Ethiopian Press Agency Editorial page
Home  |  About us |  Contact us |  Forum |  Subscribe
Login  | Register 
Language

ዜና
አስተያየትና እና አመለካከት
ርእሰ አንቀፅ
ኢኮኖሚ
ፖለቲካ
ማህበራዊ
መዝናኛ
ስፖርት
የማስታወቅያ ሚኒስተር መልእክት
ፎቶ ጋለሪ
Home | About us | Contact us | Forum | Subscribe
ርእሰ አንቀፅ
ሥርዓት የሌ...
ለካስ ይቻል ...
የሁለትዮሽ ...
አፍሪካ በአ...
ጊዜው የአፍ...
ለአህጉራዊ ...
ለአህጉራዊ ...
የተሽከርካ...
ድክመቶችን ...
መንገዶች ሁ...

መንገዶች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ ያመራሉ!

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መድረክ የመሆን ልዩ ብቃቷን እያስመሰከረች በመሆኑ መንገዶች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ ማምራታቸው በተግባር እየታየ ነው፡፡
በራሷና በጎረቤቶቿ አስተማማኝ ሰላም፣ ልማትና እድገት እውን ሆኖ ማየትና ተያይዞ ማደግ የዘወትር አጀንዳዋ የሆነው ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ያከናወነችው ተግባር ውጤት ማሳየት በመጀመሩ በእርግጥም እንግዶች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያቀኑ አስችሏል፤ የሀገራችን ዓለም አቀፍ ተቀባይነትና ከበሬታ እንዲጨምርም አድርጓል፡፡
የአፍሪካ ህብረትን 18ኛ የመሪዎች ጉባዔ ከፊታችን ጥር 20 እስከ ጥር 21 የምታስተናግደው አዲስ አበባ 5ሺ ያህል እንግዶችን እንደምትቀበል ተጠብቋል፤ እስከ ከትናንት በስቲያ ድረስ ብቻ ከ38 በላይ ርዕሳነ ብሄሮችና የመንግሥታት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ማረጋገጫ መስጠታቸው ታውቋል፡፡
አዲስ አበባ በጉባዔው የሚታደሙ እንግዶቿን ከወትሮው ለየትና ደመቅ ባለ መልኩ ነው ቤት ለእምቦሳ የምትላቸው፤ እንግዳን መቀበል ባህላቸው ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ተርታ በ200 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በቻይና መንግሥት ሙሉ ድጋፍ የተገነባው አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ህንፃ አቀባበሉን ግዙፍ ቁመናውና ውብ ገጽታው ያደምቀዋል፡፡ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ መድረክነት ያጠናክረዋል፡፡
እግሮች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ በሚያመሩት መንገዶች እንዲያቀኑ ኢትዮጵያውያን መሪዎች በአፍሪካ ጉዳይ ያላቸው አቋም ወጥና የማይዛነፍ ሆኖ መቀጠሉ ልዩ አስተዋፅኦ ማድረጉ አይካድም፡፡ የአፍሪካ አንድነትን ከመመስረት ጀምሮ በአህጉሪቱ ሀገሮች የነፃነትና እኩልነት ጉዳይ የማይናወጥ አቋም ብቻ ሳይሆን የተግባር ድጋፍና አንድነታቸው ዛሬም ድረስ ህያው ሆኗል፡፡
የአህጉሪቱ ቀደምት አባቶች ያፀኑት መሰረት ተጠብቆ እንዲጓዝ በማድረግ አፍሪካውያን በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ በኑሮና ልማት በተመቸ ሁኔታ እንዲራመዱ ለማስቻል የሀገራችን ሚና አሁንም ደምቆ እንደቀጠለ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አህጉሪቱን በመወከል በአካባቢ ጥበቃ መስክ የአፍሪካን ጥቅም ለማስጠበቅ ያደረጉት ተከታታይነት ያለው ያላሰለሰ ጥረትና ያስገኙትን ውጤት ጨምሮ የአፍሪካውያን ሰላም እንዲጠበቅ ኢትዮጵያዊና አህጉራዊ ተልዕኮ በማንገብ ከግጭትና ብጥብጥ የፀዳች አፍሪካን ለመፍጠር እያበረከቱ ያለው አስተዋፅኦ ከዚሁ ተርታ ይመደባል፡፡
የቀደምት አባቶች ውጥንና ራዕይ እንዲሳካ ኢትዮጵያ የአህጉራዊው ተልዕኮ ባለድርሻነቷን አጠናክራ መቀጠሏም የሚያስገነዝበው ይህንኑ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ዙሪያ መለስ በሆነው የአፍሪካ ጉዳይ እያበረከተች ካለው አስተዋፅኦ ባሻገር በውስጥ ሰላምና ልማቷ ያላት ትኩረት በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባቱ ተቀባይነቷን አግዝፎታል፡፡ ህዝቧ በመከባበርና በመፈቃቀር ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን አጎልብቶ ፊቱን ወደ ልማት በማዞሩ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገብ ጀምረዋል፡፡ በልማትና ዴሞክራሲ የፈጠረችው ሰላም ከኢኮኖሚ እድገት በተጨማሪ የአፍሪካውያንና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀልብና ትኩረት ወደ ኢትዮጵያ እንዲሆን አስችሏል፡፡
በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ከአስር ሺ በላይ እንግዶች በአይካሳው ጉባዔ አዲስ አበባን ናኝተውባታል፡፡ ጉባዔያቸውን በሰላም በማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረት በሰላምና ልማት ላይ ማነጣጠሩን አረጋግጠዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ አሁንም በ18ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባዔና ከወዲሁ በሚከናወኑ የህብረቱ አጀንዳዎች ለመምከር እየገቡ ያሉ እንግዶቿን በአግባቡ ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቅቃለች፡፡ በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ህንፃ አፍሪካውያን መሪዎች አህጉራዊ ውጥናቸውን ለማሳካት እንዲመክሩ ‹ሰላም ነው፣ እንኳን ደህና መጣችሁ› ትላለች፤ መንገዶች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያመሩ!

ምንጭEthiopian Press Agency
ቀን 2012-01-26 00:00:00