ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ Featured

ለፍጻሜው የሕዝቡን ተሳትፎ የሚጠብቀው የሕዳሴ ግድብ፤

በግማሽ የበጀት አመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ባለፉት ስድስት አመታት ከ9ነጥብ2ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ ለግንባታው መዋሉንም አስታወቀ፡፡

    የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብረሃም ለጋዜጣው ሪፖርተር  እንደገለጹት ጽህፈት ቤቱ ህዝብን የሚያሳትፍ የተለያዩ የገቢ ማስገኛዎች በማዘጋጀት በበጀት አመቱ አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ከያዘው ዕቅድ አራት መቶ ሚሊዮን ብር ሰብስቧል፡፡ቀሪውን ለመሰብሰብም በሚቀጥሉት ጊዜያቶች የህዝባዊ ንቅናቄ ሥራዎች ዝግጅት አድጓል፡፡

     የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሠረት የተጣለበትን ቀን አስመልክቶ ተከታታይ የህዝባዊ ንቅናቄ ሥራዎች እንደሚሰሩ የገለጹት አቶ ኃይሉ አብረሃም ከንቅናቄው አንዱ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምስረታና የሴቶች ቀን«ማርች ኤይት»ን በማስተሳሰር የካቲት 26ቀን2009ዓም በመላ ሀገሪቱ የሚካሄደው የሩጫ ውድድር መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በሩጫው ከ150ሺህ በላይ  ሴቶች እንደ ሚሳተፉና ውድድሩም ከሴቶችና ህጻናት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡

    ሴቶች ለግድቡ አሻራቸውን እንዲያሳርፉና እግረ መንገድም የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያዳብሩ የሚያግዝ ዝግጅት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ኃይሉ ለሩጫ ውድድሩ በሰው አንድ መቶ ብር ዋጋ ያለው ቲሸርት መቅረቡንና ከሽያጩም ጥሩ ገቢ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡በሚቀጥሉት ቀናትም በመላ ሀገሪቱ የቦንድ ሽያጭ፣ሽልማት የሚያሰገኝ ቶምቦላ፣የስነ-ጽሑፍ ምሽት፣የፓናል ውይይትና የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄዱ አስረድተዋል፡፡ህዝቡ ለግድቡ ግንባታ አሻራውን በማሳረፍ የቁጠባ ባህሉን እንዲያዳብር በሚደረገው የህዝባዊ ንቅናቄ ሥራ ከህዝቡ የሚሰጠው ምላሽ አበረታች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

         ከድጋፉ ጎን ለጎን ግድቡን ለመጎብኘት ያለው ፍላጎትም ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ኃይሉ በበጀት አመቱ አምስት ወራት ብቻ ከአምስት ሺህ ሰዎች በላይ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡በአጠቃላይ እስካሁን ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች መጎብኘታቸውን አመልክተዋል፡፡ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሠረት የተጣለበት 6ኛ አመት የካቲት 24ቀን 2009ዓ.ም. በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡

ለምለም ምንግሥቱ

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

የጎብኝዎች ብዛት

0002410896
TodayToday5137
YesterdayYesterday7537
This_WeekThis_Week14567
This_MonthThis_Month100001
All_DaysAll_Days2410896

            በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።