«ለሰብዓዊ ተግባር በቁርጠኝነት መሥራት ያስፈልጋል»- ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ Featured

10 May 2015

ዜጎች የቀይ መስቀልን ሰብዓዊ በጎ ተግባር በመሰነቅ እና በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስ አጋርነታቸውን መግለጽ እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የበላይ ጠባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አሳሰቡ።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የበላይ ጠባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ትናንት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት « መርሆዎቻችን በተግባር » በሚለው መሪ ሃሳብ የሚከበረውን የዘንድሮውን የዓለም የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃን ቀን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ ለሰብዓዊ ተግባሮች በቁርጠኝነት መሥራትና የበጎ ፈቃደኞችን ተግባር መዘከር ያስፈልጋል።

እንደ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ፤ «ሥራችንን ስንሠራ በመመሪያነት የምንጠቀምባቸው መሠረታዊ

መርሆዎች በተግባር ላይ እንዲውሉ የተወሰነበት 50ኛ ዓመት የተግባር ታሪክ ዘንድሮ የሚከበር በመሆኑ፤ ለበዓሉ የተመረጠውን መሪ ሃሳብ ወቅታዊ ያደርገዋል» ብለዋል። ዕለቱ ሲከበር ያለፈውን ሰብዓዊ ተግባር በማስታወስና ለዚህም ሕይወታቸውን የሰጡ በጎ ፈቃደኞችን በመዘከር፣ እንዲሁም ለቀጣይ የቀይ መስቀል ሰብዓዊነት ተግባራት በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስና መርሆዎቹን በጥልቀት በማሰብ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

ሕዝቡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በሚያዘጋጃቸው ሁነቶች ሁሉ በመሳተፍ የሰብዓዊነት አጋርነቱን እንዲገልጽ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

 

የጎብኝዎች ብዛት

0002770757
TodayToday781
YesterdayYesterday2274
This_WeekThis_Week10288
This_MonthThis_Month100001
All_DaysAll_Days2770757

       በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።