የአመልካችን የመከራከር መብት ያጠበበ የፍርድ ሂደት

28 Jul 2017

አመልካች፡- አቶ ዋቅቶላ

ተጠሪ፡- አቶ ገቢሳና አቶ ጉታ

ጉዳዩ የውርስ ንብረት ክርክርን መሠረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ናቸው ተከሣሽ ደግሞ አመልካች ነበሩ፡፡ ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘቱ ሲታይ የእናታችንን የውርስ ሀብትና ይዞታ አመልካች ይዞ ስለሚገኝ እንዲለቅልን ይወስንልን የሚል ሲሆን የአሁን አመልካች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረቡት የውርስ ሀብት ይገባናል ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን የሚገልጽ ሲሆን፤ በፍሬ ነገር ደረጃ የተመለከተው የሱልልታ ወረዳ ፍርድ ቤትም በአመልካች በቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ ብይን ሳይሰጥ በማለፉ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት በአመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን ሳይሰጥ ማለፉ ሥነ ስርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመውን የስነ ስርዓት ግድፈት በማረም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ብይን እንዲሰጥ ጉዳዩን መልሶታል፡፡

ከዚህ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የአመልካች ማስረጃ እንዲሰሙ ያዘዘ መሆን ያለመሆኑን ማብራሪያ እንዲሰጥና ትእዛዙንም አመልካች አድርሰው ማብራሪያውን እንዲያቀርቡ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ አመልካች ይህንኑ ትዕዛዝ አልፈፀሙ ም፣ይልቁንም ቀድሞ ዘርዝረው ያላቀረቡትን የመካላከያ ማስረጃ ዝርዝር አቅረበዋል በማለት መዝገቡን ዘግቶታል፡፡

በዚህ ብይን አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰበር አቤቱታቸውን ደግሞ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም፡፡ የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡

አመልካች ነሐሴ 11 ቀን 2002 .ም በፃፉት ሶስት ገጽ የሠበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ብይን ላይ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚሉባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡ አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችሎቱ ሊታይ የሚገባው ነው ተብሎ በመታዘዙ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የፅሑፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን፤ ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ወሣኔ እና አግባብነት ከላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል፡፡

ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ አመልካች ተጠሪዎች ባቀረቡባቸው የውርስ ንብረት ይልቀቅልን የዳኝነት ጥያቄ የይርጋ ክርክር አንስተው የሥር ፍርድ ቤት በዚሁ ላይ ብይን ሳይሰጥ በማለፉ የበላይ ፍርድ ቤት በአመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ተገቢው ብይን እንዲሰጥ ለስር ፍርድ ቤት ጉዳዩን ከመለሰለት በኋላ በመጀመያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ማስረጃ መስማት እንዳለበት የስር ፍርድ ቤት አምኖ ተገቢ ነው ያለውን ትዕዛዝ በሰጠው መቃወሚያ ላይ ተገቢው መጣራት ተደርጎ ብይን ሊሰጥበት ይገባል በማለት ውሣኔ የሰጠው የበላይ ፍርድ ቤት ተገቢው መጣራት ተደርጓል ሲል ማስረጃ ተሰምቶ መሆን ያለመሆኑን ማብራሪያ እንዲሰጥበት ይህንኑም አመልካች ተከታትለው እንዲይስፈፅሙ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቶ አመልካች ይህንኑ ትዕዛዝ ሳያስፈፅሙ አዲስ የማስረጃ ዝርዝር አቅርበዋል በሚል ነው፡፡

ይሁን እንጂ የአመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሰረት ያደረገው የጊዜ ማለፍ ሲሆን፤ ይህ የጊዜ ማለፍ ደግሞ ተጠሪዎች ካቀረቡት ክስ ባሕርይ እና ክስ ከተመሰረተበት ጊዜ አንፃር ታይቶ አግባብነት ባለው ሕግ ምላሽ የሚሰጠው ከመሆን ውጪ የተከሣሽ ማስረጃ ሊሰማ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የሌለው ነው፡፡

ተጠሪዎች የጊዜውን ማለፍ አምነው የይርጋ ጊዜውን ሊያቋርጡ የሚችሉ ሕጋዊ ክርክርና ማስረጃ ያላቸው ስለመሆኑ ጠቅሰው መከራከራቸው የሚያሳይ የክርክር ሂደትም የለም፡፡ የሥር ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን እንዲሰጥ ይግባኙን የተመለከተው የበላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲሰጥም በጊዜው ማለፍ ላይ ማስረጃ እንዲሰማ ብሎ የገለፀው ነገር የሌለ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

በመሆኑም በአመልካች በኩል የይርጋ ጊዜ አልፏል በሚል የቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው መሆን ያለመሆኑን የክሱን ዓይነትና ክሱ የቀረበበትን ጊዜ ለጉዳዩ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማዛመድ ብይን የሚሰጥበት ሆኖ እያለ የስር ፍ/ቤት የሰው ማሰረጃ መቅረብ አለበት ያለበት አግባብ ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖረው መሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል፡፡

ይህ ደግሞ የፍ/////ቁጥር 244/ 2// እና234 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ እንዲሁም ዓላማቸውን ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ የአመልካችን የመከራከር መብት ያጠበበ ሆኖ አግኝተናል፡፡ በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ጉዳዩ ከተመለሰለት በኋላ መዝገቡን የዘጋበት ሥርዓት መሠረታዊ የሆነ የሥነ ስርዓት ሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል፡፡

አያሌው ንጉሤ

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

            በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።