አቶ ልደቱ አያሌው ስለ ግንቦት «ኤርትራና የባህር በራችንን ያሳጣን ነው» Featured

27 Aug 2015

ግንቦት 20ን ስናስብ እያንዳንዳችን ቀኑን በየራሳችን እይታ ልንተረጉመው እንችላለን፡፡በዚህም ለብዙዎቻችን ቀኑ የድልና አምባገነናዊው የደርግ ስርዓት የተወገደበት በምትኩም ልማታዊና ዲሞከራሲያዊ ስርአት እውን የሆነበት ዕለት እንደሆነ እናስባለን፡፡ ለሌሎች ደግሞ በተቃራኒው ሌላ ትርጉም የሚሰጡበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ለማንኛውም ታዋቂውን የፖለቲካ ሰው አቶ ልደቱ አያሌውን ግንቦት 20 በእርስዎ እይታ እንዴት ይገለፃል? ስንል ጠይቀናቸው እንደሚከተለው ነግረውናል፡፡

ዘመን፡- አቶ ልደቱ ግንቦት 20ን እንዴት ይገልፁታል?

አቶ ልደቱ፡- ግንቦት 20 ሁለት መልክ ነው ያለው። የዛሬ 24 ዓመት አገሪቱን ለአስራ ሰባት ዓመታት ሲገዛ የነበረው ወታደራዊ አምባገንን መንግሥት የተወገደበትና ከስልጣን የወረደበት ዕለት ነው። ያ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ትልቅ ድል ነው፡፡ ሁለተኛው ከኢህአዴግ መምጣት በኋላ እንግዲህ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ህገ መንግሥታዊ እውቅና ያገኙበት ጊዜ ነው። ይሔ ደግሞ ከዚያ በፊት ያልነበረ ትልቅ ታሪካዊ ድልና እመርታ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እውቅና ያገኘበት ነው። ከዚያ በተጨማሪ ደግሞ መንግሥትና ህዝብ ለልማትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ትኩረት የሰጡበትና አዲስ ምዕራፍ የተከፈተበት ነው። ይሔ እንግዲህ በአዎንታዊ ወይም በበጐ ጐኑ ሊታይ የሚችል ነው።

በሌላ በኩል ግን ሁለተኛው ገፅታ ኢትዮጵያ የምትባለው በታሪክ አንድ ሆና የምናውቃት አገር፤ በእርግጥ በተለያየ ጊዜ ስትሰፋና ስትጠብ የነበረችው አገር እንደገና ለሁለት የተከፈለችበትና የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብ የተለያየበት ወቅት ነው ግንቦት 20። ይሔ እንደ መጥፎ አጋጣሚ ሊታይ የሚችል ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ህዝብ ወይም ኢትዮጵያ የባህር በር ያጡበት ዕለት ነው ግንቦት 20። ይሔም በአሉታዊ መልኩ ሊታይ የሚችል ነው።

ሌላው ከፖለቲካ አንፃር ስናየው የብሔር ፖለቲካ የበለጠ ቦታ ያገኘበትና የገነነበት ነው። በንፃሩ ደግሞ አገራዊ አንድነት የተዳከመበትና እየላላ የመጣበት ወቅት ነው ብዬ ነው የማምነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አዲስ የፖለቲካ ቅራኔዎችም የተፈጠሩበት ወቅት ነው። ኢህአዴግ መንግሥት ሲሆን ምሉዕ የሆነ ተቀባይነት አልነበረውም። በስልጣን ላይ የወጣው መንግሥት አይወክለንም ለአገሪቱም አይበጅም የሚሉ አዳዲስ የፖለቲካ ኃይሎች ተፈጥረው በሰላማዊውም በትጥቅም መታገል የጀመሩበት ወቅት ነው። እና አዳዲስ የፖለቲካ ቅራኔዎች በአገሪቱ የተፈጠሩበት ሁኔታዎች ናቸው ያሉት። እናም ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ አገሪቱ ከአንድ አምባገነናዊ ወታደራዊ ኃይል ቁጥጥር ስር ወጥታ እንደገና በሌላ አምባገነናዊ ኃይል ቁጥጥር ስር የዋለበችበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። እና ይሔንን እንደዚህ በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ነው የሚመስለኝ። ዝርዝር ጉዳዮቹን ካየን በአሉታዊም በአዎንታዊም ጐን የምናነሳቸው ጉዳዮች ይኖራሉ። በአጠቃላይ ግን እኔ የግንቦት 20ን አጠቃላይ ትሩፋት የማየው በዚህ መልኩ ነው።

ዘመን፡- በልማት በዕድገቱና በኢኮኖሚውስ በኩል ከግንቦት 20 በኋላ የታየውን ለውጥ እንዴት ይገልፁታል?

አቶ ልደቱ፡- አዎ! ቅድም ነጥቤን አልያዝከው ይሆናል እንጂ አሉታዊ ጐኖችን ሳነሳ አንዱ የጠቀሱኩት ነጥብ እሱ ነው። በመንግሥትም ሆነ በህዝቡ ልማትና የኢኮኖሚ ዕድገት ትኩረት ያገኙበት ወቅት ነው የተፈጠረው በግንቦት 20። ከዚያ በፊት ያው እንደሚታወቀው አገሪቱ በሶሻሊሰት ስርዓት ነበር ስትመራ የነበረው፡፡ በእርግጥ ደርግ ከመውደቁ አንድ ሁለት ዓመት በፊት ቅይጥ ኢኮኖሚን ተቀብያለሁ ቢልም ይሄን ያህል ትርጉም ያለው የኢኮኖሚና የልማት እንቅስቃሴ ያልነበረበት እንዲያውም ከ500 ሺህ ብር በላይ ሀብት ማፍራት የማይቻልበት ሁኔታ ነበር። ግንቦት 20ን ተከትሎ እንደ አገርም እንደ መንግሥትም ልማትና የኢኮኖሚ ዕድገት ልዩ ትኩረት ያገኙበትና ውጤቶችም የተገኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ዘመን፡- እንግዲህ ግንቦት 20 አገራችን ከአንድ አምባገነናዊ ስርዓት ወደ ሌላ አምባገነናዊ ስርዓት የተሸጋገረበት ነው ሲሉ ለዚህ ማሳያዎች ይኖሩዎታል?

አቶ ልደቱ፡- እንግዲህ በበጐ ጐን የጠቀስኳቸው አሉ። ለምሳሌ ዕውቅና ከማግኘት ልጀምር ። በዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ኢትዮጵያ ተቀብላ በህገ መንግቱ ማካተቷ አዎንታዊ ጐን ነው፡፡ በለፖለቲካው ረገድ አንፃራዊ ሰላም መገኘቱም አዎንታዊ ጐን ነው፡፡ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱም በኢትዮጵያ ዕውቅና አግኝቶ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው እንቅስቃሴ መጀመራቸውም ሌላ አወንታዊ ጐን ነው። በአንፃሩ ግን ግንቦት 20 የመንግሥት ለውጥ ካመጣ ይሔው ሃያ አራት ዓመት ሆነው። አንድም ጊዜ ግን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የመንግሥት ለውጥ ተደርጐ አላየንም፡፡

ግንቦት 20 በጠመንጃ ስልጣን የያዘው ኃይል እስካሁንም ስልጣን ይዞ የቀጠለበትን ሁኔታ ነው ያየነው። የአገሪቱን ፓርላማና አጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ምክር ቤቶችና መስተዳድሮችም ካየን በአንድ ፓርቲ ሙሉ ቁጥጥር ስር የዋሉበትን ሁኔታ ነው ያለው፡፡እንደሚታወቀው አገሪቱ ውስጥ የብሔርና የቋንቋ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ልዩነቶችም ናቸው ያሉት። ህዝቡ ከአገሪቱ ፓርላማ ጀምሮ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ እነዚያን የአስተሳሰብ ልዩነቶች ሊወክሉ በሚችሉና የእነዚያን የአስተሳሰብ ልዩነቶች ጥቅም ሊያስከብር በሚችል ደረጃ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ምክር ቤት ያላገኘበትና ሁሉም መዋቅር በአንድ ፓርቲ የበላይነት ሥር የወደቀበትን ሁኔታ ነው እስካሁን የምናየው። እንዲያውም በግንቦት 20 ማግስት አንዳንድ መሻሻሎች ታይተው የነበሩ ቢሆንም የተለያዩ የፖለቲካና የምክር ቤት ሁኔታዎች በሂደት ወደ ኋላ እየተመለሱ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው። ስለዚህ በአጠቃላይ ከፖለቲካ አንፃር ሲታይ ግንቦት 20 አንድ አንባገነናዊ መንግሥት ወድቆ ሌላ አምባገነናዊ መንግሥት የተተካበት ዕለት ነው ማለት ይቻላል።

ዘመን፡- እንግዲህ በየአምስት ዓመቱ ምርጫ ይካሄዳል፡፡ኢህአዴግም በእነዚህ ምርጫዎች አሸንፎ ነው ስልጣን የያዘውና ይሔ አንባገነን ያሰኘዋል ይላሉ?

አቶ ልደቱ፡- እንግዲህ ምናልባት ከኤርትራ በስተቀር በየአምስትና አራት ዓመቱ ምርጫ የማይካሔድበት የአፍሪካ አገር ያለ አይመስለኝም። ግን አሁን ባለው የዴሞክራሲ መለኪያ ሁሉም የአፍሪካ አገሮች ዴሞክራሲያዊ ናቸው ማለት አይደለም። እና ምርጫ በራሱ መካሔዱ አንድ ውጤት ቢሆንም በራሱ ግን ግብ አይደለም። የዴሞክራሲ አጠቃላይ መገለጫ አድርገን ልንወስደውም አንችልም። እና እስከአሁን ድረስ የተካሔዱት ምርጫዎች ከውዝግብም አልፈው ግጭቶች የተከሰቱባቸው፣ ደም መፋሰስ ጭምር የታዩባቸውና አዲስ ቅራኔዎች የነበሩባቸው ሁኔታዎች ናቸው የተፈጠሩት። እና በሌሎች በሰለጠኑ አገሮች እንደምናየው ሁሉም የተቀበሉትና የተስማሙበት የምርጫ ውጤት እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ አልታየም።

ዘመን፡- ቅድም ሲገልፁልኝ የግንቦት 20 አሉታዊ ጐኑ የአገር አንድነት መላላትና የብሔር ፖለቲካ መስተዋሉ ነው ብለውኛል፡፡ አሁን በአገራችን የፌዴራሊዝም ስርዓት ነው ያለው ፡፡ በዚህም ክልሎች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት ሁኔታ አለና ይሔ የፌዴራሊዝም መገለጫ አይሆንም ?

አቶ ልደቱ፡- ፌዴራሊዝምን በበጐ ጐኑ ልናየው የምንችለው አንዱ ነገር ነው። ከግንቦት 20 በፊት አሀዳዊ ስርዓት ነበር። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ፌዴራሊዝም የሚበጅ ሥርዓት ነው። ስለዚህ ግንቦት 20 ይሔንን በማምጣት ረገድ አንድ በጐ ሚና አለው ብዬ ነው የማምነው። ግን ፌዴራሊዝሙ የተዋቀረበት ስርዓት የአገሪቱን አንድነት የረሳና ከአንድነት ይልቅ የበለጠ ለልዩነት ትኩረት የሰጠ ነው። ለምሳሌ ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ በአንድነት አብሮ ሊኖር የሚችልበት ፌዴራላዊ ስርዓት በመላው አገሪቱ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ ምናልባት አንድነታችንን የበለጠ ሊያጠናክር የሚችል ፌዴራሊዝም ሊኖር ይችል ነበር። ግን በአብዛኛዎቹ ክልሎች ጥቅም ላይ የዋለው ቋንቋና ብሔረሰባዊ ማንነት ስለሆነ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ለአንድነት ሳይሆን ለልዩነት ትኩረት እንዲሰጡ አድርጓቸዋል። በመካከላቸውም ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንዲዳብር እያደረገ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ የሚገልፁ ምልክቶች በተለያየ ጊዜ አይተናል። በአጠቃላይ የመንግሥትን የፕሮፓጋንዳ ማሽንም ካየን ስለ አንድነት ሳይሆን በአብዛኛው ጊዜውን የሚወስደው ስለ ልዩነት በመስበክ ነው። ይሔ አዳዲስ ቅራኔዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲፈጠሩ አድርጓል ብዬ ነው የማምነው።

ዘመን፡- በአገራችን በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ፡፡ እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተደራጅተው አቋማቸውን እያራመዱ ነው። የሀሳብና የፖሊሲ ልዩነትም አለ፡፡ ይሔ ደግሞ የዴሞክራሲ ባህሪ ነው፡፡ ይሔ በአገራችን መኖሩ የፖለቲካ ቅራኔ አለ ያስብላል?

አቶ ልደቱ፡- አይደለም! እሱ ጤናማ ነገር ነው፡፡ ቅድም በበጐ ጐኑ የገለፁኩት ነው። የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ዕውቅና ማግኘቱና የፖለቲካ ፓርቲዎችም ህጋዊ እውቅና አግኝተው መንቀሳቀሳቸው በበጐ ጐኑ የገለፅኩት ነው። ስለ ቅራኔ ያወራሁት እሱን አይደለም። ስለ ቅራኔ የማወራው ዛሬም ይሔን መንግሥት በጠመንጃ ኃይል ታግሎ ማሸነፍ ይቻላል ወይም ይገባል ብለው ትጥቅ ያነሱ ኃይሎች አሉ። አቅም አግኝተው መንግሥት መለወጥ አልቻሉ ይሆናል፡፡ ግን ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ጥረት አድርገው ያሰቡትን ማሳካት ባይችሉም አሁንም እየታገሉ ያሉ ኃይሎች አሉ። ሰላማዊ ትግል እናደርጋለን በሚሉ ኃይሎች መካከልም ግጭት እየተፈጠረ ከሰላማዊ መንፈስ ውጪ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሁኔታም ነው የታየው። በየምርጫዎቹ ሂደቶች ይሔ ታይቷል። እነዚህን ነገሮች ነው እያልኩ ያለሁት እንጂ ፓርቲዎች መብዛታቸው ወይም ደግሞ ሰላማዊ ትግል በሚያደርጉበት ሂደት መበርከታቸው የቅራኔ ምንጭ ነው አላልኩም። እሱ የልዩነት ምንጭ ነው፡፡ የሀሳብ ልዩነት መኖሩን የሚያሳይ ነው፡፡ ችግሩ ያለው የሀሳብ ልዩኑት መኖሩ ላይ ሳይሆን የሀሳብ ልዩነቱን የሚያስተናግድ የምርጫ ውጤት እየታየ አይደለም። የሀሳብ ልዩነቱን የሚመስል ምክር ቤት ኢትዮጵያ ውስጥ እያየን አይደለም። በአጠቃላይ ከፓርላማ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ምክር ቤት ድረስ በአንድ ፓርቲ የበላይነት የሚመሩ ወይም የተያዙ ምክር ቤቶች ናቸው ያሉን። ይሔ መሬት ላይ ና ህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት የሚያንፀባርቅ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከዚያ በተቃራኒ ያለ ነው ለማለት ነው። እሱን ለማሳየት ነው እንጂ ፓርቲዎች በብዛት መኖራቸው የበጐ ነገር እንጂ የመጥፎ ነገር መገለጫ አይደለም።

ዘመን፡- ቅድም ስንነጋገር በአገራችን ሰላም መረጋገጡ ትልቁና አንዱ ውጤት /አቋረጡኝ/

አቶ ልደቱ፡- አንፃራዊ ሰላም ነው፡፡

ዘመን፡- እሺ! አንፃራዊ ሰላም መኖሩ /አቋረጡኝ/

አቶ ልደቱ፡- እሱ እንደ አንድ ድል ሊቆጠር የሚችል ነው።

ዘመን፡- አዎ! አንዱ ድል ነው። ነገር ግን አንዳንድ ኃይሎች ሥልጣን በኃይል ለመያዝ የሚያደርጉት ሙከራ ይኖራልና ይሔን ሁኔታ እንዴት ያዩታል እርስዎ? አሁን ካለው ሰላማዊና ልማታዊ ሂደት አንፃር፤

አቶ ልደቱ፡- ስርዓቱ ያልፈታው ችግር መኖሩን ያሳያል ነው። እነዚህ ቅራኔዎች ሊኖሩ አይገባም ነበር። አሁንም ሌላ የጦርነት አዙሪት ውስጥ አገሪቱ እንድትገባ ማድረግ አስፈላጊ አይደለም። ይሔ እንዳይሆን ለማድረግ ግን በዋናነት ከመንግሥትና ከስርዓቱ ብዙ ነገር ይጠበቃል። በእርግጥ ከመንግሥት ብቻ አይደለም ተቃዋሚ ከሆነው ኃይልና ከህብረተሰቡም የሚጠበቁ ብዙ ነገሮች አሉ። መንግሥት ሆደ ሰፊ ሆኖ በተለይም የዴሞክራሲውን ስርዓት በአዲስ መልክ ለመጀመር መጥቻለሁ እንደሚል አካል ብዙ ይጠበቅበታል። ይህን በማድረግ ረገድና በመፍታት በኩል መንግሥት በጣም ውስንነት አለበት። ህብረተሰቡ የእሱን አስተሳሰብ እንዲከተል ነው እንጂ የተለያዩ አስተሳሰቦች በነፃነት ተንሸራሽረው ህዝቡ የሚፈልገውንና የወደደውን በነፃነት እንዲቀበልና እንዲያከብር ጥረት ሲያደርግ አናይም። የእሱ አስተሳሰብ በሌሎች ላይ ተፅእኖ እንዲያግንቦት 20ን ስናስብ እያንዳንዳችን ቀኑን በየራሳችን እይታ ልንተረጉመው እንችላለን፡፡በዚህም ለብዙዎቻችን ቀኑ የድልና አምባገነናዊው የደርግ ስርዓት የተወገደበት በምትኩም ልማታዊና ዲሞከራሲያዊ ስርአት እውን የሆነበት ዕለት እንደሆነ እናስባለን፡፡ ለሌሎች ደግሞ በተቃራኒው ሌላ ትርጉም የሚሰጡበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ለማንኛውም ታዋቂውን የፖለቲካ ሰው አቶ ልደቱ አያሌውን ግንቦት 20 በእርስዎ እይታ እንዴት ይገለፃል? ስንል ጠይቀናቸው እንደሚከተለው ነግረውናል፡፡

ዘመን፡- አቶ ልደቱ ግንቦት 20ን እንዴት ይገልፁታል?

አቶ ልደቱ፡- ግንቦት 20 ሁለት መልክ ነው ያለው። የዛሬ 24 ዓመት አገሪቱን ለአስራ ሰባት ዓመታት ሲገዛ የነበረው ወታደራዊ አምባገንን መንግሥት የተወገደበትና ከስልጣን የወረደበት ዕለት ነው። ያ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ትልቅ ድል ነው፡፡ ሁለተኛው ከኢህአዴግ መምጣት በኋላ እንግዲህ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ህገ መንግሥታዊ እውቅና ያገኙበት ጊዜ ነው። ይሔ ደግሞ ከዚያ በፊት ያልነበረ ትልቅ ታሪካዊ ድልና እመርታ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እውቅና ያገኘበት ነው። ከዚያ በተጨማሪ ደግሞ መንግሥትና ህዝብ ለልማትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ትኩረት የሰጡበትና አዲስ ምዕራፍ የተከፈተበት ነው። ይሔ እንግዲህ በአዎንታዊ ወይም በበጐ ጐኑ ሊታይ የሚችል ነው።

በሌላ በኩል ግን ሁለተኛው ገፅታ ኢትዮጵያ የምትባለው በታሪክ አንድ ሆና የምናውቃት አገር፤ በእርግጥ በተለያየ ጊዜ ስትሰፋና ስትጠብ የነበረችው አገር እንደገና ለሁለት የተከፈለችበትና የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብ የተለያየበት ወቅት ነው ግንቦት 20። ይሔ እንደ መጥፎ አጋጣሚ ሊታይ የሚችል ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ህዝብ ወይም ኢትዮጵያ የባህር በር ያጡበት ዕለት ነው ግንቦት 20። ይሔም በአሉታዊ መልኩ ሊታይ የሚችል ነው።

ሌላው ከፖለቲካ አንፃር ስናየው የብሔር ፖለቲካ የበለጠ ቦታ ያገኘበትና የገነነበት ነው። በንፃሩ ደግሞ አገራዊ አንድነት የተዳከመበትና እየላላ የመጣበት ወቅት ነው ብዬ ነው የማምነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አዲስ የፖለቲካ ቅራኔዎችም የተፈጠሩበት ወቅት ነው። ኢህአዴግ መንግሥት ሲሆን ምሉዕ የሆነ ተቀባይነት አልነበረውም። በስልጣን ላይ የወጣው መንግሥት አይወክለንም ለአገሪቱም አይበጅም የሚሉ አዳዲስ የፖለቲካ ኃይሎች ተፈጥረው በሰላማዊውም በትጥቅም መታገል የጀመሩበት ወቅት ነው። እና አዳዲስ የፖለቲካ ቅራኔዎች በአገሪቱ የተፈጠሩበት ሁኔታዎች ናቸው ያሉት። እናም ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ አገሪቱ ከአንድ አምባገነናዊ ወታደራዊ ኃይል ቁጥጥር ስር ወጥታ እንደገና በሌላ አምባገነናዊ ኃይል ቁጥጥር ስር የዋለበችበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። እና ይሔንን እንደዚህ በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ነው የሚመስለኝ። ዝርዝር ጉዳዮቹን ካየን በአሉታዊም በአዎንታዊም ጐን የምናነሳቸው ጉዳዮች ይኖራሉ። በአጠቃላይ ግን እኔ የግንቦት 20ን አጠቃላይ ትሩፋት የማየው በዚህ መልኩ ነው።

ዘመን፡- በልማት በዕድገቱና በኢኮኖሚውስ በኩል ከግንቦት 20 በኋላ የታየውን ለውጥ እንዴት ይገልፁታል?

አቶ ልደቱ፡- አዎ! ቅድም ነጥቤን አልያዝከው ይሆናል እንጂ አሉታዊ ጐኖችን ሳነሳ አንዱ የጠቀሱኩት ነጥብ እሱ ነው። በመንግሥትም ሆነ በህዝቡ ልማትና የኢኮኖሚ ዕድገት ትኩረት ያገኙበት ወቅት ነው የተፈጠረው በግንቦት 20። ከዚያ በፊት ያው እንደሚታወቀው አገሪቱ በሶሻሊሰት ስርዓት ነበር ስትመራ የነበረው፡፡ በእርግጥ ደርግ ከመውደቁ አንድ ሁለት ዓመት በፊት ቅይጥ ኢኮኖሚን ተቀብያለሁ ቢልም ይሄን ያህል ትርጉም ያለው የኢኮኖሚና የልማት እንቅስቃሴ ያልነበረበት እንዲያውም ከ500 ሺህ ብር በላይ ሀብት ማፍራት የማይቻልበት ሁኔታ ነበር። ግንቦት 20ን ተከትሎ እንደ አገርም እንደ መንግሥትም ልማትና የኢኮኖሚ ዕድገት ልዩ ትኩረት ያገኙበትና ውጤቶችም የተገኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ዘመን፡- እንግዲህ ግንቦት 20 አገራችን ከአንድ አምባገነናዊ ስርዓት ወደ ሌላ አምባገነናዊ ስርዓት የተሸጋገረበት ነው ሲሉ ለዚህ ማሳያዎች ይኖሩዎታል?

አቶ ልደቱ፡- እንግዲህ በበጐ ጐን የጠቀስኳቸው አሉ። ለምሳሌ ዕውቅና ከማግኘት ልጀምር ። በዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ኢትዮጵያ ተቀብላ በህገ መንግቱ ማካተቷ አዎንታዊ ጐን ነው፡፡ በለፖለቲካው ረገድ አንፃራዊ ሰላም መገኘቱም አዎንታዊ ጐን ነው፡፡ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱም በኢትዮጵያ ዕውቅና አግኝቶ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው እንቅስቃሴ መጀመራቸውም ሌላ አወንታዊ ጐን ነው። በአንፃሩ ግን ግንቦት 20 የመንግሥት ለውጥ ካመጣ ይሔው ሃያ አራት ዓመት ሆነው። አንድም ጊዜ ግን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የመንግሥት ለውጥ ተደርጐ አላየንም፡፡

ግንቦት 20 በጠመንጃ ስልጣን የያዘው ኃይል እስካሁንም ስልጣን ይዞ የቀጠለበትን ሁኔታ ነው ያየነው። የአገሪቱን ፓርላማና አጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ምክር ቤቶችና መስተዳድሮችም ካየን በአንድ ፓርቲ ሙሉ ቁጥጥር ስር የዋሉበትን ሁኔታ ነው ያለው፡፡እንደሚታወቀው አገሪቱ ውስጥ የብሔርና የቋንቋ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ልዩነቶችም ናቸው ያሉት። ህዝቡ ከአገሪቱ ፓርላማ ጀምሮ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ እነዚያን የአስተሳሰብ ልዩነቶች ሊወክሉ በሚችሉና የእነዚያን የአስተሳሰብ ልዩነቶች ጥቅም ሊያስከብር በሚችል ደረጃ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ምክር ቤት ያላገኘበትና ሁሉም መዋቅር በአንድ ፓርቲ የበላይነት ሥር የወደቀበትን ሁኔታ ነው እስካሁን የምናየው። እንዲያውም በግንቦት 20 ማግስት አንዳንድ መሻሻሎች ታይተው የነበሩ ቢሆንም የተለያዩ የፖለቲካና የምክር ቤት ሁኔታዎች በሂደት ወደ ኋላ እየተመለሱ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው። ስለዚህ በአጠቃላይ ከፖለቲካ አንፃር ሲታይ ግንቦት 20 አንድ አንባገነናዊ መንግሥት ወድቆ ሌላ አምባገነናዊ መንግሥት የተተካበት ዕለት ነው ማለት ይቻላል።

ዘመን፡- እንግዲህ በየአምስት ዓመቱ ምርጫ ይካሄዳል፡፡ኢህአዴግም በእነዚህ ምርጫዎች አሸንፎ ነው ስልጣን የያዘውና ይሔ አንባገነን ያሰኘዋል ይላሉ?

አቶ ልደቱ፡- እንግዲህ ምናልባት ከኤርትራ በስተቀር በየአምስትና አራት ዓመቱ ምርጫ የማይካሔድበት የአፍሪካ አገር ያለ አይመስለኝም። ግን አሁን ባለው የዴሞክራሲ መለኪያ ሁሉም የአፍሪካ አገሮች ዴሞክራሲያዊ ናቸው ማለት አይደለም። እና ምርጫ በራሱ መካሔዱ አንድ ውጤት ቢሆንም በራሱ ግን ግብ አይደለም። የዴሞክራሲ አጠቃላይ መገለጫ አድርገን ልንወስደውም አንችልም። እና እስከአሁን ድረስ የተካሔዱት ምርጫዎች ከውዝግብም አልፈው ግጭቶች የተከሰቱባቸው፣ ደም መፋሰስ ጭምር የታዩባቸውና አዲስ ቅራኔዎች የነበሩባቸው ሁኔታዎች ናቸው የተፈጠሩት። እና በሌሎች በሰለጠኑ አገሮች እንደምናየው ሁሉም የተቀበሉትና የተስማሙበት የምርጫ ውጤት እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ አልታየም።

ዘመን፡- ቅድም ሲገልፁልኝ የግንቦት 20 አሉታዊ ጐኑ የአገር አንድነት መላላትና የብሔር ፖለቲካ መስተዋሉ ነው ብለውኛል፡፡ አሁን በአገራችን የፌዴራሊዝም ስርዓት ነው ያለው ፡፡ በዚህም ክልሎች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት ሁኔታ አለና ይሔ የፌዴራሊዝም መገለጫ አይሆንም ?

አቶ ልደቱ፡- ፌዴራሊዝምን በበጐ ጐኑ ልናየው የምንችለው አንዱ ነገር ነው። ከግንቦት 20 በፊት አሀዳዊ ስርዓት ነበር። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ፌዴራሊዝም የሚበጅ ሥርዓት ነው። ስለዚህ ግንቦት 20 ይሔንን በማምጣት ረገድ አንድ በጐ ሚና አለው ብዬ ነው የማምነው። ግን ፌዴራሊዝሙ የተዋቀረበት ስርዓት የአገሪቱን አንድነት የረሳና ከአንድነት ይልቅ የበለጠ ለልዩነት ትኩረት የሰጠ ነው። ለምሳሌ ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ በአንድነት አብሮ ሊኖር የሚችልበት ፌዴራላዊ ስርዓት በመላው አገሪቱ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ ምናልባት አንድነታችንን የበለጠ ሊያጠናክር የሚችል ፌዴራሊዝም ሊኖር ይችል ነበር። ግን በአብዛኛዎቹ ክልሎች ጥቅም ላይ የዋለው ቋንቋና ብሔረሰባዊ ማንነት ስለሆነ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ለአንድነት ሳይሆን ለልዩነት ትኩረት እንዲሰጡ አድርጓቸዋል። በመካከላቸውም ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንዲዳብር እያደረገ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ የሚገልፁ ምልክቶች በተለያየ ጊዜ አይተናል። በአጠቃላይ የመንግሥትን የፕሮፓጋንዳ ማሽንም ካየን ስለ አንድነት ሳይሆን በአብዛኛው ጊዜውን የሚወስደው ስለ ልዩነት በመስበክ ነው። ይሔ አዳዲስ ቅራኔዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲፈጠሩ አድርጓል ብዬ ነው የማምነው።

ዘመን፡- በአገራችን በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ፡፡ እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተደራጅተው አቋማቸውን እያራመዱ ነው። የሀሳብና የፖሊሲ ልዩነትም አለ፡፡ ይሔ ደግሞ የዴሞክራሲ ባህሪ ነው፡፡ ይሔ በአገራችን መኖሩ የፖለቲካ ቅራኔ አለ ያስብላል?

አቶ ልደቱ፡- አይደለም! እሱ ጤናማ ነገር ነው፡፡ ቅድም በበጐ ጐኑ የገለፁኩት ነው። የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ዕውቅና ማግኘቱና የፖለቲካ ፓርቲዎችም ህጋዊ እውቅና አግኝተው መንቀሳቀሳቸው በበጐ ጐኑ የገለፅኩት ነው። ስለ ቅራኔ ያወራሁት እሱን አይደለም። ስለ ቅራኔ የማወራው ዛሬም ይሔን መንግሥት በጠመንጃ ኃይል ታግሎ ማሸነፍ ይቻላል ወይም ይገባል ብለው ትጥቅ ያነሱ ኃይሎች አሉ። አቅም አግኝተው መንግሥት መለወጥ አልቻሉ ይሆናል፡፡ ግን ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ጥረት አድርገው ያሰቡትን ማሳካት ባይችሉም አሁንም እየታገሉ ያሉ ኃይሎች አሉ። ሰላማዊ ትግል እናደርጋለን በሚሉ ኃይሎች መካከልም ግጭት እየተፈጠረ ከሰላማዊ መንፈስ ውጪ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሁኔታም ነው የታየው። በየምርጫዎቹ ሂደቶች ይሔ ታይቷል። እነዚህን ነገሮች ነው እያልኩ ያለሁት እንጂ ፓርቲዎች መብዛታቸው ወይም ደግሞ ሰላማዊ ትግል በሚያደርጉበት ሂደት መበርከታቸው የቅራኔ ምንጭ ነው አላልኩም። እሱ የልዩነት ምንጭ ነው፡፡ የሀሳብ ልዩነት መኖሩን የሚያሳይ ነው፡፡ ችግሩ ያለው የሀሳብ ልዩኑት መኖሩ ላይ ሳይሆን የሀሳብ ልዩነቱን የሚያስተናግድ የምርጫ ውጤት እየታየ አይደለም። የሀሳብ ልዩነቱን የሚመስል ምክር ቤት ኢትዮጵያ ውስጥ እያየን አይደለም። በአጠቃላይ ከፓርላማ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ምክር ቤት ድረስ በአንድ ፓርቲ የበላይነት የሚመሩ ወይም የተያዙ ምክር ቤቶች ናቸው ያሉን። ይሔ መሬት ላይ ና ህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት የሚያንፀባርቅ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከዚያ በተቃራኒ ያለ ነው ለማለት ነው። እሱን ለማሳየት ነው እንጂ ፓርቲዎች በብዛት መኖራቸው የበጐ ነገር እንጂ የመጥፎ ነገር መገለጫ አይደለም።

ዘመን፡- ቅድም ስንነጋገር በአገራችን ሰላም መረጋገጡ ትልቁና አንዱ ውጤት /አቋረጡኝ/

አቶ ልደቱ፡- አንፃራዊ ሰላም ነው፡፡

ዘመን፡- እሺ! አንፃራዊ ሰላም መኖሩ /አቋረጡኝ/

አቶ ልደቱ፡- እሱ እንደ አንድ ድል ሊቆጠር የሚችል ነው።

ዘመን፡- አዎ! አንዱ ድል ነው። ነገር ግን አንዳንድ ኃይሎች ሥልጣን በኃይል ለመያዝ የሚያደርጉት ሙከራ ይኖራልና ይሔን ሁኔታ እንዴት ያዩታል እርስዎ? አሁን ካለው ሰላማዊና ልማታዊ ሂደት አንፃር፤

አቶ ልደቱ፡- ስርዓቱ ያልፈታው ችግር መኖሩን ያሳያል ነው። እነዚህ ቅራኔዎች ሊኖሩ አይገባም ነበር። አሁንም ሌላ የጦርነት አዙሪት ውስጥ አገሪቱ እንድትገባ ማድረግ አስፈላጊ አይደለም። ይሔ እንዳይሆን ለማድረግ ግን በዋናነት ከመንግሥትና ከስርዓቱ ብዙ ነገር ይጠበቃል። በእርግጥ ከመንግሥት ብቻ አይደለም ተቃዋሚ ከሆነው ኃይልና ከህብረተሰቡም የሚጠበቁ ብዙ ነገሮች አሉ። መንግሥት ሆደ ሰፊ ሆኖ በተለይም የዴሞክራሲውን ስርዓት በአዲስ መልክ ለመጀመር መጥቻለሁ እንደሚል አካል ብዙ ይጠበቅበታል። ይህን በማድረግ ረገድና በመፍታት በኩል መንግሥት በጣም ውስንነት አለበት። ህብረተሰቡ የእሱን አስተሳሰብ እንዲከተል ነው እንጂ የተለያዩ አስተሳሰቦች በነፃነት ተንሸራሽረው ህዝቡ የሚፈልገውንና የወደደውን በነፃነት እንዲቀበልና እንዲያከብር ጥረት ሲያደርግ አናይም። የእሱ አስተሳሰብ በሌሎች ላይ ተፅእኖ እንዲያሳድርና የህዝቡ አስተሳሰብ እንዲሆን ብቻ ሲጥር ነው የምናየው፡፡ እና እነዚህ ነገሮች መፈጠራቸው በራሱ ጥሩ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ግን የተፈጠሩበት ምክንያት አንዱ መንግሥት እንደዚህ አይነት ቅራኔዎች እንዲፈቱና መልካም ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረግ ባለመቻሉ ነው።

ዘመን፡- ስለዚህ በአጠቃላይ ግንቦት 20ን እንዴት ይመዝኑታል?

አቶ ልደቱ፡- እንዳልኩት ሁለት ጐን አለው፡፡ በተለይ ከልማት፣ ከአንፃራዊ ሰላም፣ ከኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያየዘ ግንቦት 20 ትልልቅ ድሎችን አምጥቷል። ወደ ፖለቲካው ስንመጣ ደግሞ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እውቅና ማግኘታቸው በበጐ ጐን የሚታይ ሆኖ ሳለ በሌላ በኩል ግን የልዩነትና የብሔር ፖለቲካ የበለጠ እንዲሰራፋና አገራዊ አንድነት እንዲላላ አድርጓል። አንድ የነበረው ህዝብና አገር ሁለት እንዲሆን አድርጓል። ኢትዮጵያ ለዘመናት የነበራትን የባህር በር እንድታጣ አድርጓል። እነዚህ ነገሮች ደግሞ በአሉታዊ ጐኑ የሚታዩ ናቸው። ስለዚህ በተለይ በዴሞክራሲ ረገድ ህዝቡ የተመኘውንና ሲታገልለት የኖረውን ውጤት አምጥቷል ማለት አይቻልም። በኢኮኖሚና በልማት አንፃር ግን ከነጉድለቶቹ በጣም በጐ የሚባሉ እመርታዎችን አምጥቷል ማለት ይቻላል።

ዘመን፡-ቅድም የባህር በር ሲሉ ይሄ አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር የሌሎች አገሮችን ሉአላዊነት መድፈር አይሆንም?

አቶ ልደቱ፡- ኢትዮጵያ ለብዙ ዘመናት የባህር በር የነበራት አገር ነበረች። የባህር በሯ በአንድ ወቅት በውጪ ኃይል ሲያዝ እንደገና ደግሞ የውስጥ ኃይሉ ተቀጣጥሎ መልሶ ሲቆጣጠረው የኖረ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ታሪክ ስታገላብጥ ምናልባት ለተወሰኑ ዓመታት ኤርትራ በጣሊያን ቁጥጥር ስር በሆነችበት ወቅት ካልሆነ በስተቀር ለሺ ዘመናት ኢትዮጵያ የባህር በር አጥታ አታውቅም። ቀይ ባህር ላይ በሺ ኪሎ ሜትር የሚቆጠር የባህር በር የነበራት አገር ነች። ይሔን ያጣቸው በ1983 .ም ግንቦት 20 ነው፡፡ ይሔን እንደ በጐ ነገር ማየት ተገቢ አይመስለኝም። ይሔ ማለትም ደግሞ የሌላ አገር ሉአላዊነትን መድፈር አይመስለኝም። ይሔ ሁኔታ በኃይል ወይም በጦርነት ይለወጥ ማለት አይደለም። 1983 .ም ላይ ኢህአዴግ ተገቢ የሆነ ሥራ መስራት ቢችል ኖሮ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ አንድነትን አሁን ካለበት በተሻለ በጥሩ ሁኔታ የሚገኝበትና የህዝቡም አንድነት ተጠብቆ የሚቀጥልበት አገሪቱም ደግሞ የባህር በር የምታገኝበት ዕድል ሊኖር ይችል ነበር ብዬ አምናለሁ። ግን በተቃራኒው የሆነው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተነጠለች የባህር በርም አጣን። ከዚያም አልበቃ ብሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ያጣችበት ጦርነት ውስጥ ነው የገባችው። እስካሁንም ድረስ ከኤርትራ ጋር ያለን ግንኙነት በቋፍ ያለ ነው። ይሔ በግንቦት 20 የተገኘው ድል ብዙ ጉድለቶች ያሉት መሆኑን የሚያሳይ ነው። ስለዚህ እንዲህ ዓይነቱን እምነት ማጣት ከሉአላዊነት መድፈር ጋር ግንኙነት የለውም። የሉአላዊነት ጥያቄ ሊነሳ የሚችለው አንድ ኃይል ይሔን ጉዳይና ነባራዊ ሁኔታ በኃይል አመጣለሁ ብሎ ሲነሳ ነው፡፡እሱ ድፍረት ሊሆን ይችላል። ግንቦት 20 ያሳጣንን አንድ ታሪካዊ ሁኔታ ግን በዚህ መልኩ መግለፅ ከሉአላዊነት ጋር ችግር ያለው አይመስለኝም።

ዘመን፡- ታሪክ እንዳለ ሆኖ አሁን ግን ሌላ አገርና ሌላ ህዝብ ነው ያለው፤

አቶ ልደቱ፡- በየትም ዓለም እኮ አንድ መንግሥት በአንድ ወቅት የሰራው በጎ ነገር ጐልቶ የሚወጣውን ያህል የነበሩት ድክመቶችና የሰራቸው ስህተቶች በታሪክ ይወሳሉ። ኢህአዴግም ከዚህ ታሪካዊ ሂደትና ተጠያቂነት ነፃ ሊሆን አይችልም። ኢትዮጵያን የባህር በር በማሳጣት ረገድ የኢህአዴግ ሚና ቀላል አይደለም። ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ባራመዳቸው አቋሞች ኢትዮጵያን የባህር በር አልባ በማድረግ ረገድ የተጫወተው ሚና ቀላል አይደለም። አሁን በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ደረጃም እንዲሆን የኢህአዴግ አስተዋፅኦ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ይሔንን አምነን መቀበል ነው እንጂ አንድ ስርዓት ያመጣውን ድልና ውጤት ወይም በጐ ነገር ብቻ እየጠቀስን በጐ ያልሆነውን ነገር ደግሞ ዝም ብለን ልንጥለው አንችልም። ታሪክ እንደዚያ ሊያዘን አይችልም። ስለዚህ ሁሉም ሊመዘን የሚገባው ጉዳይ ነው። በሂደት ደግሞ አንዳንድ የኢህአዴግ ሰዎችም ራሳቸው ያገር ስህተት መሆኑን አደባባይ እየወጡ መናገር የጀመሩበት ወቅት ይመስለኛል። ምናልባት የእነ አቶ ገብሩ አስራትን መጽሐፍ አንብበህ ከሆነ የሚያነሳው ይሔንን ነው። በዚያ ረገድ ኢህአዴግ የነበረው አቋም ምን ያህል የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እንደጐዳ የጉዳዩ የጋራ ባለቤት የነበሩ ሰዎች ሳይቀሩ እየመሰከሩ ነው። ስለዚህ ይሔን አምኖ መቀበል ነው እንጂ የሚሻለው ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያመጣው ውጤት ጥሩ ነገር ብቻ ነው ሌላ ነገር የለውም ብሎ መከራከር የሚያዋጣ አይመስለኝም።

ዘመን፡- እርስዎ አሁን በአገራችን እየተካሔደ ባለው ምርጫ እየተወዳደሩ አይደለምና መቼ ነው ወደ ውድድር የሚመጡት?

አቶ ልደቱ፡- ያው ፖለቲካ ውስጥ አለሁኝ። በፖለቲካ ውስጥ ያለ ሁሉ በምርጫው አይወዳደርም፡፡ አንድ ፓርቲ በአስር ሺና በመቶ ሺ የሚቆጠሩ አባላት ሊኖሩት ይችላል። በምርጫ የሚወዳደሩት ግን ጥቂት አባላቶቹ ናቸው። እኔ ደግሞ ሌላ ጊዜ አስፈላጊ መስሎ ሲታየኝ ልወዳደር እችላለሁ።

ዘመን፡- እስካሁን ያለውን የምርጫ ሂደት እንዴት አዩት?

አቶ ልደቱ፡- እንደገለፅኩልህ ምርጫ መካሔዱ ጥሩ ነው፡፡ ይሄ ሂደት መቀጠል አለበት። ምክንያቱም ሌላ አማራጭ የለም። ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ ሂደትን ከመቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። ከዚህ አንፃር ምርጫ መካሔዱ ጥሩ ጎን ነው፡፡ መቀጠል ያለበት ነገር ነው። ፓርቲዎችም መሳተፋቸው ጥሩ ነገር ነው። ከጉድለቶቹ አንፃር ግን ካለፉት ምርጫዎች የተለዩ ነገሮችን አላየሁም። አሁንም በምርጫው ዙሪያ የአንድን ፓርቲ የበላይነትን የሚያሳዩና ህብረተሰቡ አማራጮችን በብቃት አይቶና መዝኖ ነፃ በሆነ መንፈስ ምርጫ የሚያካሒድበት ሁኔታን የሚያደናቅፉ ብዙ ችግሮች እንዳሉ ነው የተረዳሁት። ስለዚህ ከውጤት አንፃር ይሔ ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች የተሻለ ነገር ያመጣል ብዬ ብዙም አልጠብቅም። ያን እንግዲህ ወደፊት የምናየው ሊሆን ይችላል። እና ሂደቱ አሁንም በችግር የተሞላ ነው። አብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በችግሩ ውስጥ ሆነው ነው እየተሳተፉ ያሉት። ለሂደቱ ታማኝ በመሆናቸውና በሂደቱ መሳተፋቸው የግድ አማራጭ የሌለው አማራጭ ነው ብለው በማመናቸው ነው እንጂ ባለፉት ምርጫዎች የታዩ ችግሮች አሁንም እየታዩ ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ አብዛኛዎቹ ፓርቲዎችም የሚናገሩት ይሔንኑ ነው።

ዘመን፡- በዘንድሮ የምርጫ ሂደት የተሻሉ ነገሮች እየታዩ ስለመሆኑ ህብረተሰቡም በየሚዲያው እየተገለፀ ነው፡፡ በፓርቲዎቹ ክርክሮችም የፓርቲዎችን አቋም መገንዘባቸውን እየገለፁ ነው ና በአሁኑ ሂደት የተሻለ ነገር የለም?

አቶ ልደቱ፡- ከክርክር አንፃርም ካየነው የዛሬ አስር ዓመት ከተካሔደው ክርክር የአሁኑ ያነሰ ነው። በአጠቃላይ በተሰጠው ሽፋንም፣ በትኩረቱም ብናየው ጉዳይ ተኮር፣ የበሰለና የህብረተሰቡን ቀልብ የሳበ ክርክር የለም። ከአሁን በፊት ነበር የተሻለ ነገር ሲካሄድ የነበረው፡፡ ያ ነገር አሁን እየደበዘዘ የመጣበት ሁኔታ ነው የሚታየው። እንዲያውም አስቀድሞ የምርጫው ውጤት ይታወቃል በሚል ሰዎች የምርጫውን የክርክር ሂደት ጓጉተው የሚከታተሉበት ሁኔታን አይደለም እየተመለከትኩ ያለሁት።

ዘመን፡- አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ሲገልፁ ሚዲያው ማንን መምረጥ እንዳለብን ግንዛቤ ፈጥሮልናል እያሉ ነው። መንግሥትም የአሁኑ ምርጫ ሂደት ካለፉት የተሻለ ነው ብሏል።

አቶ ልደቱ፡- ይሄ ሁል ጊዜም ይባላል ፡፡ይሄን ሊሉ የሚችሉ ሰዎች ደግሞ በማንኛውም ምርጫ ይላሉ፡፡ይሄ ማለት ደግሞ የምርጫ ክርክሮቹ ለሚያዳምጣቸውና ለሚከታተላቸው ሰው ማንን መምረጥ እንዳለባቸው ፍንጭ አልሰጡም ማለት አይደለም። ይሰጣሉ። እሱን እያልኩ አይደለም፡፡ ከጨዋታው አንፃር ግን ወደ ኋላ እየተመለሰ ነው የመጣው። ለምሳሌ የክርክሮቹን መድረክ ካየህ ተቃዋሚዎች የተሰጣቸው የጊዜ ሽፋን ያነሰ ነው። ከዚህ ቀደም በቀጥታ ስርጭት ሁሉ ነበር የሚተላለፈው፤ ተመልካች ባለበት፡፡ ዘንድሮ ግን እንደርሱ ዓይነት የለም። የመንግሥት ጋዜጠኞች ብቻ የሚጠይቁበት ነው፡፡ያም ደግሞ ከተቀረፀ በኋላ የሚተላለፍበት ሁኔታ ነው ያለው። እንዲያውም የዘንድሮው ምርጫ በጣም በሚገርም ሁኔታ ኢ ዲሞክራሲያዊ የሆነ ችግርም ይዞ ነው የመጣው። ተቋማትን መተቸች አይቻልም የሚል ሀሳብ ተይዞ የመንግሥት መገናኛ ብዙሀን ፓርቲዎች የሚያቀርቡትን የክርክር ሀሳብና ፅሁፍ ሳንሱር የሚያደርጉበት ሁኔታ ነው የተጀመረው። ይሔ ባለፉት የምርጫ ሂደቶች አልነበረም። አዲስ የተፈጠረ ችግር ነው። ስለዚህ በዚህ ረገድ የተጨበጠና የጐላ ሁኔታ ተፈጥሯል ማለት አይቻልም።

ዘመን፡- ግን መንግሥት መግለጫ ሲሰጥ ሂደቱ ካለፉት የምርጫ ሂደቶች የተሻለ ነው ብሏል።

አቶ ልደቱ፡- መንግሥት ሁል ጊዜ የሚያካሒዳቸው ምርጫዎች ካለፉት የተሻሉ ናቸው ይላል፡፡ ይሔ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ እኛ ይሔ እንዲለወጥ ነው የምንፈልገው። በመናገር ሳይሆን በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረተ እውነት ነው ለህብረተሰቡ መነገር ያለበት። መንግሥት በየአምስት አመቱ ያደረጋቸውን መግለጫዎች አዳምጣቸው፡፡ ምንም ሳይቆረጡና ሳይቀጠሉ አንድ ዓይነት ናቸው፡፡ ግን በተጨባጭ ያለው ሁኔታ የሚያሳየው እሱን አይደለም።

ዘመን፡- በመጨረሻ ግንቦት 20ን የተመለከተ መልዕክት ካለዎት ያስተላልፉ፤

አቶ ልደቱ፡- በግንቦት 20 የተገኙትን ውጤቶች ይዘን እሱ ያላመጣቸውን ውጤቶችና ከዚያ በኋላ ደግሞ የተፈጠሩ አዳዲስ ቅራኔዎችና ጉድለቶች ለመፍታት መጣር ነው ያለብን፡፡ ሁል ጊዜ ከዜሮ መጀመር የለብንም። እና ግንቦት 20ን በጭፍን መቃወም አይቻልም። በጭፍን ደግሞ በአገሪቱ ያመጣው ነገር ሙሉ ለሙሉ ትክክለኛና ጠቃሚ ነገር ነው ብሎ መከራከር አይቻልም። ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ግንቦት 20ን ማየትና በግንቦት 20 የተገኙት ድሎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የተፈጠሩ ችግሮች እንዲፈቱና ያሉት ጉድለቶች እንዲሟሉ ጥረት ማድረግ ነው የሚጠበቀው ብዬ አምናለሁ።

ዘመን፡- በጣም አመሰግናለሁ አቶ ልደቱ

አቶ ልደቱ፡- በጣም ነው የማመሰግነው።ሳድርና የህዝቡ አስተሳሰብ እንዲሆን ብቻ ሲጥር ነው የምናየው፡፡ እና እነዚህ ነገሮች መፈጠራቸው በራሱ ጥሩ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ግን የተፈጠሩበት ምክንያት አንዱ መንግሥት እንደዚህ አይነት ቅራኔዎች እንዲፈቱና መልካም ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረግ ባለመቻሉ ነው።

አቶ ልደቱ፡- በጣም ነው የማመሰግነው።

ፀሃፊው ሰሎሞን በቀለ

ማህበራዊ ድረገፃችንን ይጎብኙ

የጎብኝዎች ብዛት

0000137269
TodayToday80
YesterdayYesterday126
This_WeekThis_Week1283
This_MonthThis_Month3351
All_DaysAll_Days137269

         በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የመጀመሪያው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ኢትዮኑክስ ስርጭት ላለፉት 8 ዓመታት (1999-2007 ..) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ላለፍት 2 ዓመታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወርሃዊ ጋዜጣ ላይ ላለፈው 1 ዓመት በተግባር ተሞክሮ ሥራ ላይ ውሏል። ይህ ድረገጽ በኢትዮኑክስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ ተገንብቶ የሚሰራ ነው።