‹‹ጉብኝቱ በቡድን ቢሆን ይመረጣል›› የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት Featured


አዲስ አበባ፡- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ከተናጥል ይልቅ በቡድን ጥያቄ ቢያቀርቡ ተሻለ መሆኑን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ተሳትፎ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽሕፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም በተለይ ለጋዜጣው ሪፖርተር እንደገለፁት ፤ ዜጎች ግድቡን በቦታው በመገኘት የመጎብኘት መብት አላቸው ፡፡
የግድቡ ግንባታ በየዓመቱ በበርካታ የአገሪቱ ዜጎች እየተጎበኘ መሆኑን አቶ ኃይሉ ጠቅሰው፣ በጉብኝቱም በዋናነትም የመንግሥትና የግል ሠራተኞች እየተሳተፉ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡እስከ አሁን ከ 260 ሺ በላይ ዜጎች ግድቡን መጎብኘታቸውንም ተናግረዋል፡፡
እንደ አቶ ኃይሉ ማብራሪያ፤በዘንድሮው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በክረምት ወቅት ከፍተኛ ዝናብ በመኖሩ በተወሰነ ደረጃ የጎብኚዎች ቁጥር የቀነሰ ሲሆን፣ በሁለተኛው ሩብ ዓመት በተለይም ከህዳር ወር ጀምሮ 5ሺ 921 የሚሆኑ ዜጎች ግድቡን ጎብኝተዋል፡፡
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ግድቡን በባለቤትነትና በገንዘብ ድጋፍ እየገነባ መሆኑን ጠቅሰው፤ የደረሰበትን የግንባታ ደረጃ የማሳየት መብቱን በመጠቀምም በራሱ ወጪ ግድቡን ለመጎብኝት ወደቦታው እየሄደ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
እስከ አሁን ባለው ሂደትም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ገንዘብ በማዋጣት ወይም ከመስክ ጉብኝት በጀት ወጪ በማድረግ ጉብኝቱን ሲያካሂዱ መቆየታቸውን ዳይሬክተሩ ገልፀው፤ ሌሎችም በተመሳሳይ ጉብኝቱን ማካሄድ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
«ግድቡ የህዝቡ እስከሆነ ድረስ ማንኛውም ዜጋ ራሱን ችሎ የመጎብኘት መብት አለው›› አለው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ጉብኝቱን ለማድረግ ከጽሕፍት ቤቱ ጋር መነጋገርና ከሚኖሩበት ወረዳ ወይም ክፍለ ከተማ ደብዳቤ ማጻፍ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡ ይህም የሚደረገው የጎብኚዎቹን ህጋዊነት ለማረጋገጥ ሲባል ነው ያሉት አቶ ኃይሉ፣በክልል የሚኖሩና ግድቡን መጎብኝት የሚፈልጉ ዜጎችም በየክልሉ ከሚገኙ ጽሕፈት ቤቶች ጋር በመሆን ጉብኝቱን ማመቻቸት እንደሚችሉም አስታ ውቀዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ማብራሪያ፤ ጽሕፈት ቤቱ ጉብኝቶችን ማመ ቻቸትና ማስተባበር ዋና ሥራ ነው፡፡ ዜጎች ግድቡን ቦታው ድረስ ተገኝተው ማየታቸው በተለይም በግንባታው ላይ ላሉ ሠራተኞች ከፍተኛ መነቃቃት ይፈጥራል፡፡ይህ ደግሞ ሠራተኞች በከፍተኛ ሞራልና ወኔ ተነሳስተው ሥራቸውን እንዲሰሩ ከማድረግም በተጨማሪ የበለጠ የህዝብ ኃላፊነት እንዳለባቸውም እንዲያውቁ አድርጓል፡፡
ጉብኝቱን ተከትሎ ለቤኒሻንጉል ህዝብና ለአካባቢው ተወላጆችም የተለያዩ የሥራ ዕድሎችንና የገቢ ምንጮችን መፍጠሩንም አቶ ኃይሉ ጠቁመው፣ ጎብኚዎችም ግድቡን ከመጎብኘት በዘለለ አገራቸውንም የማየት አጋጣሚ እንደፈጠረላቸው ጠቅሰዋል፡፡
እስከ አሁን ባለው መረጃም ዳያስፖራዎች፣የአገር ውስጥና የውጭ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙ ያዎች እንዲሁም የተለያዩ የመንግሥትና የግል ድርጅት ሠራተኞች ግድቡን መጎብኘ ታቸውም ተገልጿል፡፡

አስናቀ ፀጋዬ

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

            በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።