በቀጣይ ሲፈጠሩ ከዚህ በላይ ድምቀት እንደሚኖረው አያጠራጥርም። ፌስቲቫሉ በአውሮፓ ህብረት፣ የኢትዮጵያን የባህልና ቅርስ ዕድገት በሲኒማ ፣ፎቶግራፊ እና ስነ ጥበብ የማስተዋወቅ ፈንድ ስር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ትብብር የሚደገፍ ቢሆንም ተጨማሪ አካላት መሳተፍ ይኖርባቸዋል።
በፌስቲቫሉ ላይ አስራ አንድ አፍሪካዊ የሰርከስ ክበቦች ተገኝተዋል። «ኮሎኮሎ ሰርክ አርቤን» ከሞሮኮ፤ «ዚፕ ዛፕ» ከደቡብ አፍሪካ ፤ «ሳራካሲ ትረስት» ከኬንያ፤ «ማርዮኔታስ ጅጋንቴስ» ከሞዛምቢክ እንዲሁም «ቲና ፋን» ከጊኒ ተገኝተዋል። ከኢትዮጵያ ደግሞ አዘጋጁን «ፍካት ሰርከስን» ጨምሮ ስድስት የሰርከስ ቡድኖች ተሳትፈዋል።
በዚህ ፌስቲቫል ላይ በአፍሪካ ቀንድ የመጀመሪያ የሆነው የሰርከስ ድንኳን ተመርቋል። ድንኳኑ ለሰርከስ ቡድን የእድገት፣ የጥንካሬ እና የብልፅግና ምልክት መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀዋል። ይህን ዝግጅት በተለየ መንገድ ደማቅ እና ልዩ ያደረገው ደግሞ መሰናዶው የቀረበው «የአድዋ በዓል» በኢትዮጵያውያን ተከብሮ በዋለበት እለት መሆኑ ነበር። በወቅቱ ከተለያየ አገራት ዝግጅቱን ለመታደም የመጡ የውጭ ዜጎች ከኢትዮጵያውያን ጋር የድል በአሉን እንኳን ደስ አላችሁ በመባባል አክብረውታል።
ፍካት በመኮንኖች ክበብ ካካሄደው ትርኢት ውጪ የሦስት ቀን የሰርከስ ጥበብ ልምድ ልውውጦች እና ኮንፈረንሶች በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ አድርጓል። በከተማይቱ የባህላዊና የንግድ ማዕከሎች ላይ የተለያዩ የሰርከስ ትርኢቶችም ቀርበዋል። ጅምሩ ያማረው መሰናዶ በፍካት እና በተጋባዥ የሰርከስ ቡድን አባላት ለወደፊት እድገቱ ብርሀን የፈነጠቀበት ይመስላል። ኢትዮጵያውያን አፍሪካውያንን ከባርነት ቀንበር ነፃ ለማውጣት መንገዱን እንደከፈቱት አሁንም የሰርከስን እድገት የሚያበስር ዝግጅት በተከታታይ እንደሚያቀርቡ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

ዳግም ከበደ

 

Published in ስፖርት
Sunday, 11 March 2018 01:23

የቴያትር አፍቃሪ ከሆኑ

ቲያትር መጋበዝ ይፈልጋሉ?
ቲያትር ለመጋበዝ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ይሄን ጥያቄ ይመልሱ። መቼም ነፃ ምሳ እንደሌለ ያውቃሉ። ቲያትር የማየት ልምድዎ ምን ያህል ነው? የቲያትር ወዳጅ ከሆኑ እኛ እርስዎን ይፈትናሉ ያልናቸውን ጥያቄዎች በየሳምንቱ ይዘንልዎ እንቀርባለን። ከዚያስ? ከዚያማ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር ቤት በመታየት ላይ ካሉት ቲያትሮች መካክል የመረጡትን ከወዳጅዎ ጋር እንዲመለከቱ እንጋብዝዎታለን።
የሳምንቱ ጥያቄ
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ ማለትም ህዳር 3/ 1948ዓ.ም የታየው ቴአትር ማን ይባላል?
ማሳሰቢያ
ከላይ የጠየቅነውን ጥያቄ በዚህ ስልክ ቁጥር 011-126-43-26 ወይም eletesenbet1 @ gmail.com ቀድመው ለመለሱ 5 (አምሥት) ሰዎች ሁለት ሁለት የመግቢያ ካርድ የምንሰጥ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን። በእስካሁኑ ጥያቄዎች ለተሳ ተፋችሁ ምስጋናችን ከልብ ነው። በየሳምንቱ በዚህ ጥበባዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ተሳታፊ በመሆን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ «የዕለተ ሰንበት» የመዝናኛ፣ የባህልና የኪነጥበብ ወዳጅ በመሆን የምትፈ ልጉትን ቲያትር ተጋበዙልን። አሥተያየትና የኪነጥበብ ዘገባ ጥቆማችሁን አድርሱን።

Published in መዝናኛ
Sunday, 11 March 2018 01:22

የደመወዝ ሰሞን

የሆነውስ ሆነና ዛሬ ቀን ስንት ነው? እኮ መጋቢት ከገባ ሁለት ቀን ሆነው? ሰሞነ ሁዳዴ ሊገባ ምን ቀረው ታዲያ? ሀብታም እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ በል! ሰሞነ ሁዳዴ የተባለው የያዝነው የሁዳዴ ጾም እንዳይመስልህ (ደግሞ እኮ መገጣጠሙ)፡፡ ሰሞነ ሁዳዴ የተባለው የደመወዝ ሰሞን ያልሆነው የወሩ አጋማሽ አካባቢ ነው፡፡ ‹‹ለመሆኑ የወሩ መጨረሻ አካባቢ ምን ይባላል?›› ካልከኝ ሰሞነ ፍስሃ፣ ሰሞነ ፋሲካ ይሉታል(ምን ይሉታል ነው እንለዋለን ልበል እንጂ)
ቆይ ግን ትክክለኛው የደመወዝ ቀን ከመቼ እስከ መቼ ያለው ነው? እንግዲህ ይሄ እንደየ መስሪያቤቱና እንደየአካባቢው ሁኔታ ይለያያል (ትልቅ ጉዳይ የምተነትን አስመሰልኩት አይደል?)፡፡ ለነገሩ ከዚህ በላይ ምን አለ?
አንዳንድ መስሪያ ቤት ከ23 እና 24 አካባቢ ጀምሮ ደመወዝ ይከፈላል፤ አንዳንድ መስሪያቤት ደግሞ ቀጣዩ ወር እስከሚገባ ሁሉ ሊዘገይ ይችላል፡፡ ስለዚህ ዛሬ ስለ ሰሞነ ደመወዝ ብናወራ ጉዳዩ ወቅታዊ ነው ማለት ነው (ዛሬ የሚቀበልም ይኖራል)፡፡ እንዲያውም ዛሬ ደመወዝ ለምትቀበሉ ምክር ነገር አለችኝ፡፡ ይሄን ምክር ዝም ብየ ከሜዳ ተነስቼ የጻፍኩት አይደለም፡፡ ለዓመታት ያህል ደመወዝ በማባከን ያከበትኩትን ልምድ መነሻ በማድረግ ነው (ልብ በሉ በማባከንም ልምድ ማካፈል ይቻላል)፡፡ለማንኛውም ምክሩ ወደ መጨረሻ አካባቢ ነው (ደግሞ ዘላችሁ መጨረሻ ላይ እንዳትሄዱ)፡፡
ያዝ እንግዲህ! መቼስ የደመወዝ ሰሞን አይደል? አቤት እኮ የደመወዝ ሰሞን ያለ ግርግር፡፡ እኔ እኮ ግርም የሚለኝ የዚያን ሰሞን ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ የ «ኤቲኤም» ማሽኖች ሁሉ ቀልባቸው መጥፋቱ ነው፡፡ አንዳንዴ ንግድ ባንክ ‹‹ብር ገብቶልሃል›› ብሎ የላከልህን መልዕክት «ኤቲኤም» ላይ ሄደህ ስታይ ‹‹ባክህ ውሸት ነው›› በማለት ተስፋህ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ይቸልስበታል፡፡ በኋላ ግን ነገሩ ሲጣራ ቅርጥፍ አድርጎ የዋሸው ራሱ ማሽኑ ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ያስቀኛል፡፡ ብዙ ብር አውጥቼ እኮ ነው፤ ሌላ ቀን የቀረችዋን ለማውጣት ስጠይቀው ድሮ የነበረውን ጨምሮ ‹‹ይህን ያህል ብር አለህ›› ይለኛል፡፡ እንዴ! ማን ጨመረልኝ ብየ ለማውጣት ሳዝዘው ‹‹ባክህ ስቀልድ ነው›› ይለኛል፡፡
የንግድ ባንክ «ኤቲኤም» ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጀመራት የዜማ ግብዣ ተመችታኛለች፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ… ሁሌም ሁሌም… የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ›› ይላል፡፡ እንዴት ከኋላዬ ሰው ቆሞ እጨፍራለሁ ብዬ እንጂ ዜማዋን ግን እዚያው ቆሜ እየሰማሁ ወዝ ወዝ ማለት ያምረኝ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው የደመወዝ ሰሞን ነው፡፡ ሌላ ጊዜ መንገድ ላይ «ኤቲኤም» ሳገኝ የተኳረፍን ይመስል የጎሪጥ ነው የማየው፡፡ ያ የካርዱ ማስገቢያ ላይ ያለው አረንጓዴ መብራት ቦግ ቦግ ቦግ ሲል ሳየው እንዴት እንደምቀና፡፡ ብር ባይኖረኝ ራሱ የ«ኤቲኤም» ማሽኑ ተበላሽቶ ካየሁት ያናድደኛል፡፡
በነገራችን ላይ ባንኮች ግን ሀብታምና ድሃ ለይተው አያውቁም ማለት ነው? ደመወዝ ሲገባ በገባው ብር መጠን የሎቶ ቁጥር በስልኬ ይልኩልኛል፡፡ የባንክ ሠራተኞች እንደነገሩኝ ዕጣውን ለመጠበቅ ብሩ መውጣት የለበትም (እኔ እንደሆንኩ የገባ ዕለት ነው የምጀምረው)፡፡ ገና አንዴ እንዳወጣሁ ‹‹አንዱ የሎቶ ቁጥር ከሸፈ›› ይለኛል፡፡ አሁንም ሳወጣ ‹‹አሁንም ሌላኛው ከሸፈ›› ይለኛል፡፡ ቆይ ግን ምንም ብር ሳያወጣ ዓመት ሙሉ ይጠብቀኛል መስሎት ነበር? ‹‹እኔ የምሞት ዛሬ ማታ፤ ገብስ የሚደርሰው ለፍልሰታ›› አለች አሉ፡፡ ገና ለገና መኪና አገኛለሁ ብዬ እንዴት ልቆይ ነው?
እንዴት ነው የደመወዝ ሰሞን? ስልካችሁ የሚሴጅ ድምጽ ባሰማ ቁጥር አትደነግጡም? ውይ ይሄ በ80 ምናምን የሚጀምር ቁጥር እንዴት ደሜን እንደሚያፈላው! እኔ የCBE ሚሴጅ መስሎኝ ሰፍ ብዬ ሳይ ‹‹የፍቅር ጓደኛ ይፈልጋሉ? መኪና ይፈልጋሉ? ቤት ይፈልጋሉ? ምክር ይፈልጋሉ?...›› ኧረ ምን የማይባል ነገር አለ! CBE ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያበሳጨኝ ነው፡፡ ብር ሲገባልኝ ቶሎ መልዕክቱን አይልክልኝም (ኧረ ጭራሽ የሚተውበት ጊዜም አለ) ብር ሳወጣ ግን እዚያው ኤቲኤም ማሽኑ ሥር እያለሁ ነው ‹‹አውጥተሃል›› የሚለኝ፡፡ ይሄንማ ባይነግረኝስ እስተዋለሁ እንዴ!
ወይ የደመወዝ ሰሞን ብዙ አስወራን እኮ፡፡ በወሩ አጋማሽ ሰሞን ቢሆን እኮ ይህን ሁሉ አላወራም ነበር፡፡ የዚያን ሰሞንማ ምን አደርጋለሁ መሰላችሁ? ያለኝ ብር በ«ኤቲኤም» መውጣት ስለማይችል የባንክ ደብተር ይዤ ነው የምሄደው፡፡ አቤት እዚያ እንዴት እንደማፍር! ሰው እንዴት 50 ብር ለማውጣት ሠራተኞችን ሥራ ያስፈታል? እኔማ ‹‹ለዚህ ነው እንዴ ሥራ ያስፈታኸኝ?›› ይሉኛል እያልኩ አይን አይናቸውን ነው የማየው (ደግነቱ ብለውኝ አያውቁም)፡፡ ደግሞ እኮ የባንክ ሠራተኞች ምሥጢር ጠባቂነታቸው ደስ ሲል! ያቺን 50 ብር በደብተሩ ውስጥ አድርገው ነው የሚሰጡኝ፡፡ ማየት የለ፣ መቁጠር የለ፣ ተቀብዬ ዞር ነው፡፡
የምር ግን ባንክ ቤት ውስጥ ከሀብታም ጋር መሰለፍ እንዴት እንደሚሰለቸኝ! በዚያ ላይ ጣጣቸው አያልቅ፡፡ እኔ አንድ ወይም ሁለት መቶ ብር ለማውጣት ቦርሳ ሙሉ ብር እስከሚቆጠር ድረስ መቆም አለብኝ እንዴ? እሺ ብር ቆጠራውስ ይሁን፤ የባንክ ደብተራቸው ላይ የሚሞላው ነገርስ ምን ሆኖ ነው ያን ያህል የሚያቆየው?
የምክሯን ነገር ረሳኋት አይደል? ‹‹ምክርና ቡጢ ለሰጪው ቀላል ነው›› አሉ፤ ለመሆኑ ይህን ምክር እኔ ተግባራዊ አድርጌው ይሆን? እዚህ ላይ አንድ ቀልድ ትዝ አለኝ፡፡ ሰውየው ‹‹ሚሊየነር ለመሆን የሚያግዙ ዘዴዎች›› የሚል መጽሐፍ ጻፈ አሉ፡፡ ከዚያማ ማሳተሚያ ገንዘብ አጥቶ ሳይታተም ቀረ፡፡ ለነገሩ ምክር እኮ የግድ መካሪው የተገበረው ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ለምሳሌ የሲጋራን ጎጂነት ለማስተማር የማያጨስ ሰው ብቻ መሆን የለበትም፡፡ እንዲያውም ጉዳቱን በደንብ የሚያውቀው ተጠቃሚው ሲሆን ነው፡፡ ቆይ ግን ይህን ያህል ማግባቢያ የኔ ምክር ምን ሆኖ ይሆን? በአንድ ቃል ሲጠቃለል «አታባክን!»
የምር ግን የደመወዝ ሰሞን ሀብታም የሆንን የሚመስለን ለምንድነው? የማያልቅ የሚመስለን ለምንድነው? ኧረ ብሩም እኮ ችግር አለበት፡፡ የተገዛው ነገር ሳይታወቅ የብሩ ማለቅ ብቻ ነው የሚታወቀው፡፡ እንዲያው አናውቀው ብለን እንጂ እሱስ ሳይገዙበት አላለቀም፡፡ ዋናው ነገር ያ የተገዛው ነገር ምንድነው ነው?
በነገራችን ላይ እኔን ያስቸገረኝ ‹‹ደግሞ ለአሥር ብር፣ ደግሞ ለሃምሳ ብር፣ ደግሞ ለመቶ ብር›› የሚባል ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ ልብስ ልገዛ አስቤ ‹‹እዚህ ቦታ የተሻለ ነው›› ሲሉኝ ‹‹ኤዲያ! ደግሞ ለመቶ ብር ብዬ፣ ደግሞ ለሁለት መቶ ብር ብዬ›› እያልኩ በቀላሉ የማገኘውን እገዛለሁ፡፡ አስቡት ስንፍና እንዴት እንደበደለኝ፡፡ መቶና ሁለት መቶ ብር አሁን ለኔ ቀላል ነበር?
ምግብ ቤት ስገባ ራሱ ያላሰብኩትን ነው በልቼ የምወጣው፡፡ መጀመሪያ የምገባው ሻይ በዳቦ ለመብላት ነው፡፡ ቀጥሎ ሀሳቤን ወደ ፍርፍር እቀይረዋለሁ፡፡ አሁንም የምግብ ዝርዝር ካየሁ በኋላ እንደገና ወደ ጥብስ ወይም ዱለት (በፍስክ ወቅት ማለቴ ነው) እቀይረዋለሁ፡፡ አስቡት እንግዲህ! በሁለትና በሦስት ብር የታሰበው ቁርስ በሀምሳና በስልሳ ብር ይጠናቀቃል፤ ኧረ ቆይ ገና ነው፡፡ ምግቡ ሲመጣ አስተናግጇ መጥታ ‹‹የሚጠጣ ነገር ምን ይምጣ?›› ትለኛለች፡፡ ሰው ምናለ አቅሙን አውቆ የብርጭቆ ውሃ ቢያዝዝ? ለነገሩ እዚህ ላይ እንኳን የምግብ ቤቶችም እጅ አለበት፡፡ ‹‹የቧንቧ ውሃ›› የለም ሊሉም ይችላሉ፡፡ መቼም ሰው ምግብ እየበላ የሚጠጣ ነገር ሳይዝ አይሆንም፡፡
ሆኖም ግን ጥፋቱን ሙሉ በሙሉ እነርሱ ላይ ብቻ አልዘፈዝፍም፤ የኔም እጅ አለበት፡፡ ቢያንስ ቢያንስ የታሸገ ውሃ ማዘዝ አለብኝ፡፡ ይሄ ደግሞ ለጤናም ለኢኮኖሚም ጠቃሚ ነው፡፡ እንዲህ መሆን ሲገባው ግን ሚሪንዳ፣ ኮካ፣ ላዝዝ እችላለሁ፡፡ ኧረ አለፍ ካለ እነ ስም አይጠሬንም ላዝዝ እችላለሁ፡፡
ሌላ የደመወዝ ሰሞን ትዝታ አለ? ‹‹አንተው እንደጀምርክ ጨርሰው እንጂ!›› አላችሁኝ? ዋናውን አይደል እንዴ እንዲያውስ የተውነው፡፡ እስኪ ‹‹ደሞዝ ሲወጣ›› ብሎ ያልተበደረ አለ ይሆን? የዱቤ ዕቃ ያልገዛ አለ ይሆን? የጎረቤት ባለሱቅ ሸሽተህ መንገድ ቀይረህ አታውቅም? እዚህ ላይም ምክር አለኝ (ምነዋ እንደ ሽማግሌ ምክር አበዛሁ) ይሄም በአጭሩ ሲጠቃለል «የዱቤ ዕቃ አትግዛ!»
የብድሯ ነገርስ? ብድር እንዲያውም የዱቤ ዕቃ ከመግዛት የባሰ ነው፡፡ ዱቤ እኮ ቢያንስ በዕቃው ታስታውሰዋለህ፡፡ ብድር ግን ምኑም ሳይታወቅ የመመለሱ ጊዜ ነው የሚደብረው፡፡ እዚህም ላይ የራሴን ተሞክሮ ላካፍላችሁ፡፡ አልበዛም እንዴ ግን? ገንዘብ አባካኝ እኔ፣ የዱቤ ዕቃ ገዢ እኔ፣ ብድር ተበዳሪ እኔ፤ ይህን ያህል ምን ዕዳ አለብኝ? ትቸዋለሁ ከራስህ ተማር!

ዋለልኝ አየለ

Published in መዝናኛ

ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ አንድ የቱሪስቶች ማረፊያ ሆቴል ቁጭ ብዬ ወዳጄን እየጠበኩ ነው። ከዚህ ጓደኛዬ ጋር በቀትር ለመገናኘት የተጣደፍነው በአፍሪካውያን በተለይም በኢትዮጵያውያን ፍቅር ከተለከፉ አንድ ጀርመናዊ የእድሜ ባለፀጋ ጋር ተገናኝተን በጋራ ለመጨዋወት ነበር። እኚህ ባለ ታሪክ ከእድሜያቸው ግማሽ በላይ በተካኑበት የሙያ መስክ እና በበጎ ፍቃደኝነት በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ጠይም ከጥቁር፤ ነጭ ከቀይ ዳማ ሳይለዩ፤ ያላቸውን ሳይሰስቱ እንካችሁ ብለዋል። እኛም ይህን ተገንዝበን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ግማሽ ምዕተ ዓመት በአፍሪካ አህጉር በመቆየት የቋጠሩትን ታሪክ አፍታተን ለናንተ ለአንባቢዎቻችን ለማካፈል የህይወት እንዲህ ናት ዓምዳችን እንግዳ አደረግናቸው። (ሁሉንም የዘመን አቆጣጠር በአውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር መሆኑን ልብ ይሏል)

ማንፍሬድ ማን ናቸው?
ከሠላሳ አገራት አንድ መቶ ሚሊዮን ሰዎችን ያሳተፈው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አብቅቶ ጥቁሩ ሰማይ በሰላም ብርሀን ለመተካት ዳርዳር የሚልበት ዘመን ነው። የጎርጎሮሳውያኑ 1944። በተለይ የዓለም ታላላቅ አገራት በጠንካራ ክንዱ እና በቁንጮ ጭራቅነቱ በሚታወቀው አዶልፍ ሂትለር የሚመራውን የናዚ ስርዓት ለመገርሰስ ያለ የሌለ ሀይላቸው እየተጠቀሙ ነው። ታዲያ እናት ልጇን አትውጠው ትደብቅበት አጥታ በምትቅበዘበዝበት ዘመን አንድ ተስፈኛ ህፃን በጀርመኗ በርሊን ከተማ ተወለደ። የ74 ዓመቱ የእድሜ ባለፀጋ ሚስተር ማንፍሬድ ሴት።
የዓለሙን ጩሀት በቅጡ የማይረዳው ህፃን ኑሯቸውን በዝቅተኛ ገቢ ከሚደጉሙት ከአናፂ አባቱ እና ከቤት እመቤቷ እናቱ ጋር በጀርመን በርሊን የኑሮ ውጣ ውረድን «ሀ» ብሎ ጀመረ። በወቅቱ የጀርመኑ ናዚ የአገሩን ዜጎች «ዓለም ላይ ካሉ የሰው ዘሮች የተለዩ እና ምርጦች» እያለ ቢያሞካሻቸውም 8 ቤተሰብ ያቀፈውን ጎጆ ግን በችግር ከመቆራመድ፤ብሎም በድህነት ጠንካራ ክንድ ከመደቆስ አልዳነም ነበር። የዚህ ዳፋ በቀጥታ ለማንፍሬድ ደርሶታል። ማንፍሬድ የናዚ ጀርመን ተገርስሶ ሲወድቅ የ9 ወር ህፃን ነበር። ስርዓቱን በደንብ ማየት ባይችልም የአዶልፍ ሂትለር ጦስ ይዞት የመጣው የኢኮኖሚ ድቀት ግን በቀጥታ አርፎበታል። ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ ባዶ እግሩን ነበር። ከትምህርት ቤት ውጪም የበርሊንን ጎዳናዎች በባዶ እግሩ ሊዳስሳቸው ይገደድ ነበር።
ምንም እንኳን የማንፍሬድ ቤተሰቦች ኑሯቸውን የሚመሩት የቤቱ አባወራ በአናፂነት ሥራ ተሰማርቶ በሚያገኛት አነስተኛ ገቢ እየተደጎሙ ቢሆንም ሁሉም ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ከመግባት እና ዘመናዊ ትምህርትን ከመከታተል አላገዳቸውም ነበር። ማንፍሬድም እድሜው ለመኖር እውቀትን የሚጠይቅበት ወቅት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በበርሊን በሚገኝ የመንግሥት ትምህርት ቤት ገብቶ መከታተል ጀመረ። ጎበዝ ተማሪ ካልሆነ የአባቱን የአናፂነት መዶሻ መረከቡ ስለማይቀር የግዴታ በትምህርቱ ጠንካራ መሆን እንዳለበትም በልጅነት አዕምሮው ጠንቅቆ ተረድቶ ነበር።
ህይወት ፈተና የበዛባት የተወሳሰበ የዳንቴል ክር መሆኗንም ገና በጨቅላ እድሜው ነበር የተገነዘበው። እነዚህ የልጅነት ፈተናዎች ደግሞ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በጥሩ ሁኔታ እንዲከታተል የኋላ ደጀን ሆኑት። በኋላም መክሊቱ ወደሆነው የግብርና ሙያ ላይ እንዲሰማራ ብሎም የህይወት ጉዞው ፈር እንዲይዝ መንገዱን ወለል አድርገው ከፈቱለት። ማንፍሬድ ዘመናዊ ገበሬ ለመሆን ሳይንሱን ለማጥናት ፍላጎት አደረበት። በትሮፒካል አግሪካልቸር የትምህርት ክፍል የግብርና ሙያን አጠና። ሙያውን የበለጠ ለማዳበርም ሲዊዘርላንድ እና አሜሪካን አገር ተጉዟል።
እውቀት በተግባር ሊፈተን
እኔና ወዳጄ ከጀርመናዊው አዛውንት ጋር ተቀምጠን እየተጨዋወትን ነው። ያሳለፋቸውን የህይወት የከፍታ እና የዝቅታ ወቅቶች ሲያወጉን ረጋ ካለ አንደበታቸው ጋር ተደምሮ የልጅነት ህይወታቸውን በችግር አሀዱ ብለው ቢጀምሩም በነበራቸው ጥንካሬ እና ብሩህ ተስፋ ታግዘው ህይወትን ድል እንደነሷት ያሳብቅባቸዋል። ማንፍሬድ ወጋቸውን ቀጥለዋል። ከኛ የሚጠበቀው አንዳንድ ጥያቄዎች እያነሱ ፈር ማስያዘ ነበር። የልጅነታቸውን ዘመን ለመግለፅ አክብሮታችን አንደተጠበቀ ሆኖ «አንቱታው» ስለከበደን ትረካችንን አንተ እያልን እንቀጥል።
ማንፍሬድ አሁን የልጅነት ዘመኑን ጨርሶ ብዙ ትግል እና ጥንካሬን ወደሚጠይቀው የወጣትነት ህይወት ገብቷል። የከፍተኛ ትምህርቱን በሚፈልገው የሙያ መስክ አጠናቋል። ሥራ መግባት ይኖርበታል። ሆኖም ቀጥታ በጀርመን የግብርና ሥራ ውስጥ መሰማራት አልፈለገም። ይልቁንም ወገኖቹን ጥሎ ወደማያውቃት የአፍሪካ ምድር ለመጓዝ ልቡ ተነሳሳ። ምክንያቱ ደግሞ አንድ እና አንድ ነበር። ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ የተፈጥሮ ፍላጎቱ መሆኑ ነው። እርሱ በልጅነቱ ማጣትን እና ችግርን በሚገባ አይቶታል። ስለዚህ አሁን ላይ ያለውን እውቀት ተጠቅሞ እራሱን ማዳን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም መድረስ እንዳለበት የወጣትነት እድሜው አስገንዝቦታል። ለዚህ ደግሞ አንድ አማራጭ መጠቀም ይኖርበታል። በጎ ፍቃደኛ መሆን።
ወቅቱ 1966 ነው። የአፍሪካ አገራት በጊዜው በተለይም በግብርና ላይ ሙያዊ ድጋፍን ከምንጊዜውም በላይ ይፈልጉ ነበር። እርሱ ደግሞ ሁለት ነገሮች ነበሩት። አንድ እውቀት፤ ሁለትም ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን ለመርዳት የሚሻ ቅን ፍላጎት። ስለዚህ የምዕራብ ጀርመን መንግሥት ጋር ቀርቦ በበጎ ፍቃደኝነት ማገልገል እንደሚፈልግ አሳወቀ። ፍላጎቱን የተረዱ አካላትም ማንፍሬድ ልቡ ወደሻተው የሙያ መስክ እንዲሰማራ መንገዱን ጠረጉለት። ንፁህ ልብ ያለው ማንፍሬድ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ አፍሪካ ምድር ለመጓዝ ተነሳ። በወቅቱ የጀርመን መንግሥት በአንዳንድ አገራት ውስጥ በግብርናው ዘርፍ ላይ ድጋፍ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ያስተዳድር ነበር። ማንፍሬድም በነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ ባለሙያ ሆኖ ነበር የተመደበው።
ቀዳሚ ማረፊያ ኢትዮጵያ
ጊዜው 1966 ። የጀርመን መንግሥት ማንፍሬድን «የሚኒስትሪ ኦፍ ኮሚኒቲ ዴቨሎፕመንት» የጀመረው ፕሮጀክት ላይ ተሳታፊ እንዲሆን መደበው። «የተቀደሰች እና ኩሩ ህዝብ ያላት አገር» እያለ ወደሚጠራት ኢትዮጵያ ገባ። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አፍሪካ አገር ሲመጣ የመጀመሪያ ስራውን በዚህቺው አገር ጀመረ። ኢትዮጵያ እንደገባም በሰሜን ሸዋ ክፍለ አገር ማጀቴ በሚባል ቦታ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት ላይ ተመደበ።
ማንፍሬድ ወቅቱን ልክ ዛሬ ላይ እንደሆነ ሁሉ ሁሉንም ነገር ያስታውሳል። «በእስራኤል አገር የሚገኙ የምርጥ ዘር ዶሮዎችን በቀበሌዋ እያመጣን ከአራት የሥራ አጋሮቼ ጋር በኢንኩቤተር እናባዛ ነበር» ይላል። በአካባቢው በሚገኙ ስምንት መንደሮች ውስጥ እነዚህን የዶሮ ዝርያዎች በማሰራጨት አርሶአደሩ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ነበር የበጎ ፍቃደኛው ወጣት ባልደረቦች የሚሰሩት። በቀበሌው የሚረቡ ዶሮዎችን እና የሚገኘውን እንቁላልም አዲስ አበባ ድረስ በማምጣት ለገበያ ያቀርቡ ነበር። አርሶአደሮችን በሙያ ማገዝ እና ዘመናዊ የግብርና ሳይንስን ማስተማር በጎ ፍቃደኛ ሆነው የኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢን አቋርጠው ለመጡት የነ ማንፍሬድ ቡድን አባላት የመንፈስ እርካታን የሚያጎናፅፍ ሀይል ነበረው።
ለዚህ ወጣት ደግሞ ከሁሉም በበለጠ አገሩ ውስጥ ያልተመለከተውን ወግ፣ ባሀል እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንዲመለከት እረዳው። ዓለምን በጀርመን ዓይን ሲመለከት ማደጉ ሌላ ውበ እሴቶች ያሏቸው አገሮች መኖራቸውን እንዳይገነዘብ አድርጎት ነበር። አሁን በእድሜ መግፋቱ አስረሱት እንጂ አማረኛ ቋንቋንም አቀላጥፎ መናገር ችሎ ነበር። አሁንም ቢሆን ሰላምታ ለመለዋወጥ የሚረዱ ጥቂት መግባቢያዎች ያውቃል።
ማንፍሬድ የኢትዮጵያን ምድር በረገጠበት የአገሪቷ ዜጎቸ ቁጥር 17 ሚሊዮን ይደርሱ ነበር። በወቅቱ ኢትዮጵያ አፄ ኃይለስላሴ አገዛዝ ስር ትተዳደር ነበር። በጊዜው የነበረው ማህበረሰብ ፈሪሃ አግዚአብሄር ያለው እና እጅግ ሰው አክባሪ መሆኑን ከሚመሰክሩ የውጪ አገር ዜጎች መካከል ቀዳሚው ማንፍሬድ እና ጓደኞቻቸው ነበሩ ቢባል ማጋነን አይሆንም።
በጀርመን መንግሥት ድጎማ የሚደረግለት ፕሮጀክትም በተደጋጋሚ ጊዜ በንጉሱ ምስጋና በማግኘቱም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተደጋጋሚ ሽፋን አግኝቷል። በማንፍሬድ እይታ የፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን መውረር በሁሉም ዘርፍ ላይ አገራዊ ቅኝት ባለው መልኩ ብልፅግና እንዳይመጣ እንቅፋት ቢሆንም አንፃራዊ በሆነ መንገድ የንጉሱ ስርዓት የፈራረሰውን ኢትዮጵያዊ ማንነት ለመገንባት ጥረት የሚያደርጉበት ጊዜ ነበር።
አገሩን የኔ ሙያዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል በማለት ወደ ማጀቴ ያቀናው ማንፍሬድ እስከ 1969 ድረስ በግብርና በተለይም በዶሮ እርባታ ሥራ ላይ ቆየ። ከላይ እንደጠቀስነውም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ከማረግ ባለፈ አርሶአደሮች ፕሮጀክቱ ደግፏቸው ምርቶቻቸውን በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እንዲያቀርቡ አስቻላቸው። ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ነገሮች እየተቀያየሩ በመምጣታቸው ፕሮጀክቱ ተቋርጦ ወደሌላኛው የአገሪቷ ክፍል እንዲዘዋወር ተደረገ።
በሌላኛው የአገሪቷ ክፍል በሆለታ ከተማ የጀርመን መንግሥት በሚደግፈው ቮኬሽናል ሴንተር እና የጤና ጉዳዮች ላይ መስራት ጀመረ። ሙያው ግብርና ቢሆንም በጎ ፍቃደኛ በመሆኑ የመጀመሪያው ፕሮጀክት ሲቋረጥ ወደ አገራቸው አልተመለሰም። ይልቁንም የጀርመን መንግሥት በመደባቸው ሆለታ ላይ ከኢትዮጵያውያን ባህል ጋር ተዛምዶ ሲያገለግል ቆየ። አሁን የያኔው ወጣቱ ማንፍሬድ በዛሬው አዛውንት ማንፍሬድ ተተክቷል። ትረካችንም በአክብሮት ተለውጧል።
መለያየት ሞት ነው
ከ1966 ጀምሮ በኢትዮጵያ ለአራት ዓመታት የቆዩት ማንፍሬድ በአገሪቷ ጀርመኖች የጀመሩት ፕሮጀክት በመጠናቀቁ ወደሌላ አፍሪካ አገር ለመዘዋወር ተገደዱ። በቶሎ ከአገሪቷ ወግ እና ባህል ጋር ለተላመዱት የያኔው ጠንካራ ወጣት ውሳኔው እጅግ አስቸጋሪ ነበር። ሆኖም በኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆየት ምንም አይነት አማራጭ ስላልነበር ውሳኔውን ማክበር ነበረባቸው። በዚህም ጋና እና ቡርኪናፋሶ ወደሚያዋስኗት የምዕራብ አፍሪካዋ ቶጎ አቀኑ። በዚያ ለአራት ዓመታት በተመሳሳይ ፕሮጀከት ላይ ከጂቲ ዜድ ጋር ሰሩ።
ማንፍሬድ ኢትዮጵያን ከረገጡ በኋላ አፍሪካ ልትለቃቸው አልቻለችም። ለእረፍት እና ቤተሰብ ጥየቃ አንዳንዴ ወደ ጀርመን ቢጓዙም የእድሜያቸውን እኩሌታ ግን በዚህችው አህጉር ውስጥ እንዲያሳልፉ ተገደዱ። ከቶጎ በኋላ ወደሌላኛዋ አፍሪካዊት አገር አይቮሪኮስት በተመሳሳይ ፕሮጀክት ተጉዘው ለተወሰኑ ዓመታት አሳለፉ። ረጅሙን የሥራ ጊዜያቸውን የተሻማችው ግን ኮንጎ ነበረች። ለ17 ዓመታት በአገሪቷ ጂቲ ዜድ በሚሰራው «የኮሚውኒቲ ዴቨሎፕመንት» ሥራዎች ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ቅንነት በተሞላበት መንገድ አገለገሉ። እአአ ከ1992 እስከ 94 ባለው ጊዜ ደግሞ ማንፍሬድ ሱዳን እና ሩዋንዳ ነበሩ። በሁለቱ አገራት በነበሩ የእርስ በርስ ጦርነቶች ላይ የአደጋ ጊዜ እርዳታን ከመንግስታቸው ጋር በመሆን ያቀርቡ ነበር። በተለይ ሩዋንዳ ውስጥ የተከሰተው የዘር ጭፍጨፋ መንስኤ እና ያስከተለውን አሰቃቂ ገዳት በቅርበት ተከታትለዋል።
ሩዋንዳን በማንፍሬድ ዓይን
በእ.አ.አ 1994 በሩዋንዳ አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ጎሳዎች ላይ የተካሄደውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ማስታወስ ለማንፍሬድ «የደረቀ ቁስልን» እንደመነካካት ነው የሚሰማቸው። ጉዳዩን ወደኋላ መለስ ብለው ሲያስተውሉት የሰው ልጅ መጥፎ ጎኑ ቁልጭ ብሎ የታየበት እንደነበር ይናገራሉ። በዚያን ወቅት በክቡር የሰው ልጆች ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ዘርን መሰረት አድርጎ በህዝቦች መካከል ተነስቷል የሚል አመለካከትም የላቸውም። በዋናነት ፖለቲካና የቋንቋ ልዩነት ተደራርበው የፈጠሩት ልዩነት እልቂት ነው የሚል እምነት አላቸው። «francophone» በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንዲሁም «anglophone» በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት እንጂ ለብዙ ዘመናት በጥብቅ ቁርኝት ሲኖሩ በነበሩት ሁቱና ቱትሲ የቂም በቀል ተነሳሽነት አለመሆኑን ይናገራሉ
ማንፍሬድ ሩዋንዳ በነበሩበት ጊዜ የአውሮፓውያንን ጣልቃ ገብነት በአፍሪካ አገራት በተለይም በሩዋንዳ መኖሩን ታዝበዋል። የፈረንሳይ ጣልቃ ገብነትም በሁለቱ የሩዋንዳ ጎሳዎች መካከል ቂም እና ጥላቻ እንዲኖር ጉልህ ድርሻ መጫወቱን ተመልክተዋል። በቆይታቸውም ሁለት ጊዜ ለሞት ከሚያበቃ አደጋ ተርፈዋል። ለ51 ዓመታት በአፍሪካ ምድር ላይ በበጎ ፍቃደኝነት በተለያዩ አገራት ሲሰሩ እንደ ሩዋንዳ ዘርን መሰረት ያደረገ ግጭት አጋጥሟቸው አያውቅም ነበር።
ኢትዮጵያን መናፈቅ
ከጀርመናዊው አዛውንት ጋር የምናደርገው ጨዋታ ቀጥሏል። ካኪ ቁምጣ፣ ቲሸርት እና እጅጌ የሌለው ጃኬት የደረቡት የእድሜ ባለፀጋ በራሳቸው ላይ የኃይለስላሴ ምስልና ባንዲራ ያለበት ኮፍያ አድርገዋል። የቀድሞውን ንጉስ አፄ ኃይለስላሴ ምስልን ለማድረግ ለምን መረጡ? ጃማይካዊ አሊያም ጥቁር አፍሪካዊ ቢሆኑ ብዙም የሚያስገርም አይመስልም ነበር። ነገር ግን እሳቸው ለኢትዮጵያ ከሌሎች አፍሪካ አገራት በተለየ ፍቅር አላቸው።
በአገሪቷ ጥቂት ዓመታትን የቆዩ ቢሆንም ህብረተሰቡ ባለው ልዩ ስብእና፣ ሃይማኖተኝነት እና ጠንካራ አገራዊ ስሜት የተለየ ፍቅር እንዲያድርባቸው አድርጓል። ኢትዮጵያ ውስጥ በቆዩበት አራት ዓመታት ከንጉስ አፄ ኃይለስላሴ ጋር የመገናኘት አጋጣሚው ተፈጥሮላቸዋል። «ወቅቱ 1967 ነበር። ባዘጋጀነው የግብርና ኤግዚቢሽን ላይ ንጉሱ ተገኝተው ነበር። እጅግ ማራኪ ስብእና ያላቸው እና ግርማ ሞገሳቸውም የሚያስፈራ ነበር። ትሁት እና ለአገራቸው ዜጎች አሳቢ እንደነበሩም በቆይታዬ ተግንዝቤያለሁ» ይላሉ። ስለ አጼ ኃይለስላሴ አንስተው አይጠግቡም።
በወቅቱ የህዝብ ቁጥሩ አነስተኛ ነበር። የንጉሱ ስርዓት ከጣሊያን የቅኝ ግዛት ሙከራ እና አስከፊ ጦርነት ውስጥ ዜጎቹን በመሰረተ ልማት፣በትምህርት እና በስልጣኔ አንድ እርምጃ ወደፊት ለመውሰድ ሲያደርጉት የነበረውን ትጋት አዛውንቱ ጀርመናዊ በስፍራው ተገኝተው መታዘባቸውን ይመሰክራሉ። «እርሳቸው ታላቅ ንጉሥ ነበሩ። ከንግስት ኤልሳቤጥ ቀጥሎ ጀርመንን ሲጎበኙ ከፍተኛ አቀባበል አግኝተዋል» በማለት ንጉስ ለአገራቸው እና ለዓለም ሰላም ጠበቃ የቆሙ ብሎም ኢትዮጵያን እንድትበለፅግ በፍፁም ልባቸው የታገሉ መሆኑን ያምናሉ። በወቅቱ የነበረውን የውጪ ተፅኖ በመገንዘብም «እግርህን የምትዘረጋው በአልጋህ እርዝማኔ ልክ ነው» በማለት አፄ ኃይለ ስላሴ የሰሩትን ሥራ ያሞካሻሉ።
በአዛውንቱ ጀርመናዊ ሚስተር ማንፍሬድ አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ከሌሎች አገራት ባህል፣ ሀይማኖት እና ታሪክ ጋር ማነፃፀር ፍፁም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም የአገሪቷ ባህል፣ ወግ እና ታሪክ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ፣ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ስርዓቱ ጥንታዊነቱን የጠበቀ ነው። በተለይ በገጠራማው አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለራሳቸውም ሆነ ለሰው ልጅ ሁሉ ክብር ያላቸው ናቸው። በተለያየ ዓለማት የሚኖሩ አገራት የቅርብ ጊዜ ታሪክ ያላቸው ከመሆኑም በላይ እርስ በርስ የሚመሳሰል እሴቶች አሏቸው።
ማንፍሬድ ከ47 ዓመት በኋላ ኢትዮጵያን በድጋሚ ለማየት እድሉን አግኝተዋል። አሁን አገሪቷ እርሳቸው ከሚያውቋትም በላይ በብዙ መንገድ ተለውጣለች። የህዝብ ቁጥሩ ጨምሯል። ስልጣኔ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ ተስፏፍቷል። እርሳቸው የሚያውቋት አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ቀድሞ ከነበራቸው ገፅታ ፍፁም ተቀይረዋል። ነገር ግን ይሄ ሁሉ በቂ አይደለም ባይ ናቸው። ኢትዮጵያ እንዲሁም ሁሉም የአፍሪካ አገራት በተሻለ ፍጥነት ወደ እድገት እና ስልጣኔ ለመጓዝ ከፈለጉ ከዚህም በላይ በትብብር መስራት ይኖርባቸዋል።
ዓለም ላይ ነገሮች በፍጥነት ይቀያየራሉ። አንድን ባህል እና ማንነት ሳይበረዝ መጠበቅ አስቸጋሪ ነው። ሚስተር ማንፍሬድ ከአራት አስርት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያንም ቀድሞ በሚያውቋት ቦታ አላገኟትም። በተለይ በአዳዲስ የውጪ ተፅኖ እና የተበረዘ ማንነትን ተመልክተዋል። ነገር ግን ሁሉም ትክክል አይደለም የሚል እምነት የላቸውም። ለዚህ ደግሞ እንደምሳሌ የምትሆናቸው የትውልድ አገራቸው ጀርመን ነች። በጀርመን ከዚህ ቀደም በተለይ በእምነት በኩል የሙስሊም ማህበረሰብ አልነበረም። አሁን ግን ከአገሪቷ አጠቃላይ ዜጎች 8ነጥብ 2በመቶ የሚሆኑቱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው።
«ዓለም ላይ ብዙ ነገር ይቀየራል። ይሄን ማስቆም አይቻልም። ባህል ከባህል ጋር ይበረዛል። ሀይማኖቶች ይስፋፋሉ። ይሄ ጤናማ ለውጥ ነው» የሚሉት ሚስተር ማንፍሬድ እንደ እሳቸው አስተውሎት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ አገራት የእድገት እና ለስልጣኔ እንቅፋት፤ ለባህል መበረዝ እና ለማንነት ግጭት መጋለጥ ዋንኛው ምክንያት «ኒዮ ኮሎኒያሊዝም» ወይም ደግሞ በኢንቨስትመንት እና በንግድ ትስስር የቀድሞው ቅኝ ገዥ አገራት ከአህጉሪቱ ጋር በሚፈጥሩት ጣልቃ ገብነት ነው። ስለዚህ ሳይወለዱባት ሁሌም የሚናፍቋት ኢትዮጵያ ከዚህ ማነቆ አምልጣ ሉአላዊነቷ ሳይደፈር የስልጣኔ ጫፍ ላይ ለመውጣት መታገል አለባት የሚል ቀና ተግሳፅ ይሰጣሉ።
በተለይ ከአጼ ምኒልክ ብዙ ነገር መረዳት ይቻላል። ማንፍሬድ አጼ ምኒልክ ለዓለም ህዝብ «ኢትዮጵያዊነት» ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሚገባ ያስመሰከሩ መሆናቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ማንም አገር በቀላሉ መጥቶ ኢትዮጵያ ላይ ልሰልጥንም ሆነ ሀያል ልሁን ማለት እንደማይችል አሳይተዋል። ይሄ ደግሞ አጼ ምኒልክ በወቅቱ ፋሽስት ጣሊያንን ሲገረስሱ የተፈጠረ ብቻ ሳይሆን ለሦስት ሺ ዘመን የቆየ ነው። በጀርመናዊው አዛውንት እይታ አሁን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታትም በዚሁ ቆራጥ የራስ ማንነት መታገል ያስፈልጋል።
ጡረታ የፈጠረው እፎይታ
ሚስተር ማንፍሬድ 51 ዓመታት በተለያዩ የአፍሪካ አገራት በበጎ ፍቃደኝነት ተዘዋውረው ሰርተዋል። አሁን እረፍት አስፈልጓቸዋል። በዘመናቸው ተግተው በመስራታቸው እዚህ ፀጋ ላይ ደርሰዋል። ጡረታ በመውጣታቸው የሚወዱትን የኢትዮጵያ አየር በእርጋታ እንዲኮመኩሙ እድሉን ከፍቶላቸዋል። አሁን መጣሁ መጣሁ እያለ የሚያስፈራራቸው እርጅና ባይጫጫናቸው ኖሮ መላው ኢትዮጵያን በድጋሚ ዞረው መመልከት ይፈልጉ ነበር። ነገር ግን የአዲስ አበባ እምብርት የሆነችው ፒያሳ ላይ ከትመው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የጉዞ መቆጣጠሪያ መሳሪያቸውን አንገታቸው ላይ አጥልቀው በእግራቸው ዞር ዞር ማለታቸው አልቀረም።
በቀን 6 ኪሎ ሜትር በእግር ይጓዛሉ። በመንገድ ላይ «ሰዎችን ማውራት ያስደስተኛል» ይላሉ። በተለይ የኢትዮጵያውያን ልዩ ፈገግታና ትህትና የተሞላበት ሰላምታ ሚስተር ማንፍሬድ ልብ ውስጥ ተሰንቅሮ ቀርቷል። ታዲያ ከስኬታማ የሥራ ዘመን በኋላ አዕምሮን ዘና ለማድረግ ሁለተኛ አገራቸውን ቢመርጡ ማን ይፈርድባቸዋል።
የማንፍሬድ 5 ወንድም እና እህቶች አሁን በህይወት የሉም። እርሳቸው የሁሉም ታናሽ ነበሩ። ነገር ግን የፊታቸው ገፅታ ላይ የብቸኝነት ስሜት አይነበብም። አፍሪካ ውስጥ በሰሩባቸው ዓመታት ብዙ ቤተሰብ አፍርተዋል። በሄዱበት የሚቀበላቸው አያጡም። ተግባቢ እና ተጫዋች መሆናቸው ደግሞ በሰዎች እንዲከበቡ ያደርጋቸዋል። ቀሪ ዘመናቸውን ያለፏቸውን ፈተናዎች እና የስኬቶች መንገዶች ከወዳጆቻቸው ጋር እያወጉ ይኖራሉ። ከዚህ በላይ ሀሴት ከየት ይገኛል?
የማንፍሬድ የህይወት መንገድ
ባለፉት ዓመታት የሥራን ክቡርነት ተገንዝበው በጥንካሬ እና በቅን ፍላጎት ሰርተዋል። ሁሉም ሰው ሊደርስበት የሚገባው ግብ በህይወቱ ሊኖረው ይገባል የሚል እምነት አላቸው። ከምንም ነገር በላይ ግን ላለፉት 51 ዓመታት በአፍሪካ ውስጥ ሲቆዩ የተገነዘቡት የሰላም እና የአንድነትን ጥቅምን ነው። አፍሪካ እስካሁንም ድረስ በስልጣኔ ወደኋላ ልትቀር የቻለችው ይህን መገንዘብ የሚችሉ መሪዎች እና ተከታዮች በማጣቷ ነው። የውጪ ተፅእኖን አስወግዶ አንድነትን ማጠንከር ከተቻለ ኃያላን የደረሱበት ስፍራ ላይ መድረስ ቀላል ነው።
ማንፍሬድ ለጊዜው በሩዋንዳ በሚገኝ አነስተኛ መንደር ውስጥ መቀመጫቸውን አድርገዋል። የአካባቢውን ማህበረሰብ ንቃተ ህሊና ሊጨምር ይችላል ብለው ያመኑበትን ድጋፍ በአቅማቸው ያደርጋሉ። ከጡረታ በኋላ ግን ቋሚ የግል ሥራ ላይ የመሰማራት ፍላጎት የላቸውም። በጉብዝናቸው ዘመን ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ ሰርተውበታል። ሁሉም ሰው ህይወቱን በዚህ መልክ መምራት አለበት የሚል ጠንካራ እምነት አላቸው። ሌላኛው ጠንካራ የህይወት ፍልስፍናቸው «ለመስራት አልኖርም እምሰራው ግን ለመኖር ነው» ይላሉ። ይህም ደግሞ በዘመናቸው ሁሉ ጠንካራና ሥራ ወዳድ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። በጥሩ ሁኔታ ለመኖር ከተፈለገ ሥራን መናቅ የለብንም ይላሉ።
ማንፍሬድ ቀለል ባለ መንገድ ህይወትን ማጣጣም ችለዋል። «ለመኖር ጠንክሬ ብሰራም ግን በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ እምብዛም ተማርኬ አላውቅም» ይላሉ። አሰስ ገሰስ ሳያበዙ በቀላሉ መንገድ ህይወትን መኖር ይቻላል የሚል ጠንካራ እምነት አላቸው። አሁን ተጨማሪ 10 እና 15 ዓመታትን በህይወት መኖር ይመኛሉ። «ዕድሜዬ ገፍቷል። አምላክ ወደኔ ና እስኪለኝ የጡረታ ጊዜዬን በደስታ ማሳለፍ እፈልጋለሁ» ያሉት ማንፍሬድ በተለይ ከግማሽ በላይ የሆነውን ዕድሜያቸውን ከምንም በላይ እንደ ቤተሰቤ አየዋለሁ ያሉትን የአፍሪካ ህዝብ በበጎ ፍቃደኝነት እያገለገሉ በፍቅር ማሳለፋቸው የስኬት ማማ ላይ አስቀምጧቸዋል።

ዳግም ከበደ

 

Published in ማህበራዊ
Sunday, 11 March 2018 01:17

የአለላዋ ምድር

ከአዲስ አበባ ምስራቅ አቅጣጫ 500ኪሎሜትሮችን ቢጓዙ የእራሳቸው የተዋቡ ቀለማት ያላቸውን ሐረሪዎችን ያገኟቸዋል። የሐረሪ ክልል መዲና ሐረር በአብዛኛው በስነህንፃ ውበቶቿ በተለይም በጀጉል ግንብ ታዋቂ ብትሆንም የክልሉ ባህላዊ አልባሳት፣ መገልገያ ዕቃዎች እና በቤቶች ውስጥ ያረፉትን የዕደ ጥበብ ውጤቶች ደግሞ ከአዕምሮ ሊጠፋ የማይችል ትዝታን የመፍጠር አቅም አላቸው። 

ሐረሪዎች ጥንታዊ ዕደጥበብን ከቤተሰብ እየተቀባበሉ ያደጉ ናቸው:: የሐረሪ የዕደ ጥበብ ውጤቶች ለቤት ማስጌጫነት እና ለውበት ማድመቂያነት ይውላሉ:: በተለይ የስፌት ሙያ የሌላት ሴት ቤቷን ለማስጌጥ እና ባህሏን ለማክበር ያላት እድል ዝቅተኛ በመሆኑ ከዘመድ አዝማድም ሆነ ከጎረቤት ሙያውን ለመልመድ ከፍተኛ ጥረት ታደርጋለች::
«የእደጥበብ ውጤቶች በተለይም የስፌት እና የማስዋቢያ እቃዎች በአንድ አካባቢ ውስጥ እንደባህል ተወስዶ የሚለመደው ማህበረሰቡ በአንድ ቦታ ተረጋግቶ መኖር ከጀመረ በኋላ ነው» ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች:: ምክንያቱም የማስጌጫ እና የቅንጦት እቃዎችን ጥበብ ማስፋፋት የሚቻለው ለማህበረሰቡ አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ጉዳዮችን ማሟላት ከተቻለ በኋላ መሆኑን እንደ ማስረጃነት ያቀርባሉ:: ይህ አባባልም ሐረሪዎች የስፌት ጥበባቸውን እና ቤት ማስጌጫዎቻቸውን መስራት የጀመሩት ዘመናዊነት ከገባቸው እና ዘመናዊነትን ከተላመዱ ቆየት ያለ ጊዜ እንዳስቆጠሩ ማሳያ ይሆናል::
የክልሉ ርዕሰ መዲናም ሐረር ከፍተኛ የስልጣኔ እድገት ደረጃ ላይ በደረሰችበት በ16ኛው ክፍለ ዘመን ላይ የምስራቅ አፍሪካ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት እና የንግድ ማዕከል በመሆን ግልጋሎት ሰጥታለች፡፡ ይህም የበርካታ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶች እንዲሁም ረቂቅ የእጅ ጥበብ ያረፈባቸው መገልገያዎች ባለቤት እንድትሆን አድርጓታል የሚሉ የታሪክ ምሁራንም በርካታ ናቸው፡፡ ከቤት አሰራሩ ጀምሮ እስከ ምንጣፋቸው ድረስ ለአይን በሚማርክ መልኩ ማዋቀርን ተክነውበታል::
ከሐረሪዎች መኖሪያ ብንነሳ የእጅ ጥበብ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው መረዳት ይቻላል:: የሐረሪዎች ባህላዊ ቤት «ጌይ ጋር» ይባላል:: ቤቱን የአገሩን ባህል የማያውቅ ጥበበኛ ካልሆነ በቀር ማንኛውም የግንባታ ባለሙያ አሳምሮ ሊሰራው ያይቸገራል:: በሐረሪዎች «ጌይ» ማለት ከተማ ሲሆን «ጋር» ማለት ደግሞ ቤት ነው:: ከፍቺው የምንረዳው «ጌይጋር» ማለት የከተማ ቤት እንደማለት ይሆናል:: ከተሜዎቹ ሐረሬዎች ደግሞ ቤቶቻቸው ግድግዳ ላይ በርከት ብለው የሚንጠለጠሉ የዕደጥበብ ወጤቶችን እንደማስጌጫነት ይጠቀማሉ::
የክልሉ ነዋሪ አቶ መሃመድ ካሊድ እንደሚሉት፤ በወይን ጠጅ፣ ቀይ፣ አረንጓዴ እና ሌሎችም ህብረ ቀለማት የተጌጡ ሰፌዶች፣ ኢራዝ ሙዳይ እና ሌሎች የስፌት አይነቶችም በሐረሪዎች ቤት የማይጠፉ የዕደጥበብ ውጤቶች ናቸው:: ሁሉም የየእራሳቸው አገልግሎት ቢኖራቸውም ከአገልግሎታቸው በተጨማሪ ግን ለውበት መገለጫነት እንዲያገለግሉ በሚል በስነውበት ደረጃቸው ከፍ እንዲል ተደርጎ ይዘጋጃሉ:: በመሆኑም ለዳቦ እና ቆሎ ማቅረቢያነት የሚውል የስፌት እቃ እንኳን በግድግዳ ላይ ቢቀመጥ ጀርባው ውብ ሆኖ ለሰው መታየት አለበትና በሐረሬዎች እጅ በጥልቅ ዲዛይን እንዲዋብ መደረጉ አይቀሬ ነው::
በአሁኑ ወቅት የሐረሪዎች የስፌቶቻቸው ቅርፅ እና ስነ ውበት የላቀ ደረጃ ከመድረሱም ባሻገር የተለያዩ ጎብኚዎችን ቀልብ መሳብ እየቻለ ይገኛል:: በተለያዩ ቀለማት ደምቀው እና ተውበው የተሰናዱት የዕደ ጥበብ ውጤቶችን ለተመለከተም ሐረሪዎች ምን ያህል የቀለማትን ህብር የመጠቀም ችሎታቸው የላቀ መሆኑን እንዲረዳ ያስገድደዋል::
ዕደ ጥበባቱ ለሐረሪዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አላቸው:: ምክንያቱም አንድም ለመገልገያነት ሲጠቅማቸው በሌላ በኩል ደግሞ ለጌጥ እና ማስዋቢያነት ጥቅም ላይ ይውላል:: ከዚህ ባለፈ ግን ለህብረተሰቡ ተምሳሌትነት እና ምልክት ሆኖ በመቅረብ እያስተዋወቃቸው ይገኛል::
ከእደ ጥበብ ውጤቶቻቸው መካከል በውበቱ ትልቁን ስፍራ የሚይዘው አለላ ነው:: አለላ የሐረሪ ሴቶች አሳምረው የሚሰፉት የሳሎን ሞሰብ አይነት የዕደጥበብ ውጤት ነው:: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል የህዝብ ግንኙነት እና ዓለም አቀፍ ዳይሬከተሯ ወይዘሮ ሰብለ አበበ እንደሚሉት፣ የሐረሪዎች ሞሰብ ከሌሎቹ የአገሪቷ ክፍል ከሚሰሩት የተለየ በመሆኑ ተፈላጊነቱ እየጨመረ ይገኛል:: በህብረቀለማት ከማጌጡም በላይ ደግሞ አለላው አክርማ ለሚሰኝ ከሳር ዝርያ መሰራቱ ከሌሎቹ ተመራጭ እና የተለየ ለመሆኑ አይነተኛ ሚና አበርክቷል::
በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚዘጋጁት መሶብ እና ሙዳዮች ከሰበዝ ወይም ስንደዶ ከተባለ የሳር ዝርያ የሚዘጋጁ ናቸው:: ነገር ግን የሐረሪዎቹ አለላ በጥንቃቄ በተዘጋጁ የገብስ ተረፈ ምርት የሚሰሩ በመሆኑ በዋጋም ውድ ናቸው:: በሐረሪ ባለሙያ ሴት የተሰፋ አለላ በአሁኑ ወቅት ከአራት እና አምስት ሺ ብር በላይ ያወጣል:: የማህበረሰቡ ዲዛይንም ተወዳጅ እና ለአይን የሚማርክ በመሆኑ በቤት ውስጥ እንደ ማስጌጫነትም ያገለግላል:: በመሆኑም ይህን የዕደጥበብ ውጤት በሰፊው በማስተዋወቅ ሴቶች በገቢ ደረጃ አቅማቸውን የሚያሳድጉበት የሥራ መስክ ማድረግ ያስፈልጋል::
ሌላው የሐረሪዎች የእጅ ጥበብ ያረፈባቸው መታወቂያቸው የባላዊ አልባሳት ናቸው:: «ጠይ ኢራዝ» የሚባለው ባህላዊ ልብስ በጥቁር ጨርቅ ላይ በተለያዩ ዲዛይኖች የሚዋበው ነው:: የባህል ልብሱ ልክ እንደ ነጭ የሐበሻ የአገር ባህል ልብስ የእራሱ የሆኑ ባለሙያዎች አማካኝነት በአግባቡ ይዘጋጃል:: ነገር ግን የሚለብሱት ያገቡ እና የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናችው:: በአንዳንድ የኢትዮጵያ ከልሎች ላይ ያላገቡ ሰዎችን እና ያገቡ ሰዎች ለመለየት የጸጉር አቆራረጣቸው እንደሚመሰክረው ሁሉ በሐረሪዎች ዘንድም የትዳር እና የእድሜ ሁኔታን ለመለያየት የሚያገለግል የባህል አልባሳት ሆኖ እየተዘወተረ ይገኛል::
ልጃገረዶች እና ሙሽሮች ደግሞ «አጥላስ» የተሰኘውን ባህላዊ ልብስ ይዋቡበታል:: ባህላዊ ልብሱ ደማቅ ቀለማትን የያዘ ሲሆን በአብዛኛው ጊዜም ለስላሳ ሆኖ በአረንጓዴ እና ቀይ ቀለማት ባላቸው ጨርቆች ይዘጋጃል:: በተለይ በጥልቅ የጥልፍ ዲዛይን እና በአበባ ቅርጽ የተጠለፉ ወርቃማ ክሮች ያሉበት ልብስ በመሆኑ በሰርግ ወቅት ሙሽሪት እና ሚዜዎቿ ተውበው ህዝብ ፊት ሲቀርቡበት ሐረሪዎች ውብ ባህል እንዳላቸው ምስክር የመሆን አቅም አለው::
ወንዶቹ በ«ጌይ ከሎይታ» ወይም ነጭ ኮፍያ መዋብ ከፈለጉ በባህላቸው የተዘጋጀ ቆብ ይዘጋጅላቸዋል:: ኮፍያዎቹ በብዛት ከክር የሚሰሩትን እና ለየት ባለ ጥበብ የተዘጋጁ ሲሆኑ ወንዶችም ከሐይማኖትም ሆነ ከባህል አንፃር በጭንቅላታቸው ላይ በማድረግ በከተማዋ ሲዘዋወሩ ይታያሉ:: ኮፍያዎቹ በማህበረሰቡ የዕደጥበብ ባለሙያዎች የሚዘጋጁ ናቸው:: የተለያየ አሰራር ያላቸው ሲሆን «አሩዘ ከይሎታ»/የሙሽራ ኮፍያ/፣ «ነጪሕ ከሎይታ»/ነጭ ኮፍያ/ እና ሌሎች ስያሜዎች ተሰጥቷቸዋል:: አንዱን በጥልቅ የጥልፍ ጥበብ የተሰራ ኮፍያ ለመስራት ሳምንታት ወይም አንድ ወር ሊፈጅ ይችላል:: በተለይ የሙሽራ ኮፍያ ከሆነ በጥንቃቄ የሚሰራ በመሆኑ እስከ አራት ሺ ብር ድረስ ሊያወጣ ይችላል:: በዘርፉ የተሰማሩ የሐረሪ ሴቶችም ጥሩ ገቢ የሚያገኙበት የዕደጥበብ ውጤት ነው::
ከአለላ እና አልባሳት ወጣ ስንል ደግሞ የተለያዩ የእጅ እና የአንገት ጌጦችን በሐረሪ የዕደጥበብ ውጤቶች ውስጥ እናገኛለን:: አንደኛው «ቀርማ» የሚባለው ሲሆን በግንባር ጫፍና በፀጉር መካከል ላይ የሚደረግ ውብ ጌጥ ነው:: ጌጡ በተለያዩ ሐይማኖታዊ ባህላት፣ ባህላዊ ዝግጅቶች እና በሰርግ ወቅት ይደረጋል:: «ቀርማ» ከብር ማዕድን በቀጭኑ ተዘጋጅቶ በተለያዩ ገበያዎች ላይ ለሽያጭ ይቀርባል::
ሌላው ደግሞ በውበቱ እና ግርማ ሞገሱ ከሌሎች ጌጦች ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጠው «ወቅሪ» የተባለው ጌጥ ነው:: ጌጡ በክብ ንብ ቀፎ አምሳያ የሚዘጋጅ ከብር የተሰራ የአንገት ላይ ማጌጫ በመሆን ያገለግላል:: አሰራሩ በአንድ በኩል የሚከፈት እና የሚዘጋ ሲሆን አንገት ላይ በሚያርፍበት ጊዜም በውስጡ የተለያዩ መኳኳያዎችን እና መሃረብ ለመያዝ አመቺ ነው:: በመሆኑም ሴቶች በጭፈራ እና ጭብጨባ ወቅት በቀላሉ ከደረታቸው ላይ ወሰደው ውበታቸውን እንዲያገኙ ይረዳል::
«ወቅሪ» ከብር የተሰራ ጌጥ ቢሆንም የተለያዩ ተንጠልጣይ ዲዛይኖች የሚኖሩት በመሆኑ በግምት ከ150 ግራም በላይ የብር ማዕድን ሊፈጅ ይችላል:: ይህ ውድ የዕደ ጥበብ ውጤትም ታዲያ የሚዘጋጀው በጥበበኞቹ ሐረሪዎች ነው:: ተዝቆ ከማያልቀው የሐረሪዎች የዕደጥበብ ውጤቶች መካከል እነሆ የተወሰኑትን አቀረብንላችሁ እንጂ በርካታ ናቸው:: እኛም ይህን ጥበብ ወደ ሃብትነት በመቀየር የሴቶቹን አቅም ማሳደግ ይገባል እንላለን::

ጌትነት ተስፋማርያም

 

 

Published in ማህበራዊ
Sunday, 11 March 2018 01:15

ውበታችን እንደባህላችን

ከቀናት በፊት የሴቶች ቀን ተከብሯል፤ በአገር ደረጃ ለ42ኛ ጊዜ። አውቀነውም ይሁን ሳናውቀው ይህን ቀን አስበንና አክብረን የማሳለፍ ባህልን ይዘናል። የአከባበር ባህላችን ምን ይመስላል? ይህ ጥናት ሳይፈልግ አይቀርም። ባይሆን በሴቶች ቀን መከበር መነሻነት ከባህል ጋር በተያያዘ አንድ ሌላ ጉዳይ ላነሳ ወደድኩ፤ ስለውበት።

የሃይማኖት ሰዎች ፈጣሪ ሁሉን ውብ አድርጎ እንደሠራ ቅዱስ መጽሐፍን ጠቅሰው ይናገራሉ። በእርግጥም ተፈጥሮ ለህጻን ልጅ የእናት ወተት እንደምታዘጋጅ ለዓይንም ውበትን ለማስቃኘት ሰስታ እንደማታውቅ ልብ ስንል እናውቃለን። በዙሪያችን የሰው ልጅ በራሱ ጊዜ በራሱ ስህተት ካጠፋቸው ነገሮች ውጪ በተፈጥሮ ሁሉም ነገር ውብ ነው።
አየሩ፣ሰማዩ፣ደመናው፣ ዝናቡ፣ አፈሩ፣ እፅዋቱ፣ ቀለሙ፣ ውሃው፣ ሜዳው፣ ተራራው፣ ማለዳው፣ ምሽቱ፣ ፀሐይዋ፣ ከዋክብት፣ ጨረቃ...እስቲ ከተፈጥሮ አንድ የሚያስቀይም ነገር ጥሩ? ወዲህ መለስ እንበል፤ ወደ ሰው ልጅ ውበት። ለሰው ተብለው የተፈጠሩና የከበቡት ፍጥረታት ሁሉ እንዲህ ደምቀውና አምረው ከታዩን የሰው ልጅማ ምንኛ ውብ ነው!
ሴቶች ደግሞ የበለጠ ለውበታቸው ይጨነቃሉ ይባላል። ይህን ውሸት ነው የሚል የለም። ሰኔ 2008ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በታተመ «ባህል ወቱሪዝም» የተሰኘ መጽሔት ላይ «ሴቶችና የውበት ማድመቂያቸው ድሮና ዘንድሮ» በሚል ርዕስ ከተጻፈ ጽሑፍ የሚከተለው ይገኛል።
«ለቁንጅና በዓለም ላይ ያልተደረገና ያልተሞከረ ጥረት የለም። የፈረንሳይ ንግስት ኢውጀኒ ገላዋን በታጠበች ቁጥር ለሰውነቷ ቆዳ ማሳመሪያና ማለስለሻ አንዳንድ ቅርጫት ኢንጆሪ ያስፈልጋት ነበር። ቤድፎርድ የተባለች የሆላንድ ወይዘሮ ደግሞ ገላዋን ስትታጠብ አንድ ደርዘን ጠርሙስ ወተት አዘጋጅታ ከውሃ ጋር በመቀየጥ ለሰውነቷ የተለየ ውበት ለመስጠት ትጥር እንደነበር ይነገርላታል።»
ሁሉም የሰው ልጅ ለውበቱ የሚጨነቅ ቢሆንም ሴቶች የበለጠ ለውበታቸው ስሱ ናቸው። በአንጻሩ ደግሞ ወንዶች በሴቷ ፊት የሚታይ ጀግንነታቸው ብቻውን ውበታቸው እንደሆነ ሲቆጠር እናያለን። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በጦር ጀግንነት ፊትአውራሪዎች በበዙባት አገር። ሥነጽሑፋዊ ሥራዎቻችንም የወንዶችን ሳይሆን የሴቶችን ውበት ነው በብዛት አድምቀውና አድንቀው የሚጽፉት። የሴት ጸሐፍያን በብዛት አለመኖር ነው ምክንያቱ ካልተባለ በቀር። ጉዳዩን ወደአገራችን ሰብሰብ አድርገን እናምጣውና ወደተነሳንበት ጉዳይ ዘልቀን እንግባ።
ድሮም ዘንድሮም ሴቶች ውበታቸውን ለመጠበቅና ለማድመቅ ብዙ ነገር ያደርጋሉ። «ሲያጌጡ ይመላለጡ» እስኪባል ድረስ ወደ መስክ ወጥተው በሚታዩበት አጋጣሚ ውበታቸውን አጉልተው ለማሳየትም የማያደርጉት ጥረት የለም። «ቆንጆ» መባል ለራስ ያለን ግምት ከፍ ለማድረግ ይረዳል። አሁን ላይ በራስ መተማመን ይጨምራል እንደሚባለው። በተጓዳኝ በቃ! በሌሎች ዐይን ውስጥ ውብ ሆኖ መታየት ደስ ይላል። ለዚህ ታዲያ የውበት መጠበቂያና መዋቢያ ጌጣጌጥና ስራስሮች ብዙ ናቸው።
ሴቶችም ውበታቸውን ለማድመቅ ሲሉ ከጸጉራቸው ጀምረው እስከ እግር ጥፍራቸው ድረስ አንድም ቦታ በስህተት ሳያመልጣቸው ብዙ ነገሮችን ያደርጋሉ። እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦች ይነሳሉ፤ በአንድ በኩል ያለውን ውበት እንዳለ ማድመቅና መንከባከብ ሲሆን፤ በሌላ በኩል በተለያዩ ጌጣጌጦች ጎልቶ መታየት መቻል ነው። ብዙዎች ያለውን ተንከባክቦ በማቆየት ይስማማሉ፤ «ለአበባ ምን ሌላ ጌጥ ያስፈልገዋል? እንዲሁ የሚያምር ነገር ሌላ ማሳመሪያ ምን ይሠራለታል?» ይላሉ።
ያም ተባለ ይህ ሴቶች ዛሬም በፊትም ውበታቸው ላይ አይደራደሩም። ሁሏም በአቅሟ፤ በምትችለው መጠን አምራና ደምቃ ለመታየት ትጥራለች፤ ታደርገዋለችም። ይህም እንደምትኖርበት አካባቢና አገር ባህል ይለያያል። እኛም ዛሬ መቀንደብ፣ መኳል፣ የፊት ቀለሞችን መቀባት፣ ንቅሳት፣ ስቲም መግባት፣ ጸጉርን በእሳት መተኮስ፣ የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ከፍ ያሉ ጫማዎችን መጫማት፣ ጉርድ ቀሚስና ሱሪዎችን መልበስ ሳይመጡ በፊት የራሳችን የሆነ የውበት አጠባበቅና መጠበቂያ መንገዶች ነበሩን።
«በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ» አርኖ ሚሼል ዳባዲ /ራስ ሚካኤል ዳባዲ/ በተባለ ሰው በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተጽፎ በገነት አየለ የተተረጎመ መጽሐፍ ነው። ይህም ጸሐፊው ከ1836 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እስከ 1962 ዓ.ም ያደረገውን ቆይታ አስቃኝቶበታል። ከቅኝቱም «ባህልና የሰውነት አቋም» በሚል ርዕስ በምዕራፍ ሁለት ከአለባበስ ጀምሮ ስለኢትዮጵያውያን ውበትና ባህል አንስቷል።
«ወይዛዝርት ከጥጥ የተሠራ ሸማ ይለብሳሉ። ቀሚሱን ሰፊና ረዘም አድርገው ይሰፉትና ከክንዱ ላይ ሰፋ ብሎ ወርዶ ወደታች እጅጌው ላይ ጠበቅ ብሎ ያልቃል። ከላዩ ላይ ነጠላቸውን ከነብነብ ብለው ይለብሱታል።...የባላባት ወገን የሆኑ ሴት ወይዛዝርት ቀሚሱ መሬት እስኪጠርግ ዘርፈፍ እንዲል ያደርጉታል። ኮረዶች ደግሞ ቀሚሱን ብቻ ያለነጠላ ሊለብሱት ይችላሉ።
«ወይዛዝርት አደባባይ የወጡ እንደሆነ ራሳቸውን ይሸፍኑና ከዚያም ነጠላቸውን ዝቅ በማድረግ ዓይናቸው ብቻ እንዲታይ አድርገው ይከና ነቡታል።...የሹማምንት ሚስቶች በነጠላቸው ላይ በጥልፍ ወይም በተዋበ ጨሌ የተጌጠ በርኖስ ይደርባሉ። ሁሉም በሹሩባ ያጌጣሉ።
«...ተጊጦ የተሠራ ወለባ ጸጉራቸው ላይ ሰካ ማድረግ ይወዳሉ። ወለባው እንደየአቅማቸው ከእንጨት፣ ከጎሽ ቀንድ ወይም ከእንስሳት ጥርስ የተሠራ ይሆናል። ጣቶቻቸው ላይ ቀጠን ብለው የተሠሩ ብዙ የብር ቀለበቶች ያደርጋሉ።...ለጆ ሮቻቸው እንጥልጥል ወይም ልጥፍ ጉትቻ፣ ለእግሮቻቸው የብር አልቦ፣ ለእጆቻቸው አምባር እንዲሁም ከፍ ብሎ ክንድ ላይ የሚውል ሌላ አምባር በማድረግ ይዋባሉ። ሰውነታቸው መልካም መዓዛ እንዲኖረው ልዩ ልዩ ስራ-ስርና ብርጉድ በማጨስ ይታጠኑታል። አንዳንዶች በጉትቻ ፋንታ ቅርንፉድ ጆሯቸው ላይ ይሰካሉ። ዓይናቸውን ደግሞ ስር ኩል ይኳሉታል።» እያለ ይቀጥላል።
ይህ እንግዲህ ጸሐፊው በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ ያየውና የታዘበው ነው። በዚህ ታድያ ውበትን ለመጠበቅ ከውጪ የሚገቡ ቁሶችን መጠቀም ሳንጀምር በፊት እንዲህ በአገር ነገር፤ በቅርብ በሚገኘውም ሁሉ ውበትን የሚያደምቁና የሚጠብቁ ሴቶች እንደነበሩ የሚነግረን ነው። ከዚህ ባሻገር ጥርስን መነቀስ፣ እጅንና ደረትንም እንዲሁ በንቅሳት ማድመቅ፣ እጅና እግርን እንሶስላ መሞቅ፣ በማር ወለላና በወተት መታጠብና የመሳሰለውን ያከናውኑ ነበር። ይህ ሁሉ እንግዲህ ከአውሮፓና ከሌሎች አገራት አንዳች ነገር ሳያስገቡ ነው።
ያም ቢሆን በጊዜ ሂደት ለውጦች መኖራቸው አልቀረም። አስቀድሞ በጠቀስነው መጽሐፍ ላይ ይህንኑ ነጥብ በማነሳት እንዲህ ይላል። «በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የሕዝብ አለባበስ እንደዘረዘርኩት ሲሆን፤ ከልብስ ጋር የሚደረጉ ጌጣጌጦች አይነታቸው ከአውራጃ አውራጃ ይለያያል። የልብስና ጌጣጌጣቸው አይነት መሠረታዊ ይዘቱ አንድ ቢሆንም ወቅትና ጊዜውን የጠበቀ በዘመን አመጣሽ ሞድ ይለዋወጣል። እንደዘመኑ እንደወቅቱ አዳዲስ ቅድ፣ ቀለም፣ ጥልፍ ወይም ጌጥ የተጨመረበት ሁሉም በአገሩ ልብስ ሲሽቀረቀር ሲዋብ ይታያል» ይላል።
ወደአለባበስ ስንሄድ፤ ባህል ወቱሪዝም በተባለው መጽሔት ላይ ተከታታዩ ተጽፎ ይነበባል፤ «የሴቶች ቀሚስ አለባበስ ከፍተኛ ክርክር ፈጥሮ የነበረው በ1964ዓ.ም ለ4ኛው የመምሪያ ምክር ቤት የተመረጡት ሁለት ወይዛዝርት ቆራጣ ቀሚስ ለብሰው በምክር ቤት አባልነት በቀጠሉ ጊዜ ነበር።» ይላል። ከዛም በተጓዳኝ ሜሪ አርምዴን እናንሳ። ሜሪ አርምዴ የሴቶች የውበት ሥራ ጀማሪ እንደሆነች ይነገርላታል። እንግዲህ ወደዛሬ የሴቶች የውበት አጠባበቅ ዘዴ ያደረሱን እነዚህ እርምጃዎች ናቸው።
እነዛ የውበት ማድመቂያዎች ሥራቸው ያለውን ውበት ማጉላት እንጂ ሌላ ውበት መሆን አልነበረም። የጥርስ ንጣትና መቃ አንገትን በንቅሳት፣ ሎሚ ተረከዝን በአልቦ፣ ሳንቃ ደረትን በአሸንክታብ አድምቀው ያሳዩታል። ዛሬም ያለው እንዲያ መሆኑን እንጃ! የውበት መጠበቂያ የሚባሉት ሁሉ ያለውን ውበት ከማድመቅ ይልቅ አዲስ መልክ ለመስጠት ጥቅም ላይ የሚውሉ ሳይመስሉ አልቀሩም።
ዛሬ ላይ ባህላዊ የሆኑ የውበት መጠበቂያ የሚባሉት በብዛት አይስተዋሉም። አሉ ከተባሉም ጥቂቶቹ እና ከከተማ ወጣ ባሉ አካባቢዎች ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በወይባ የመታጠን በወሎና ራያ አካባቢ የተለመደ የሴቶች የውበት መጠበቂያ ዘዴ ብቻ አብሮን የቀረ ይመስላል። ያም ብቻ ሳይሆን ውበትን መጠበቅ እንደምክንያት እየተነሳ ብዙ ሴቶች የተፈጥሮ ውበታቸውን አጥተው በመዋቢያ ቁሳቁስ ቀለማ ቀለሞች ላይ ጥገኛ ሆነዋል። ከቀደመው ጋር ሲነጻጸር ትልቁ ልዩነት የሚመስለኝ ይህ ነው።
በፊት ውበት ይጠበቃል፤ ዛሬ ደግሞ ውበትን መጠበቅ ቀርቶ ሌላ ውበትን ለመታጠቅ ጥረት ይደረጋል። አንዲት ሴት ስትቀባባና ሳትቀባባ ያላት ልዩነት በጣም ሰፊ ከሆነ፤ ከተቀባባች በኋላ ያየነው እርሷን ሳይሆን ቅቡን እንደሆነ ግልጽ ነው። ከዛም ሲብስ ይህ መታጠቅ በተለያዩ ውህዶች የሰውነት ቆዳን ሲጎዱና ጥገኛ ሲያድርጉት ይታያል። ይህም በአንድ በኩል ከአጠቃቀም ችግር እንደሆነ ብዙ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በዚህ ላብቃ! እንደው ነገሩን ለማንሳት ያህል የሴቶችንም ቀን ደገፍ ብለን ስለውበት አጠባበቅ ባህል አነሳን። ምንም እንኳ ከጊዜ ጋር አብረው የሚለወጡ ነገሮች ቢኖሩም ሰው የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን ለይቶ መጠቀም እንዳለበት ግን ሁሉም ይስማማል። በአንድ በኩል እያጣጣልን በሌላ በኩል ከባህር ማዶ በተለየ መንገድ ሲመጡ የተቀበልናቸው እንደ ንቅሳት ያሉ የውበት ማድመቂያዎች አሉ።
ያሉንን በባለሙያ እገዛ በዘመናዊ መንገድ ቀምሞና አዘጋጅቶ ማቅረብ የበለጠ አትራፊ ሳያደርገን አይቀርም። ይህም በአንድ በኩል ለጤና ምንም ጉዳት የሌለውን የውበት መጠበቂያ ማዘጋት ያስችላል። በሌላ በኩል የውበት መጠበቂያዎችን ከውጪ ከማምጣት ይልቅ ውጪ ላሉት ለመላክና ራስን ለማስተዋወቅም ይረዳል። እንግዲህ ማንነትን እንደተላበስን ውበታችንንም እንደባህላችን ማድመቅ ይገባናል፤ ሰላም!

 

ሊድያ ተስፋዬ

 

Published in ማህበራዊ
Sunday, 11 March 2018 01:14

ድል! ሸራ ላይ ተሥሏል

70 ሚሊዮን ወታደሮችን እንዲሁም 60 ሚሊዮን የአውሮፓ ዜግነት ያላቸው ሰዎችን ያሳተፈው «የመጀመጀ መሪያው የዓለም ጦርነት» ከጦርነት ታሪኮች ውስጥ በቀዳሚነቱ ይነሳል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1914 እስከ 1918 ድረስ የተደረገው ጦርነት በአሥከፊነቱ አቻ የማይገኝለት ብቻ ሳይሆን፤ 11 ሚሊዮን ወታደሮችን እና 7 ሚሊዮን ንፁሀን ዜጎችን ቀርጥፎ የበላ በሰው ልጆች ላይ የተላከ እርግማን ተደርጎ ይቆጠራል። ይህ ጦርነት በዓለም ላይ ሰፊ የአመለካከት እና የርዕዮተ ዓለም ለውጥ ለመምጣት መነሻ መሆኑም ይታመናል። በሰው ልጆች የማህበራዊ አኗኗር ግንዛቤ እና እይታ ላይ አሻራውን አሳርፏል። የዚህ ጦርነት አሻራ ካረፈባቸው መካከል ጥበባዊ ሥራዎች ይጠቀሳሉ።

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በተጠናቀቀበት 1918 በተለይ የዓለሙን ጩኽት፣ ማህበራዊ መሥተጋብር ብሎም ግላዊ ምልከታ በሸራቸው ለታሪክ የሚያቀብሉ ሰዓሊያን የወቅቱን አሰቃቂ የጦርነት ምሥሎች ያሰፍሩ ነበር። ሰዓሊው «በሪያሊዝም የአሳሳል ፍልስፍና» አንድን ነገር እንዳለ ወይም ምንም የግል ምልከታ ሳይጨምርበት በብሩሹ እና በቀለሙ ብቻ ተጠቅሞ ምሥሉን እንደነበረ ያስቀምጥ ነበር።
አሜሪካዊው አርቲስት ሪቻርድ ካቶን ውድቪል በሪያሊዝም የአሳሳል ጥበብ የዓለም ጦርነትን ገፅታዎች በሚያሳዩ ሥዕሎቹ ይታወቃል። በዚህ ጥበባዊ ክህሎት ዓለም በጦርነቱ ውሥጥ ሥትዳክር፤ አንዱ ድል ሲነሳ ሌላኛው ደግሞ ሽንፈቱን ሲከናነብ፤ ይህኛው ሉአላዊነቱን ለማስከበር ሲዳክር፤ ያኛው ዳር ድንበር ሲደፍር፤ ሰው የሰውን ነፍሥ ሲነጥቅ፤ እናቶች ልጆቻቸውን በጉያቸው ሸሽገው የሚገቡበት እምጥ ሲፈልጉ... በወቅቱ ቀለም አዋህደው ብሩሽ ጨብጠው ሸራቸው ላይ እውነታውን ያፍረጠረጡ፤ ታሪክ ይፈርድ ዘንድ ጥበባዊ ምልከታቸውን ያቀበሉ በርካታ ናቸው።
በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሪያሊዝም የአሳሳል ፍልስፍናን የሚገዳደር አዲስ የሥነ ጥበብ ፍልስፍና ተጀመረ። «ኤክስፕረሽኒስት» ወይም አንድን ሸራ ላይ የሚሰፍር ሥዕል በራስ ምልከታ «በአብስትራክት» ዘይቤ የመግለፅ፤ ዋና መልዕክቱ በተመልካች እይታ ውስጥ እንዲጠነሰስ የማድረግ ፋሽን እየተለመደ መጣ። ይህ እንዲሆን መንገዱን የከፈተው የፎቶግራፍ ቴክኖሎጂ መተዋወቅ እና የሪያሊዝም የአሳሳል ሥልትን ተፈላጊነት እየቀነሰ መምጣት ነበር። የኤክስፕረሽኒስትስ አሳሳል በተመሳሳይ ታሪካዊ ሁነቶችን በተለይም የጦርነት ገፅታዎችን በሸራቸው ላይ በማሥፈር ይታወቃሉ። በተለይ ድል እና ጀብደኝነትን ቁልጭ አርጎ ለመጪው ትውልድ ለማሥቀመጥ የሥነ ጥበብ ሚናው እጅጉን የጎላ ነው።
የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀንዲል በመሆኑ ላለፉት 122 ዓመታት ትውልድ ሊዘክረው፣ የታሪክ ፀሀፊያን ሊያሞካሹት፣ የኪነ ጥበበ ባለሙያዎች ሊቀኙለት ችለዋል። በመግቢያችን ላይ ሥለ ዓለም ጦርነት እንዳወሳነው ሁሉ የአድዋ ጦርነት ታሪክ የማይዘነጋው የመላው ዓለም ተፈጥሯዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሰበት ነው። አድዋ ላይ ታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል። በዓለማችን ላይ ከተደረጉ ጦርነቶች ሁሉ ለየት የሚያደርገውም ወራሪ ሀይልን ለመከላከል፣ ነፃነትን በጉልበተኞች ላለመነጠቅ የተደረገ መስዋእትነት መሆኑ ነው። በወቅቱ ሰው ለሰው ክብር ሲል ሞቷል። የነፃነት ልክ እና ጥግ በአድዋ አርበኞች ቁና ተሰፍሮ ልክ ተበጅቶለታል። ይህን ደግሞ ለመጪው ትውልድ ለማሻገር ከጥበብ በላይ የቀረበ ከየትም ሊገኝ አይችልም።
ለዘመናት የአገራችን የጥበብ ባለሙያዎች በቻሉት አቅም የኢትዮጵያን ታሪክ አጉልተው ለማሳየት ተግተዋል። በጥረታቸው እና ባላቸው አቅም ልክም ተሳክቶላቸዋል። የኋላውን ለወደፊቶቹ ለማሻገር ሥነ ፅሁፍ፣ ሙዚቃ ፊልም እና መሰል ሥራዎች ለተጠቀመባቸው ትክክለኛ መሳሪያ ናቸው። በተለይ «ነገር በአይን ይገባል» እንደሚባለው አገርኛ ብሂል ታሪክን በሚገባ ሰንዶ ለማስቀረት፤ የሥነ ጥበብ ዘርፍ የሆነው ሥዕል ሁነኛ መንገድ ነው። ታዲያ በዚህ ዘርፍ ታላቁን የሀበሻ ድል እና ተጋድሎ ለመዘከር ምን ተሰራ?
በኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ በተለይ ደግሞ ስዕል ብዙ መቶ ዓመታትን አሥቆጥሯል። በመላው ዓለም እና በአህጉራችን አፍሪካ የኢትዮጵያ ሥነ ሥዕል በሰፊው ይታወቃል። ሆኖም ግን በወቅቱ የነበሩት የሥዕል ሥራዎች የቤተክርስቲያናትን ትውፊት፣ ገድል እንዲሁም የአምልኮ ሥነሥርዓትን የሚዳስሱ ነበሩ።
በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ አርቲስቶች አዳዲስ ርእሶች እና ከሀይማኖት ነክ ሥራዎች የተለዩ ጉዳዮችን ይዘው ብቅ ብለዋል። በርግጥ በሰዓሊያን ዘንድ ተመራጭነት ያላቸው ሀይማኖት ነክ ሥዕሎች አሁንም ድረስ ይዘወተራሉ። በዚህ ውሥጥ ሥለ ኢትዮጵያ ታሪክ የሚያወሱ ውስን ሥራዎች አይጠፉም። በመግቢያችን ላይ እንዳወሳነው የአሜሪካዊው አርቲስት ሪቻርድ ካቶን ውድቪል የሪያሊዝም የአሳሳል ሥልት እንዲሁም የኤክስፕሬሽኒስትስ ዘይቤን በመከተል በብዛት ታሪክን የሚያወሱ ሥራዎች ቀርበዋል ለማለት ባያስደፍርም ኢትዮጵያዊ ሰዓሊያን ውሥን ሙከራዎችን ማድረጋቸውን መገንብ ይቻላል።
የአድዋ ድልን በሸራ
ከሳምንት በፊት የነበረው 122ኛው የአድዋ ድል በዓል ከዚህ ቀደም ከነበረው ይዘት እጅጉን ባማረና በደመቀ መንገድ በልዩ ልዩ መሰናዶዎች ተዘጋጅተው በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል። ያለፉት አባቶች በደማቸው ያቆዩትን የድል በዓል ለማክበር የተሰጠው ትኩረት ይበል የሚያሰኝ ከመሆኑም በዘለለ፤ የአርበኞቹን የጀብዱ ታሪክ በአዲስ መልክ ለማሥታወስ የተሞከረበት መንገድ አሥደናቂ ነበር። ከከያንያን አስከ ገጣሚያን፤ ከደራሲያን እስከ ሰዐሊያን፤ ከወጣት እስከ አዛውንት የጀግኖቹን የድል ማድረግ ብስራት እንደየአቅማቸ ውና ችሎታቸው በተለያዩ መሰናዶዎች ዘክረውት ውለዋል። ኢትዮጵያም በማንነት ኩራት ደረቷን ነፍታ ሰንብታለች። ባሳለፍነው ሳምንት በጣይቱ ሆቴል የቀረበው የሥዕል ኤግዚቢሽንም የዚሁ ዝግጅት አካል ነበር።
የካቲት 22 በጣይቱ ሆቴል የአድዋን ድል በሥዕል ሥራዎች ለመዘከር የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ለአንድ ሳምንት ለተመልካች ክፍት ሆኖ ባለፈው ዓርብ ተጠናቋል። 15 ወጣት ሰአሊያንን በዝክረ አድዋ ዝግጅት ላይ ተሳትፈዋል። ሁሉም ሦስት ሦስት የሥዕል ሥራዎቻቸውን ይዘው ቀርበዋል። ሥራዎቹም የሪያሊዝም እና የኤክስፕሬሽኒስት የአሳሳል ዘይቤን የሚያሳዩ የጦርነት እና የድል አድራጊነት ታሪኮችን ያካተተ ነበር።
ሰዓሊ ፍፁም ታሪኩ የዝክረ አድዋ የሥዕል አውደ ርዕይን ከጓደኞቹ ጋር አዘጋጅቷል። ድሉን የሚዘክሩ አራት ሥራዎችንም ይዞ ቀርቧል። የአውደ ርዕይው ዋና ዓላማ አትዮጵያዊ ማንነትን ለማንፀባረቅ እና ያለፈውን በጎ ታሪክ ለመጪው ትውልድ በሥዕል ሥራ ለማሥተላለፍ መሆኑን ይናገራል። «ወደፊት ለመሄድ የግዴታ ወደኋላ መመልከት ይኖርብናል» በማለትም ታሪክን በሥነ ጥበበ ሥራዎች መዘከር አሥፈላጊ መሆኑን ይገልፃል። ሥራዎቹም የጀግኖች አባቶችን ታሪክ ብሎም ለድል የበቁበትን ሚሥጥር ለማሳየት ሙከራ አድርጓል።
ሰዓሊ ፍፁም «በዚህ ዘመን በማይጠቅሙን የምዕራባውያን ባህል ተተብትበናል። ይህ ደግሞ የእጅ አዙር ቀኝ ግዛት ነው» በማለት ጀግኖች አርበኞች በደማቸው ያሥከበሩትን ማንነት የሚሸረሽርና አደራውን የሚበላ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን ይገልፃል። በሥዕል ሥራዎቹ ላይም ሁለቱን ፅንፎች ለማሳየት ሙከራ አድርጓል። ከዚህ ውጥንቅጥ ውሥጥ ለመውጣትም ቀላሉ መንገድ ወደኋላ መመልከት እና የአድዋ ድል እንዴት እንደመጣ መገንዘብ በቂ ነው ይላል።
ሰዓሊያኑ ድልን በሸራ ላይ ከማሥፈር በዘለለ የአሁኑ ትውልድ ፈሪሃ እግዚአብሄር እንዲኖረው፣ በወጉ አለባበሱን እንዲያሥተካክል፣ በራሱ ኢትዮጵያዊ ባህል እና ወግ መኩራት እንዲችል ብሩሾቻቸውን ከቀለም ጋር አሰባጥረው ጥልቅ የሆኑ መልዕክቶችን አሥተላልፈዋል። ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታም የብሄራዊ በዓሉን በሥነ ጥበብ ሥራ ደምቆ እንዲውል ብሎም ተሻጋሪ ታሪክ እንዲሆን ተግተዋል። ዝግጅታቸው ጅምር ቢሆንም ሀሳባቸው ትልቅ ነውና ለወደፊቱ በይዘትም ሆነ በአሳታፊነቱ እያደገ እንደሚሄድ በቀላሉ መገመት እንደሚቻል ለመገመት አያዳግትም።
አውደርዕይው ላይ ሥራዎቻቸውን ካቀረቡት ሰዓሊያን መካከል ወጣት ሲሳይ ምትኩ ይገኝበታል። ሦስት ስራዎችን አቅርቧል። ከዚህ ቀደም የአድዋ ድልን በሥዕል ሥራዎች ሳይሆን በተለያዩ ዝግጅቶች ነበር የሚያከብረው። ሙያው ድሉን የመግለፅ እና ታሪክን የማውረስ አቅም እንዳለው በመረዳቱም ከጓደኞቹ ጋር በጋራ በመሆን አውደርዕዩን አዘጋጅተዋል። ሁለት የቀለም ቅብ እና እንጨትን በመቅረፅ «Wood engraving» አንድ ሥራ አቅርቧል።
ሰዓሊ ሲሳይ በአንደኛው ሥዕሉ ላይ የኤክስፕሬሽኒስት የአሳሳል ዘይቤን ተከትሎ «የነፃነትን» ትርጉም ለመግለፅ ሞክሯል። ሥራው ከአንድ ጥቁር ነገር ግልፅ ወደሆነ ብርሀን መውጣትን ያመለክታል። በዚህም የሰው ልጅ ነፃቱን እና ሉአላዊነቱን ለምን ማስደፈር እንደማይፈልግ ለማሳየት ሙከራ አድርጓል። የአድዋ ጦርነትም በዚህ መንፈስ የተደረገ ተጋድሎ መሆኑን አሳይቷል። አሁን ያለው ትውልድም የተከፈለለትን ዋጋ እንዲረዳ እና በዚህ ልክ ክብሩን፣ ማንነቱን ብሎም አገሩን ከወራሪ ሊከላከል እንደሚገባው በሸራው ላይ የተሳለው የድል ብሥራት ያስረዳል።
ሥነ ጥበብ በተለይም ሥዕል ጥልቅ እይታን በመጠቀም የሰውን ልጅ መስተህልይ (አዕምሮን) የማንቃት ኃይል አለው። ይህን አቅም ደግሞ ታሪክን ለማውሳት እና «ያኔን» ለመንገር ሥንጠቀምበት በትውልዶች መካከል ጠንካራ ድልድይ መሥራት ይችላል። ታሪኩን ያላወቀ ትውልድ ለራሱም ለአገሩም ክብር አይኖረውም። ታዲያ ይህን መሰል ክፍተት እንዳይኖር የጥበበ ባለሙያዎች ድርሻ ጉልህ ነው። ባለፉት ጊዜያት በነበሩ የድል ክብረ በዓሎች የኪነ ጥበብ እና ሥነ ጥበበ ባለሙያዎች በባለቤትነት ድርሻቸውን ባለመወጣታቸው በተፈለገው መንገድ መልዕክቶችን ለህብረተሰቡ ማድረስ አልተቻለም ነበር። በዘንድሮው ክብረ በዓል ላይ «ድልን ሸራ ላይ ከመሳል» አንስቶ በተለያዩ የጥበብ ሥራዎች አድዋን መዘከር በመቻሉ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች ታይተዋል። የዝግጅት ክፍላችንም ይህን መሰል ዝግጅት እንዲሁ እንደተሟሟቀ ይቀጥል የሚል መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ዳግም ከበደ

 

 

 

Published in ማህበራዊ

አንድ ማንበብ የማይወድ ሰው ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር ምንድነው?›› ተብሎ ቢጠየቅ ‹‹የሀዲስ አለማየሁ መጽሐፍ›› ብሎ መመለሱ አይቀርም፡፡ ፍቅር እስከ መቃብርን ምንም ማንበብ የማይችሉ እንኳን ቢያንስ በስም ያውቁታል፡፡ በይዘቱ ላይ ማብራራት አይችሉ ይሆናል እንጂ እረኞች እንኳን በዛብህና ሰብለ ወንጌል የሚባሉ እንዳሉ ያውቃሉ፡፡ ከዚያ አለፍ ሲል ደግሞ ፊት አውራሪ መሸሻና ጉዱ ካሳ የሚባሉ ሰዎች እንደነበሩ መጽሐፍ የማያነቡ ሁሉ ያውቃሉ፡፡ እንዲያውም አሁን አሁን በዛብህና ሰብለወንጌል የሚባሉት በሕይወት የነበሩ ሰዎች የሚመስሏቸውም አሉ፡፡ ይሄ ማለት የማያነቡና ልብወለድ መሆኑን የማያውቁ ሁሉ ስለፍቅር እስከ መቃብር ሰምተዋል ማለት ነው፡፡
ይህ የሆነው በብዙ ምክንያት ነው፡፡ አንደኛ ፍቅር እስከ መቃብር ከሰፈር ጨዋታ እስከ ትልልቅ መድረኮች ብዙ ተብሎለታል፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይደመጥ በነበረው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ራዲዮ በ1990ዎቹ አካባቢ ለረጅም ጊዜ ተተርኳል፡፡ ራሳቸው ሀዲስ አለማየሁ እንዳሉት ወጋየሁ ንጋቱ ለመጽሐፉ ሕይወት ሰጥቶታል፡፡ በፍቅር እስከ መቃብር ውስጥ ያሉ ገጸ ባህሪያት በሕይወት ያሉ እስከሚመስለን ድረስ ውስጣችን ገብተዋል፡፡ የወጋየሁ ንጋቱ ትረካ ለማያነቡት ሁሉ መጽሐፉ እንዲታወቅ አድርጎታል፡፡
የማንበብና መጻፍ ልምድ ወደአላቸው ሰዎች ስንመጣ ደግሞ ፍቅር እስከ መቃብር በርካታ ውይይቶች፤ በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎች ተሰርተውበታል፡፡ የቅድመ ምረቃም ሆነ የድህረ ምረቃ ምርምሮች ተሰርተውበታል፡፡ በብዙ ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ ዳሰሳ ተደርጎበታል፡፡ የራዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የስነ ጽሑፍ ባለሙያዎች ብዙ ብለውበታል፡፡ብዙ የመድረክ ውይይቶች ተደርገውበታል፡፡
ፍቅር እስከ መቃብር ስሙ የሚነሳው ለሱ ተብሎ በተዘጋ መድረክ ላይ ብቻ አይደለም፡፡ በየትኛውም የስነ ጽሑፍ መድረክ ላይ፣ የመጻሕፍት ውይይት ላይ ፍቅር እስከ መቃብር የልብወለድ መጽሐፍ ማነጻጸሪያም ተደርጎ ስሙ ይነሳል፡፡ በማስተማሪያ መጻሕፍት ውስጥም ይጠቀሳል፡፡ ተማሪዎች ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ ቢያንስ በስም ያውቁታል፡፡
ከእነዚህ ሁሉ ምክንያቶችም በላይ ደግሞ መጽሐፉ በራሱ ላነበበው ሁሉ አይረሴ ሆነ፡፡ እዚህ ጋ የበዛብህና ሰብለወንጌል ፍቅር አለ፤ እዚያ ጋ የቦጋለ መብራቱና የውድነሽ በጣሙ ፍቅር አለ፤ አሁንም እዚያ ጋ የፊት አውራሪ መሸሻ እና ወይዘሮ ጥሩአይነት ፍቅር አለ፡፡ የካሳ ዳምጤ እና የእንቆጳ ፍቅርም እይዘነጋም፡፡ የሁሉም ፍቅር የሚሄደው እስከ መቃብር ነው፡፡ ይህም በሰዎች ልብ ውስጥ አይረሴ አድርጎታል፡፡
ወዲህ ደግሞ በዚያ ዘመን የማይታሰበውን፣ በዚያ ዘመን ተደፍሮ የማይባለውን ካሳ ዳምጤ(ጉዱ ካሳ) ደፍሮ እየተናገረ የአንባቢን ቀልብ ያንጠለጥላል፡፡ እነ አበጀ በለው በዚያ በፊውዳል ሥርዓት ውስጥ ‹‹እምቢ!›› ማለት በማይታሰብበት ዘመን ‹‹አንገብርም›› እያሉ ያምጻሉ፡፡ የመብት ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር ፍቅር ነው፤ ፖለቲካ ነው፣ ማህበራዊ ሕይወት ነው፡፡ መጽሐፉ በፍቅር፣ በማህበራዊ ኑሮ እና በፖለቲካ ብዙ ሊባልለት የሚገባ ነው፡፡
ይህን መጽሐፍ በሁሉም ዘውግ መዳሰስም ሆነ መወያየት ይከብዳል፡፡ በፍቅር፣ በማህበራዊ ኑሮም ሆነ በፖለቲካ ሥርዓቱ እየለዩ ሊያወያይ ይችላል፡፡ ከስነ ጽሑፍ ቅርጽ አንጻር ደግሞ ሌላ ራሱን የቻለ መድረክ መሆን ይችላል፡፡
በብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጄንሲ በሚደረገው የመጻሕፍት ውይይት ላይ ሚዩዚክ ሜይ ዴይ ባለፈው ወር (የካቲት 11 ቀን 2010 ዓ.ም) በፍቅር እስከ መቃብር ላይ ውይይት አድርጎ ነበር፡፡ በውይይቱም የስነ ጽሑፍ ባለሙያና መምህር መሰረት አበጀ ‹‹የግፍ መርህ ዳፋ- የሀዲስ አለማየሁ ደወል(በፍቅር እስከ መቃብር)›› በሚል በመነሻ ሀሳብ አቅርበው ውይይት ተደርጓል፡፡ አቅራቢው ትኩረት ያደረጉት መጽሐፉ በፊውዳሉ የአገዛዝ ሥርዓት ላይ ብቻ ባለው ይዘት ነው፡፡ ይሄውም በፊትአውራሪ መሸሻና በነዋሪው መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ማለት ነው፡፡
በመጽሐፉ ውስጥ ፊትአውራሪ መሸሻ የገዥው መደብ ወኪል ናቸው፡፡ እርሳቸው የፊውዳሉን ሥርዓት ሲወክሉ ከጭቁኑ ሕዝብ ጋር የነበረውን ግብግብ ያሳያል፡፡ የጭቁኑ ሕዝብ ጥያቄም የነጻነትና የፍትህ ጥያቄ ነው፡፡ ይህም የግፍ አሰራር ነጻነትን በማሳጣቱ የመጣ ብሶት ነው፡፡ የነበረው ጭቆና የተፈጥሮ መብትን ሁሉ የሚጋፋ ነው፡፡
በበዛብህና በሰብለወንጌል ፍቅር እንኳን ስንሄድ ሁለቱ እንዳይገናኙ ያደርጋል፡፡ ግፍ ሲበዛ አመጽን ያስነሳል፡፡ በዛብህና ሰብለወንጌል ግፍ ሲበዛባቸው አምጸዋል፤ ተሰደዋል፡፡ በዛብህ ከወላጆቹ ኋላቀር እምነት ጋር፤ ሰብለወንጌልም ከወላጆቿ ኋላቀር አስተሳሰብና ልማድ ጋር፤ ጉዱ ካሳ ከሥርዓቱ አሮጌ አስተሳሰብ ጋር ሲፋለሙ ያሳያል፡፡ ይሁን እንጂ የተናጠል እንቅስቃሴያቸው ደግሞ አሸናፊ አያደርጋቸውም፡፡ የጉዱ ካሳ፣ የበዛብህና የሰብለወንጌል መጨረሻ ነጻነትና ፍትህ እንደናፈቁ መቅረት ይሆናል፡፡ ሌላኛው አይነት አመጽ ሕዝባዊ የሆነው ነው፡፡ ይሄውም በገበሬዎችና በገዥው መደብ መካከል የነበረው ማለት ነው፡፡ ቅራኔው በጣም የቆየ ነበር፡፡ ይህንንም እነ አበጀ በለው አሳይተዋል፡፡
ፊትአውራሪ መሸሻ ከተለመደው ግብር በተጨማሪ ለዓመት በዓል መታያ እንዲቀርብላቸው ፈለጉ፡፡ ገበሬዎቹ ለሰላም ሲሉ ያቀርቡላቸው ነበር፡፡ ገበሬው ፍትሃዊ እንዳልሆነ እያወቀ፤ ነገር ግን ሀብትና ንብረቱ እንዳይጠፋ፣ ልጆቹ እንዳይበተኑበት ሲል ገበሬው በደሉን እያወቀ ይገብር ነበር፡፡ በኋላ ፊታውራሪ ግፉን በጣም ሲያበዙት ገበሬው ተሰብስቦ መመካከር ጀመረ፡፡ ‹‹ግዴታ የለብንምና አንከፍልም›› አሉ፡፡ ከመካከላቸውም አበጀ በለውን መረጡ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ ፊት አውራሪ ፈተና የገጠማቸው፡፡ እነ አበጀ በለው ዘመናዊ አስተሳሰብ የነበራቸው ሆኑ፡፡ አበጀ በለው ፊት አውራሪን በማረካቸው ጊዜ ‹‹ተዋግተህ እንኳን ብትይዘኝ አይቆጨኝም ነበር›› ሲሉት ‹‹ተዋግቼ መያዝ እችል ነበር፤ ግን እኔ ደም እንዲፈስ አልፈልግም›› ነው ያላቸው፡፡
‹‹ገበሬ እና ወይፈን እንዛዝላ ሲጥሉበት ነው›› ይሉ ነበር ፊት አውራሪ መሸሻ፡፡ ገበሬን ከከብት ጋር እያነጻጸሩ ማለት እኮ ነው፡፡ ገበሬውን እንዲህ ሲንቁ ሲንቁ ነው ኋላ ጉድ የሰራቸው፡፡ ፊት አውራሪ ገበሬዎችን ለመያዝና ለመቅጣት ሲዘምቱባቸው ገበሬዎች ግን ይሸሹላቸው ነበር፤ ይህም ደም እንዳይፈስ በማሰብ ነው፡፡ ፊት አውራሪ ግን ይህን አልተረጎሙትም፤ ፈርተውኝ ነው የሚሸሹ ብለው ነው ያመኑት፡፡ ከእርሳቸው ይልቅ ሕዝቡ ሰላም ይፈልግ ነበር ማለት ነው፡፡ ከዘመኑ አስተሳሰብ ወጣ ያለ ዕይታ የነበረው ጉዱ ካሳ ‹‹ልጅ ናቸው፤ አያውቁትም›› እያለ ይሳለቅባቸው ነበር፡፡ አበጀ በለው ደግሞ ‹‹ህጋዊ ሽፍታ›› ይላቸው ነበር፡፡
ፊት አውራሪ መሸሻ በእኩልነት አያምኑም፡፡ በዛብህን ‹‹የድሃ ልጅ›› እያሉ የባላባት ልጅ ባለመሆኑ በጣም ያሳንሱታል፡፡ ልጃቸው ሰብለወንጌል ‹‹እርስዎ የድሃ ልጅ የሚሉትን እኔ እወደዋለሁ›› ስትላቸው ‹‹ያ መተተኛ የተበተበብሽ መተት ነው እንዲህ የሚያደርግሽ›› እያሉ ይቆጣሉ፡፡ ምክንያቱም ራሳቸውን የተቀባ የባላባት ዘር አድርገው ስለሚያስቡ ሌላውን አሳንሰው ነው የሚያዩት፡፡
ፊት አውራሪ መሸሻ እምነታቸውም የተምታታ ነው፡፡ ዳዊት ይደግማሉ፤ ልጃቸውንም ያስተምራሉ፤ ጊዮርጊስን ያምናሉ፤ ያስቀድሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከባዕድ አምልኮ የተላቀቁ አይደሉም፡፡ ዘመቻ ሲሄዱ ቀበሮ ካገኙ እንደ መጥፎ ዕድል ነው የሚቆጥሩት፡፡ ጊዮርጊስን እያመኑ ያሰቡት ነገር ካልደረሰላቸው ደግሞ ‹‹ጊዮርጊስ ከዳኝ›› እያሉ ይወቅሱታል፡፡ ፈረሳቸውን እንኳን ‹‹እንደ ጊዮርጊስ እንዳትከዳኝ›› ብለውታል፡፡
ፊት አውራሪ መሸሻ ያንን ሁሉ ግፍ ይዘው መጨረሻ ላይ ተሸንፈዋል፡፡ ልጆቻቸው ተሰቃይተዋል፤ራሳቸው ተሰቃይተዋል፤ ከብቶታቸውን ተዘርፈዋል፡፡ የገዢው መደብ ወካይ ነበሩና የሥርዓቱን ውድቀት አሳይተዋል፡፡ ፍትህ ለማግኘት ሲደክሙም አድካሚነቱን አይተዋል፡፡
የስነ ጽሑፍ ባለሙያና መምህሩ መሰረት አበጀ እንደሚሉት ስነ ጽሑፍ መጻፍ ያለበት መሆን ስለሚገባው ቅንና በጎ ጉዳይ ነው፡፡ ስለመከባበር ማሳየት አለበት፡፡ መጥፎውን ነገር ብቻ መጻፍ ከገሃዱ ዓለም ከሚታየው የተለየ አይሆንም፡፡ በአገራችን ግን የማንበብ እንጂ የመተርጎም ችግር እንዳለ ያሳሉ፡፡ ለዚህም አንድ ምሳሌ ይጠቅሳሉ፡፡ በዓሉ ግርማ ‹‹የቀይ ኮከብ ጥሪ›› መጽሐፉ ላይ በጣም መመስገን ነበረበት፤ ግን ብዙም ሲመሰገንበት አይሰማም፡፡ እንዲያውም የመንግሥት ደጋፊ ተደርጎ ነበር የተወሰደው፡፡ በቀይ ኮከብ ጥሪ ላይ ግን ደርግና ኢህአፓ መታረቅ እንዳለባቸው ነው ያሳየው፡፡ ሌላ መንግሥት ከሚመጣ ያለውን መንግሥት ማረቅና ማስተካከል እንደሚያስፈልግ ነው፡፡ «ሂሩት ኢህአፓ ናት፡፡ ደርቤ ደግሞ የአብዮት ጠባቂ ነው፡፡ ሂሩት ተመታ ስትወድቅ ደርቤ አንስቶ ወደ ሆስፒታል ይወስዳታል፡፡የዚህም መልዕክት ኢህአፓና ደርግ እንዲታረቁ ነው» በማለት ሀሳቡን ያነፅሩታል።
ፍቅር እስከ መቃብር ለውጥ ፈላጊነትን ያሳያል፡፡ ግፍ መጨረሻው እንደማያምር ያሳያል፡፡ ድርሰቱ በወቅቱ የነበረው የዘውዳዊ አገዛዝ የአንድ ብሄር የበላይነት የሚታይበት እንዳልሆነም ያሳያል፡፡ የገዥው መደብ ወካይ ፊትአውራሪ መሻሻ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ናቸው፡፡ ፍዳ ሲያሳዩት የነበረው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪውንና የክርስትና እምነት ተከታዩን ነበር፤ የራሳቸው ወገን ላይ ነው ያን ሁሉ ግፍ ሲፈጽሙ የነበረው፡፡
ደራሲው ሀዲስ አለማየሁ በፊትአውራሪ መሸሻ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን አገዛዝ ነው ያሳዩት፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ ነበር ከመድረኩ ተሳታፊዎች አንድ ክርክር የተነሳው፡፡ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሀዲስ አለማየሁን ሸልመዋቸዋል፡፡ ጥያቄ የሆነው ‹‹የእርሳቸው አገዛዝ የግፍ አገዛዝ መሆኑን እየተረከ እንዴት ሊሸልሙ ቻሉ?›› የሚለው ነው፡፡ አንዳንዶቹ ‹‹ንጉሱ መጽሐፉን ሳያነቡት ይሆናል፤ ወይም አልገባቸውም ማለት ነው›› ብለዋል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ‹‹የለም! እንዲህ ማለትማ ድፍረት ነው፤ እንዴት አያነቡትም? እንዴትስ አይገባቸውም? በቃ! ሥራው ድንቅ ስለሆነ ተደስተውበት ነው፤ እንዲያውም ንጉሡ በቤተ መንግሥት ውስጥ ከነበሯቸው መጻሕፍት አንዱ ፍቅር እስከ መቃብር ነበር›› ብለዋል፡፡
የስነ ጽሑፍ ባለሙያና መምህር መሰረት እንደሚሉት በወቅቱ በስነ ጽሑፍ መዝነው ሽልማት የሚሰጡት የስነ ጽሑፍ ባለሙያዎች ነበሩ፡፡ ንጉሡም ያንን አይቃወሙም፡፡ ቢያነቡትም ባያነቡትም የመጽሐፉን ታሪክ ያውቁታል፡፡ መሪዎች በፖለቲካም፣ በኢኮኖሚም በየትኛውም ነገር አስረጂዎች አሏቸው፡፡ ባለሙያዎች ይነግሯቸዋል፡፡ ዳሩ ግን ንጉሡ ለምን ሀዲስ አለማየሁን እንደሸለሙ ተጠይቀው ‹‹እንደዚህ መሆኑን እኔ መቼ አውቄ›› ብለዋል፡፡ በዚያ ላይ በወቅቱ የነበራቸው ጊዜ ያንን መጽሐፍ ለማጣጣም የሚያመች አልነበረም፡፡ በፖለቲካ ሥራ ተጠምደው ነው የሚውሉት፡፡
ፍቅር እስከ መቃብር እውነትም የዘመኑን ዘውዳዊ አገዛዝ የተነበየ ነበር ማለት ነው፡፡ የሥርዓቱ ወካይ ፊትአውራሪ መሸሻ መጨረሻቸው እንዳላማረው ሁሉ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መጨረሻም አላማረም፡፡ የነበረው የባላባትነት ዘመን አክትሟል፡፡ በባላባትነት ያምኑ የነበሩት ንጉሱ በመጨረሻ በደርግ እጅ ወድቀዋል፡፡ ሥርዓታቸው መውደቅ ብቻ ሳይሆን እርሳቸውም ተሰቃይተዋል፡፡
በነገራችን ላይ የስነ ጽሑፍ ባለሙያና መምህር መሰረት ከተናገሩት ‹‹ትርጉም›› የሚባለው ነገር ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ብዙዎቻችን እናነባለን እንጂ አንተረጉምም፡፡ ለዚህም ነው አረዳዳችን የተለያየ የሚሆነው፡፡ እርግጥ ነው ቢተረጎምም ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ የተለያየ አተረጓጎም መኖሩ አይቀርምና፡፡
ለምሳሌ ፍቅር እስከ መቃብርን ያነበበ አንድ ወጣት፣ አንድ የሃይማኖት እና አንድ ፖለቲከኛ ስለመጽሐፉ ጭብጥ ብንጠይቅ የተለያየ አረዳድ ልናገኝ እንችላለን፡፡ ምናልባትም ወጣቱ ስለ በዛብህና ሰብለወንጌል የፍቅር ጽናት፣ የሃይማኖት አባቱም ስለ እምነት፣ ፖለቲካኛውም በዘውዳዊ ሥርዓቱ ውስጥ የነበረውን አገዛዝ ሊነግሩን ይችላሉ፡፡ መጽሐፉ ከዚህም በላይ ብዙ የሚያወያይ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

ዋለልኝ አየለ

Published in ማህበራዊ

ሕገ መንግሥቱንና ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን፣ የአገርን አድነትና ሠላም ለማስጠበቅና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታውን አፋጥኖ አገራዊ ልማትን በማጠናከር ፀረ ድህነት ትግሉን በውጤታማነት ለማስቀጠል የሚያስችል ለሁሉም አገራት የሚሠራ የተሻለ ነው የሚባል አንድ አይነት ዘዴ የለም። ለአሜሪካ የሚሠራ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለእኛ ላይሠራ ይችላል። አውስትራሊያና ካናዳ አንድነታቸውን የጠበቁበት ዘዴ ለእኛ ላይሆን ይችላል። ቻይና ያደገችበት የልማት ቅደም ተከተል ለእኛ ሂደት ላይገጥም ይችላል። እነሱም የራሳቸውን ዘዴ ይዘው ይቀጥላሉ። እኛም የሚጠቅመንንና በተጨባጭ ከፊታችን ለተደቀኑ ችግሮቻችን መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ዘዴዎችን መምረጥ ይጠበቅብናል።
ለአንድ ተመሳሳይ ችግር እንኳ አንድ ዘዴ ብቻ ሁልጊዜ ይሠራል ማለት አይቻልም። ለትናንቱ የፀጥታ ችግር መፍትሄ የተጠቀምንበት ዘዴ ለዛሬው የፀጥታ ችግራችን መፍትሄ ይሆናል ማለት አይደለም። እንደ ችግሩ መጠን፣ /ስፋት/ ጥንካሬና አስጊነት ችግሩ ከተከተላቸው አዳዲስ ዘዴዎች /ታክቲኮች/... ወዘተ አንፃር የእኛም የመፍትሄ ዘዴ በሚመጥን ደረጃ መቃኘት አለበት።
ካለፈው ሂደታችን የተገኙትን ልምዶች ቀምረን ለአሁኑ ችግር በሚሆን ሁኔታ መጠቀም መቻል አለብን። ወደ እኛ ጉዳይ ስንመጣ በሕገመንግሥቱና በሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ፣ በአገራችን አንድነትና ሰላም ላይ፣ በሕዝቦች የዕለት ተዕለት ኑሮ፣ የመንቀሳቀስ ነፃነት ላይ የተደቀኑብንና ብሔርን/ዘርን/ ማዕከል አድርገው በሚንቀሳቀሱ በታኝ አመፆች ላይ የምንወስደው ርምጃ ይህንኑ ችግር በሚፈታ ደረጃ መሆን አለበት።
ለዚህ ችግር በርካታ መፍትሄዎች ቢኖሩም ችግሩን ባለበት ለማቆም ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አንዱ ነው። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም ዓርብ የአድዋ ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያፀደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአገራችን ጊዜያዊ ሁኔታ ለሚጠይቀው ጥያቄ ተመጣጣኝና ተገቢ መፍትሄ ነው። አዋጁ በፖለቲከኞችና በሕዝቦች ዘንድ እኩል አተያይ የለውም። ፖለቲከኞቹ አዋጁ አያስፈልግም ወይም መፍትሄው የበለጠ ዴሞክራሲ መስጠት እንጂ ማጥበብ አይደለም። የሚሉ ይበዛባቸዋል። ሕዝቦች ደግሞ አዋጁ የግድ ያስፈልገናል፤ ወጥቶ መግባት፣ ሰርቶ መብላት፣ ደክሞ መተኛት፣ የልጆቻችን ትምህርት ተስተጓጉሎብናል መፍትሔው አዋጅ ነው ብለው ያምናሉ።
አዋጁ መጽደቅ ያለበት መሆኑን የምናምን ዜጐች ደግሞ « አይፀድቅ ይሆን?» የሚል ስጋት ውስጥ ነው የከረምነው። የፓርላማ አባላት ለአዋጁ መጽደቅ ድምጽ እንዳይሰጡ ወይም አዋጁን እንዳይደግፉ በማኅበራዊ ድረ ገፆችና በስልክ ጭምር ማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያዎች ሲረጩ ሰንብተዋል። በፓርላማ አባላት ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ፣ ቤት ንብረታቸው ላይ አደጋ እንደሚጥሉ ሲዝቱና ሲያሸማቅቁ ከርመዋል። አዋጁ የፀደቀው ይህን ሁሉ ፈተና አልፎ ነው። በእርግጥ በፓርላማው ውስጥ ከዚህ በፊት በነበሩት ዓመታት ሂደት ባልታየ መጠን 88 ተቃውሞዎችን አስተናግዷል። ብዙ ነው።
ተቃውሞው የነውጠኞቹ ማስፈራሪያና ዛቻ ይሁን ወይም በፓርላማው ውስጥ ያለው ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብና የአባላቱ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አጠቃቀም እድገት አሳይቶ ይሆን? በአዋቂዎች መጠናት ሊኖርበት ይችላል። መከራከሩ ጥሩ ነው። መቃወሙም ጥሩ ነው። ተቃውሞው ግን ብሔር ተኮር ሳይሆን መርህ ተኮር መሆን አለበት። በአንድ ብሔር ወገንተኝነት አካሄድ አገር ሲታመስ የከረመው አንሶ አሁን ፓርላማ እስከመግባትና እስከ ማመስ ድረስ እንዲዘልቅ ፊት ሊሰጠው አይገባም። አሁን የምንመራበትን ስልት አውቀናል። እስከጊዜው ድረስ (ቢያንስ ለ6 ወር) የምንመራው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሆኑን አረጋግጠናል።
የአስቸካይ ጊዜ አዋጁ ክብደትና ቅለት፣ ርዝመትና እጥረት የሚወሰነው በእኛው የውስጥ ሁኔታ አይነት ነው። ሰላምና ፀጥታ ከሰፈነ ሊያዋጣን ይችላል። ይህ ካልሆነ ግን ኮማንድ ፖስት ማንኛውንም ርምጃ ይወስዳል። ከኢሰብአዊነት በመለሰ የሚያግደው የለም። ከዚያም ከባሰ አገሪቱ ወደ ወታደራዊ አስተዳደር የማትሸጋገርበት ምክንያት አይኖርም። የትም ፍጭው ሰላሙን አምጭው! የባሰ እንዳይመጣ እንፀልይ! ሰላማችንን በጋራ እናረጋግጥ።
በቀጣይ የሚነሳው ጉዳይ «ማን ይምራን?» የሚለው ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ለፖለቲካ ፍጆታ ካልሆነ በቀር የሕዝቡ ጥያቄ የመሪ ማንነት ጥያቄ አይደለም። ማንም ይምራ ማን የሕዝቡ ችግር አይደለም። አቶ ኃይለማርያም የተነሱት በሕዝብ ጥያቄ አይደለም። ንፁህና የታረሙ ምሁር መሪ መሆናቸውን ሕዝቡ ያውቃል፤ ያምናል። የሕዝቡ ጥያቄ የዕለት ተዕለት ኑሮው ነው። ምግብ፣ ውሃ፣ መጠለያ፣ ሥራ፣ የልጆች ዋስትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ነው። ችግሩ አንዱ በይ! ሌላውን ተመልካች ያደረገው ሥርዓት ነው።
ሕዝቡ የሚፈልገው የሥርዓት ለውጥ እንጂ የግለሰቦች መቀያየርን አይደለም። የሚመራን ሰው ይህን የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት የሚችል መሆን አለበት። «እየሠራን እንታደሳለን። እየታደስን እንሠራለን» ማለት እዚያው በዚያው እንደ ፕላስቲክ ጣሳ እየተገላበጥን (ሪሳይክል እያደረግን) እንቀጥላለን ማለት አያዋጣም። ጠጋ ብሎ ላስተዋለው ሕዝቡን ካንገሸገሹት አማርኛዎች ዋነኞቹ «ተሀድሶ፣ ስልጠና፣ ግምገማ፣ ስብሰባ... ምናምን ወዘተ» የሚሉት ናቸው። 25 ዓመት ሙሉ ተሀድሶ፣ ሥልጠና፣ ግምገማ... ለሕዝብ ያስገኘለት ተጨባጭ ጠቀሜታ ምንድን ነው? ምንም! እዚያው እርስ በርስ ለመጠቃቀምና ለዕድገት መወጣጫ እንዲሆን እገሌ ሥልጠና ወስዷል፤ እገሌ ተሀድሶ ገብቷል፤ እያሉ እርስበርሳቸው ከፍ ዝቅ ሊደራረጉበት ካልሆነ በቀር ለሕዝብ ያስገኘው ፋይዳ የለም።
በየጊዜው «ለከፍተኛ አመራሮች፣ ለመካከለኛ አመራሮች፣ ለፈፃሚዎች... እየተባለ የሀገር ሀብት ከማሟጠጥ በስተቀር ለሕዝብ ያስገኘው ለውጥ የለም። በየጊዜው የሚካሄደው ተሀድሶ፣ ስልጠናና፣ ስብሰባ በማን ገንዘብ ? በማን ኪሳራ? በማን ወጪ? ነው። ትራንስፖርት፣ አልጋው፣ ሆቴሉ የውሎ አበሉ... ደሃው ሕዝብ መቀነቱን እየፈታ ከሚከፍለው ግብር ላይ የሚወጣ መሆኑ የታወቀ ነው። ይህ ወጪ ለሌላ ሕዝባዊ ጠቀሜታ መዋል አለበት። ይህም ቢሆን አረረም መረረም አንድ መሪ መኖር አለበት። የጠቅላይ ሚኒስትርነት ወንበር ይሄን ያህል የሚመኙት ነገር አይደለም። እሾህ ላይ መቀመጥ ነው! እሳት ላይ መጣድ ነው! ይሁን እንጂ «እሆናለሁ» ያለ ሰው መወዳደር ይችላል።
አሁን ለጊዜው ተለይተው የታወቁ ሦስት ሰዎች አሉ። አብይ አህመድ፣ ደመቀ መኮንን፣ ሽፈራው ሹጉጤ! ሌላ ሰው ከውጭ አምጥቶ መሾም አይቻልም። በሕገመንግሥቱ ዝግ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል ይመረጣል! የምክር ቤት አባል ያልሆነ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆን እድል የለውም። የኢህአዴግ ነገር አይታወቅም ሌላ ያልተጠበቀ ሰው ካላመጣብን በቀር ለጊዜው ያሉት ሦስቱ ናቸው።
ማን ይመረጥ ይሆን? አደገኛ ጥያቄ ነው! ጠንቃቃ ምላሽ የሚፈልግ ጥያቄ ነው። ኦሮሚያ ወንበሩን ለመያዝ ቆርጦ ተነስቷል። አሁን ጊዜው የእኔ ነው። እያለ ነው። ቄሮ ከጐጉ ነው። ከመደበኛው የሕግ ማስከበር አግባብ በላይ የሆነ ቡድን ነው። አብይ ተመረጠ ማለት ሦስቱም ሥልጣኖች ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አፈጉባዔ፣ ፕሬዚዳንት በኦሮሚያ መያዙ ነው። የሚያስኬድ አይመስልም። የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ለማግኘት ሲባል ፕሬዚዳንቱ በፈቃዳቸው ሥልጣን እንዲለቁ ማድረግ ወይም አባዱላ ከዚህ በፊት ያስገቡትን የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ አቧራውን አራግፈን ስናጠናው ቆይተናል፣ውሳኔ ላይ ደርሰናል። በጥያቄያቸው መሠረት ይልቀቁ ብለናል ማለት ይቻላል። ማንኛውም ግለሰብ የትኛውም ብሔራዊ ድርጅት ወክሎ ቀርቦ ቢመረጥ አይከፋንም፦
* የሚመረጠው ሰው ግን አገራችን የሚያስፈልጋት በራሷ ባህልና ታሪክ ላይ የተመሠረተ የመንግሥት አስተዳደር ሥርዓት እንጂ ከየሀገሩ ተለቃቅሞ እንደተፈለገ ተተርጉሞ በተጫነብን ሰነድ አማካይነት የሚንቀሳቀስ ግዑዝ አሠራር አለመሆኑን የተገነዘበ መሆን አለበት።
* የሚመረጠው ሰው ሕዝባችንን ዛሬ በደረሰበት የዕድገት ደረጃ በድሮው ዘዴ መምራትና ማስተዳደር የማይቻል መሆኑን የተገነዘበ መሆን አለበት።
* የሚመረጠው ሰው ሕዝቡ እስከአሁን መንግሥት ላይ እምነት ያጣ መሆኑን ተረድቶ ሕዝብና መንግሥት የሚተማመኑበትን ሥርዓት ለመዘርጋት ቁርጠኛ አቋም ያለው መሆን አለበት።
* የሚመረጠው የአገሪቱ ችግር የዘዴ /ሜቶዶሎጂ/ የአስተዳደራዊ አሰራር ጉድለት፣ የቴክኒክ ችግር ሳይሆን የመሠረታዊ መርሆዎች ችግር መሆኑን ያጤነ መሆን አለበት። ችግራችን የሥርዓት ችግር ነው፤ የቴክኒክ አይደለም። አዲስ አቅጣጫ መቀመጥ አለበት።
* የሚመረጠው ሰው ልበ ሙሉ፣ ደፋርና ቆራጥ መሆን አለበት። «አይነኬ» ሆነው ያሉትን «እንደራደርባ ቸውም» የሚባሉትን ጉዳዮች እንደገና መመርመር መቻል አለበት። ከሕገ መንግሥቱ ጀምሮ የሚሻሻሉ አንቀፆች ወይም አገላለፆች ካሉ የአዋቂዎች ቡድን /ኮሚሽን/ ተቋቁሞ እንዲመረምር እድል ይሰጠው። የፌዴራሊዝም ሥርዓት በሕዝቦች አንድነት ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ካለም ይመርመር፤ ይታይ፤ ይፈተሽ። እንደ ፀረ ሽብር ያሉ አንዳንድ ሕጐችም ይታዩ። ሁሉም ዓለም የሚጠቀምበት ነው አትበሉን። ለእኛ እንዲሆን በልካችን ይሰፋልን!
* የሚመረጠው የአገሪቱ ሕዝብ አገሪቱ ከምታመነጨው ገቢ እኩል ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ መቻል አለበት። የመሬቱም ሆነ የልማቱ ተጠቃሚነት በፍትሐዊነት ሊከበር እንዲችል መሥራት አለበት። አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ለቃቃሚ የሚሆንበት ሥርዓት መታረም አለበት። ዋናው ነገር ግን ሰላም ነው። የትም ፍጭው ሰላሙን አምጭው።

ግርማ ለማ

Published in አጀንዳ
Sunday, 11 March 2018 01:05

ጥቂት ስለአፈጣጠር

ዓለማችን በሚያስደንቁ ተፈጥሯዊ ነገሮች የተሞላች ነች። ልጆች በሳይንሳዊ ምርምር እና የሰው ልጅ በግሉ ሁሉንም የተፈጥሮ ሚስጥሮች መረዳት አለመቻሉ ምን ያህል ረቂቅ (ጥልቀት ያለው) እንደሆነ የሚያስረዳን ነው። እኛ የሰው ልጆች ደግሞ ከሁሉም ፍጥረታት ለየት የሚያደርገን ዓለማችን ላይ ያሉ ልዩ ነገሮችን ለመረዳት በምናደርገው ጥረት እና ጉጉት ነው። ታዲያ የሰው ልጆች ፍላጎትን ተመስርተን አመቺ በሆነ አጋጣሚ ሁሉ ለእናንተ በዚህ ገፅ ላይ ስለ ተፈጥሯዊ ባህሪ እንነግራችኋለን። ለዛሬ «ንስር» ስለሚባል በራሪ የአእዋፍ ዘር አስገራሚና ልዩ ባህሪያት እንንገራችሁ።

ሀይለኛ ከሚባሉት አዳኝ እንስሳት መካከል አንዱ ነው። ንስሮችን ጭልፊት የሚያስብላቸው የሚገሉበት ጥፍራቸው ነው።
ንስሮች በቅጽበት ነገሮችን ያነሳሉ፤ እንዲሁ በጥፍራቸው የሚያድኑትን ነገር በቅጽበት ይገሉታል። ንስሮች በራሪ እንስሳት ሲሆኑ፤ የሚያድኑት 24 ካሬ ሜትር ክልል እንደ ጠረፍ ጠባቂ እየበረሩ የሚታደነውን በመፈለግ ነው። ቁልቁል ሲወረወሩ ደግሞ320ኪሎ ሜትር በመሄድ ነው።
በአንድ ጊዜ ሚዳቋን የሚያክል እንስሳት ማንሳት ይችላሉ። በቀለማቸው ወርቃማ ሲሆኑ፤ በአብዛኛው ጥንቸል፣ ሽኮኮና የመሳሰሉ እንስሳትን በማደን ይመገባሉ። የንስር ክንፍ ውስጥ አጥንት የሚባል ነገር የለም። ይህ ደግሞ በቀላሉ እንዲበሩ ያስችላቸዋል።
ክብደታቸውና ጥንካሬያቸው የሚመነጨው ደረታቸው ውስጥ ካሉት የመብረሪያ ጡንቻዎች ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ለመቆምና ለመንሳፈፍ ሲሞክሩ አየር ወደላይ እንዳያስቀራቸው ያግዛቸዋል። ንስሮች የሚያድኑትን እንስሳ ከመቶ ሜትር ርቀት ላይ መመልከት ይችላሉ። ከአዕምሯቸው የሚበልጥ ሉል ዓይናቸው ላይ አላቸው።
የንስር ላባ ልክ እንደሰው ልጅ የተለያዩ ጣቶች ልዩነት አላቸው። የክንፋቸው ስፋትም 2ሜትር ሲሆን፤ ትልቅ፣ ፈጣንና ሀይለኛ አዳኝ ከሚባሉት መካከል ይመደባሉ። ጥፍሮቻቸው የተለጠጡ ሲሆን፤ ጫፋቸው ቆልማማ ነው። አይናቸው ሦስት እጥፍ አይታዩም ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን ከርቀት የመመልከት አቅም አለው።

 

ተፅዕኖ ፈጣሪዎች

 

ቀኝ አዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ዘ ብሔረ ቡልጋ

ልጆች እንዴትናችሁ በዚህኛው ዓምድ ላይ ታዋቂ ፈላስፋዎችን፣ ሳይንቲስቶችን እና ለዓለም ስልጣኔ የበኩላቸውን ድርሻ የተወጡ ሰዎችን እናስተዋውቃችኋለን። እስቲ ልጆች የዓለም ስልጣኔ እዚህ እንዲደርስ ትልቅ ድርሻ አላቸው የምትሏቸውና ከዚህ ቀደም እናንተ ከምታውቋቸው ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን አስታውሱ። ሊደነቁ ይገባል አይደል? መልካም ልጆች! ሁሉም ሰው በእኩል ደረጃ ለዓለም መሰልጠን እና ዘመናዊ መሆን ድርሻ ባይኖረውም ነገር ግን የራሱን ኃላፊነት መወጣት ይኖርበታል።
አቅማችን ከተጠቀምንበት አዲስ ነገር ለመስራት፣ አዳዲስ አስተሳሰቦችን ለማፍለቅ እና ለመፍጠር እኛ የሰው ልጆች ከሌላው የዓለም ፍጡር በተለየ መንገድ ልዩ ስጦታ አለን። ታዲያ እናንተ ምን አሰባችሁ? አዲስ እና ጠቃሚ ነገር ለአገራችሁ ብሎም ለዓለም ህዝብ ለመስራት ተዘጋጃችሁ? መልካም ለዛሬ ጥሩ ምሳሌ እንዲሆናችሁ ስለ የቀኝ አዝማች ተስፋ ገብረ ስላሴ እናወራችኋለን።
1. ቀኝ አዝማች ተስፋ በሰሜን ሸዋ ቡልጋ በሚባል አገር በ1895 ዓ.ም ታህሳስ 24ቀን ተወለዱ።
2. በአባታቸው አማካኝነት በአራት ዓመታቸው ፊደል ቆጥረዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚሰጡ የቤተ ክህነት ትምህርትም ተምረዋል።
3. ቀኝ አዝማች ተስፋ ቤተክርስቲያንን በድቁና እያገለገሉ የወላጅ አባታቸውን አርዓያ በመከተል ከእፅዋት ቀለም አዋህደው፣ ከሸምበቆ ብዕር ቀርፀው፣ የፍየል ቆዳ ፍቀውና አለስልሰው በመጻፍ «ሀ..ሁ… ዕውቀት ይስፋ፣ ድንቁርና ይጥፋ - ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ» የሚል መፈክር ተጠቅመው ወደ ማህበረሰቡ የፊደል ገበታን ያስገቡ የመጀመሪያው ሰው ናቸው።
4. ብራና በማዘጋጀትም ቀለሙን ከልዩ ልዩ እጽዋት እያዘጋጁ በብዕራቸው የተለያዩ የሀይማኖት መጸሐፍትን እያባዙ ለአንባቢያን አቅርበዋል።
5. በ1921ዓ.ም ደግሞ የኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ የነበሩት አቡነ ቄርሎስ በቤተክህነት ግቢ ቦታ ስለሰጧቸው በሰው ሀይል የሚሰራ የማተሚያ ማሽን ገዝተው ከፊደል ገበታ ጀምሮ ያሉትን የንባብ መማሪያ፣ የጸሎትና የሃይማኖት መጸሐፍት እንዲሁም በራሳቸው የተደረሱ መጸሐፍትና ግጥሞች ሌሎች ጽሁፎችን ያትሙ ነበር።
6. በተጨማሪ የዮፍታሔ ንጉሴንና የሌሎች ተዋቂ ደራስያንን ሥራ አትመዋል። በዚህም ለኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ እድገት አስተዋጽኦ አድርገዋል። በተለይ ግን ያዘጋጇቸው በነበሩት ልዩልዩ የፊደል ገበታዎች ያልተማረ ኢትዮጵያዊ የለም ማለት ይቻላል።
7. ቀኝ አዝማች ተስፋ ገብረስላሴ ግንቦት 26 ቀን 1992ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በወቅቱ የ97 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ነበሩ።

ፅጌሬዳ ጫን ያለው

 

 

 

Published in ማህበራዊ
Page 1 of 2

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

            በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።