ህፃናትና ወጣቶች የህዳሴ ግድብ ግንዛቤያቸውን በንባብ ሊያዳብሩ ይገባል Featured

አውደርዕዩ በተከፈተበት ወቅት

 

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ህፃናትና ወጣቶች ግንዛቢያቸውን በንባብ ማዳበር እንዳለባቸው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ፅህፈት ቤቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ጋር በመተባበር ‹‹ማንበብ አእምሮን፣ታላቁ የህዳሴ ግድብ አገርን ያበለጽጋል›› በሚል መሪ ቃል በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ያዘጋጀው የንባብ፣ የመፃህፍት አውደ ርዕይና ሽያጭ ሳምንት ትናንት ተጀምሯል፡፡

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የፅህፈት ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍቅርተ ታምር እንደገለፁት፤ የታላቁ የህዳሴ ግድብና ንባብ ሳምንት ዋና ዓላማ የግድቡን ግንባታ በተመለከተ በህብረተሰቡ ውስጥ የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠር ብሄራዊ መግባባቱን የበለጠ ማጠናከር ነው፡፡ ንባብ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ብሎም ለሃገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ለማመላከት ይህ አይነቱ ዝግጅት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ህፃናትና ወጣቶች እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ግንዛቤያቸውን በንባብ እንዲያሳድጉ ማድረግ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ድጋፍና ተሳትፎ እንደሚያጠናክር ምክትል ዳይሬክተሯ አስታው ቀዋል፡፡በተለይ የህፃናትና ወጣቶችን የንባብ ባህል በማዳበር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አገራዊና ክፍለ አህጉራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፋይዳዎችን ለማስገንዘብ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተናግረዋል፡፡

አውደ ርዕዩና የሽያጭ ሳምንቱ እስከ መጪው ቅዳሜ የሚቆይ ሲሆን ፣በርካታ የመፃህፍት መፅሃፍት እንባቢያንና ነጋዴዎች የሚታደሙበት መሆኑም ታውቋል፡፡

 

አስናቀ ፀጋዬ

 

 

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

            በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።