‹‹የደመራ በአል አከባበር የአገሪቱን ባህልና እሴት የሚያሳይ ነው››- ቱሪስቶች Featured

በደመራ በዓል በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ታድመዋል ፤

 

የደመራ በአል አከባበር ከሃይማኖታዊነቱ በዘለለ የአገሪቱን ባህልና እሴት የሚያሳይ መሆኑን በበአሉ ላይ የተገኙ የውጭ አገር ዜጎች ገለፁ፡፡

በመስቀል አደባባይ የተከበረውን የደመራ በዓል የታደሙ የውጭ አገራት ቱሪስቶች ለጋዜጣው ሪፖርተር እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በርካታ ባህላዊ አከባበር ያላቸው በአላት አሏል። ከዚህም ውስጥ የደመራ በአል አከባበር ልዩ የሆነና ከሃይማኖታዊነቱ በዘለለ የአገሪቱን ባህልና እሴት የሚያሳይ ነው፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የምርምር ስራ ለመስራት ከስዊድን እንደመጡ የሚናገሩት ሚስተር ጃን ብራውን ሜድሪክ፤ በደመራ በአል አከባበር ላይ የሚታዩት ሃማኖታዊ ትርኢቶች እንዳስደነቃቸው ገልፀዋል፡፡ በአገሪቱ ያሉትን ባህሎች ባላቸው ጊዜ ለመመልከትም ፍላጎታቸውን እንዳሳደገው ጠቁመዋል፡፡

በአገሪቱ ያሉትን የቱሪስት መዳረሻዎች በማስተዋወቅ ረገድ ሰፋ ያሉ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው የተናገሩት ሚስተር ጃን ብራውን፤ ደመራና ሌሎች ሃይማኖታዊ በአላት አከባበር ለየት ያለና ባህሉን ጠብቆ የሚሄድ በመሆኑ ለሌሎች የአገራቸው ሰዎች እንደሚያስተዋውቁና መጥተው እንዲያዩ እንደሚናገሩ ጠቅሰዋል፡፡

ሌላዋ አስተያቷን የሰጠችው ከአሜሪካዊቷ ሚስ ፓወላ ኖርማን፤ የደመራ በአል ለማክበር ለሶስተኛ ጊዜ እንደተገኘችና የበአሉ አከባበር ሁሌም እንደ አዲስ እንደምትመለከተው ገልፃለች፡፡ የደመራ በአል የአገሪቱን ባህልና እሴት የሚታይበትና ሁሉም ህብረተሰብ በአንድነት ወጥቶ የሚያከብረው በመሆኑ የተለየ ደስታ እንደሚፈጥርባት ተናግራለች፡፡

ሚስተር ጃሽ ካትሪን ከአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ የመጣ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን እንዳየና በቆይታውም አክሱምና ላሊበላ በመሄድ መጎብነቱን ተናግሯል፡፡ የደመራ በአል አከባበር ከሃይማኖታዊነቱ በተጨማሪ የአገሪቱን ባህል የሚያሳይ መሆኑን እንደተረዳ ተናግሯል፡፡ የቤተክርስቲያን ዘማርያን የሚያቀርቡት መዝሙር ለበአሉ ልዩ ውበት እንደሰጠውም ጠቁሟል፡፡

በአፍሪካ ከጎበኛቸው አገራት ኢትዮጵያ ልዩ እ

ንደሆነችና በተለይ ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው በአላት አከባበር ድምቀት ያለው መሆኑንም ገልጿል፡፡ ወደ ሚኖርበት ከተማ ሲመለስም ኢትዮጵያን ለጓደኞቹ እንደሚያስተዋውቅና መጥተው እንዲጎበኟት ግፊት እንደሚያደርግ አመልክቷል፡፡

 

መርድ ክፍሉ

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

            በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።