በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ የሰፈረው ድምፃዊ Featured

13 Feb 2017

ሙዚቃ የዓለም ቋንቋ ነው። ታዲያ መክሊታ ቸውን በመጠቀም ከራሳቸው አልፈው የተመልካቾ ቻቸውንና የአድማጮቻቸውን ቀልብ መግዛት የቻሉ ዕውቅ አቀንቃኞች እንዳሉ አይካድም። ሥራችን ከሥራነት ባለፈ  ባልጠበቅነው ሁኔታ አነጋጋሪ ሲሆን ደግሞ የበለጠ ደስታን ያጎናጽፋል። ለሠራነው ሥራም በርታ፣ እሰየው በዚሁ ቀጥል መባልም ለበለጠ ሥራ ያነሳሳል።

ከሰሞኑ የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ መስፈር የቻለው ጄ ባልቪን በኒውዮርክ የወንዶች ፋሽን ሳምንት አምባሳደርነት እንዲሁም «ጊንዛ» የሚል መጠሪያ ባለው የላቲን ዘፈኑ የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሊሰፍር ችሏል።

ዘፋኙ የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሊሰፍር የቻለው በአሜሪካ ሞቅ ያሉ የላቲን ዘፈኖች የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በመቆየቱ ክብረ ወሰኑን ሊሰብርና ስሙ ሊሰፍርለት ችሏል። «ጊንዛ» የሚል መጠሪያ ያለው ይህ ዜማው ይህን ክብር ሊያሰጠው የቻለው በሚገርም ሁኔታ ለ22 ሳምንታት በደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ ሊቆይ በመቻሉ ነው።

ነጠላ ዜማው እ.አ.አ በ2015 በደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከፍተኛ ደረጃን ይዞ የነበረው «ኢነርጂያ» በተሰኘው አልበሙ ላይ የተለቀቀ ነው። በወቅቱ ይህ አልበሙ እ.አ.አ ከጥቅምት 11/2015 እስከ የካቲት 12/ 2016 ለአስር ወራት ተቆጣጥሮት ነበር።

ጊንዛ አንደኛ ከነበሩት የባልቪን ስድስት ነጠላ ዜማዎች መሀል አንዱ ነው። ይህ ሙዚቃው ልንክደው የማንችለው የዚህ ትውልድ የሬጌ ስልት መሪ እንዲሆን አድርጎታል። በዚህም ይህ ዜማ በዓለማችን የተለያዩ ከተማዎችን በማጥለቅለቅም የላቲን ሙዚቃ ግንባር ቀደም እንዲሆን ረድቶታል።

የኮሎምቢያ ተወላጅ የሆነው ይህ አቀንቃኝ ከተለያዩ ዕውቅ የዓለማችን ዘፋኞች ጋር   የመሥራት ዕድልን አግኝቷል። ከእነዚህም ውስጥ አሪያና ግራንዴ፣ ሜጀር ሌዘር እንዲሁም ጀስቲን ቢበር ተጠቃሽ ናቸው። በቅርቡ ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከፍተኛ ቦታ የያዘው ዘፈኑ ሳፋሪ ላይም ከፍሪያ ዊሊያምስ ጋር ሠርቷል።

ጄ ባልቪን በዩኤስ ኒውዮርክ በሚገኘው የዓለም ድንቃድንቅ ወይም አስገራሚ መዝገብ ዋና ቢሮ በሠራው ሥራ ለሚደረግለት ዕውቅና ለማግኘት በገባበት ጊዜም በህይወቱ ብዙ ነገር ያስብ እንደነበር ተናግሯል። «ነገር ግን ይህ ፍፁም ያልጠበቅኩት ነገር ነው። በሙዚቃ ሥራዬ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ  እሰፍራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም» በማለት ለሽልማቱ ክብር እንደሚሰማውና ደስተኛ እንደሆነም ገልጿል። ቀጣይ ብዙ ህልም እንዳለው የሚያመላክት ንግግሩን ጠቁሟል።

በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ በዳኝነት የምትሳተፈው ሳራህ ኬሰን ክብሩን ስታበረክትለት «የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ጄ ባልቪን በሠራው የሚያስደምም ሥራ ይህን ዕውቅና መስጠቱ ይበልጥ ደስታን ይሰጠዋል» በማለት ተናግራለች። ቀጥላም «ይሄን የዓለም ክብረ ወሰን መውሰድ የመጨረሻው እንደማይሆን እናስባለን» ስትል ሙዚቀኛው ቀጣይ ያለውን ተስፋ አመላክታለች።

ፍዮሪ ተወልደ

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

            በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።