ከባለሀብቶችና ከልማት ድርጅቶች ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዢ መፈፀሙ ተገለጸ Featured

በውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሀብቶችና መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የ41 ሚሊዮን 923 ሺ 900 ብር የቦንድ ግዢ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስም መፈጸሙን የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ 

      ሚኒስቴሩ የቦንድ ግዥውን ለፈፀሙት ትናንት በሸራተን አዲስ ሆቴል ባደረገው የምስጋናና የእውቅና መርሐ ግብር ላይ የውሃ፣ የመስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደተናገሩት፣ከባለሀብቱና ከሚኒስቴሩ የተውጣጣና ዘርፉን  የሚያስተባብር ዓብይ ኮሚቴ በማቋቋም በተከናወነው ተግባር የቦንድ ግዢ እንዲፈፀም ተደርጓል፡፡ በዚህም የቦንድ ግዢ ለመፈፀም ቃል ከገቡ 193 ባለሀብቶች 55 ሚሊዮን 716 ሺ 115 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ150 ባለሀብቶች የ41 ሚሊዮን 923ሺ 900 ብር የቦንድ ግዢ ተፈፅሟል፡፡ በዚህ መሠረት  የዕቅዱን 75 በመቶ ማሳካት አስችሏል፡፡

        «ቦንድ ለመግዛት ቃል ገብተው ሙሉ በሙሉ ያላሳኩ ባለሀብቶች በመኖራቸው በቦንድ ግዢ ሂደት ውስጥ የአፈፃፀም ክፍተት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል» ያሉት ሚኒስትሩ፣ ከ150 ባለሀብቶች መካከል 105ቱ ቃላቸውን ጠብቀው ሙሉ በሙሉ ቦንዱን መግዛታቸውን ጠቁመዋል፡፡ የቦንድ ግዢውን ጀምረው ያላጠናቀቁ ባለሀብቶችም ቃላቸውን እንዲያከብሩም አሳስበዋል፡፡ ቦንድ ድጋሚ ለመግዛት የሚፈልጉ ባለሀብቶች እንደሚበረታቱም ገልጸዋል፡፡

      ከዚህ በተጨማሪም፣ በውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ዘርፎች የሚሰማሩ አዳዲስ ባለሀብቶች ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ቦንድ በመግዛትና የግደቡን ግንባታ እውን በማድረግ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

     ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በአምስት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ እስከአሁን ድረስ ለግድቡ ግንባታ ዘጠኝ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡

ዑመር እንድሪስ

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

የጎብኝዎች ብዛት

0002566273
TodayToday2286
YesterdayYesterday6567
This_WeekThis_Week38094
This_MonthThis_Month100001
All_DaysAll_Days2566273

            በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።