የስፖርት ዓለም አስደናቂ ታሪኮች

27 Jul 2015

ለአሸናፊዎች ይሰጡ የነበሩት የብር ሜዳሊያዎች፤

«ወርቃማው ልጅ» በመባል የሚታወቀው አሜሪካዊው የውሃ ዋና ተወዳዳሪ ሚቼል ፊሊፕስ ሀገሩን ወክሎ በተሳተፈባቸው ሦስት ኦሎምፒኮች (አቴንስ፣ ቤጂንግና ለንደን ኦሎምፒኮች) 22የኦሎምፒክ ሜዳልያዎችን መሰብሰብ ችሏል። ፊሊፕስ እነዚህ የሰበሰባቸው ሜዳልያዎች ሀገራት ካገኟቸው ሜዳልያዎች ጋር በደረጃ የሚቀመጡበት ሁኔታ ቢኖር 97ሀገራትን በመቅደም 35ኛ ደረጃን ማግኘት ይችላል።

ፊሊፒንስ በበጋው ኦሎምፒክ በብዛት ብትሳተፍም አንዴም የወርቅ ሜዳልያ ማግኘት አልቻለችም። ባንግላዴሽ ፣ጉዋም፣ ቻድ፣ አንጎላ፣ ካምቦዲያ፣ ኪሪባቲ፣ ቦሊቪያ፣ ብሩኔ ፣ፊጂ ፣ ሆንዱራስና ቡርኪናፋሶም አንድም ጊዜ የኦሎምፒክ ሜዳልያ አግኝተው አለማወቃቸው ነው።

ዘመናዊው ኦሎምፒክ እአአ በ1896 በግሪኳ አቴንስ ተጀመረ። አሁን ባለንበት ዘመን በየትኛውም ውድድር አሸናፊ የሆነ ቡድን ወይም ግለሰብ የወርቅ ሜዳልያ ያገኛል። በመጀመሪያው የዘመናዊ ኦሎምፒክ አሸናፊ የሆነው ስፖርተኛ ግን የብር ሜዳልያና የወይራ ዛፍ ቅርንጫፍ እንዲሁም ዲፕሎማ ነበር የተሸለመው። ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን ያጠናቀቀ ተወዳዳሪ ደግሞ የመዳብ ሜዳልያ ከለምለም ቅጠልና ዲፕሎማ ጋር ተሸላሚ ይሆናል።

ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ የተሳተፈ ችው እአአ በ1932ቱ የሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ሲሆን፤ እስከ 1984ቱ የሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ድረስ አንድም ሜዳልያ ማስመዝገብ አልቻለችም። ቻይና በመጀመሪያው ተሳትፎዋ የላከችው አንድ አትሌት ነው። ከ52ዓመታት በኋላ 353አትሌቶችን አሳትፋ 15 ሜዳልያዎችን የግሏ ማድረግ ችላለች። ራሷ ባዘጋጀችው የ2008ቱ የቤጂንግ ኦሎምፒክ ደግሞ100 ሜዳልያዎችን አስመዝግባለች።

በወንዶች ርዝመት ዝላይ ስፖርት እአአ በ1969 በአሜሪካዊው አትሌት ማይክል ፓውል 8.95ሜትር በመዝለል ሪከርዱን መያዝ የቻለ ሲሆን፤ እስካሁን በዘርፉ ሪከርዱን ያሻሻለ ዘላይ ግን ሊገኝ አልቻለም።

 

ጸሐፊ ብርሃን ፈይሳ

 

 

 

 

 

 

 

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

            በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።